ሆሴዕ 2:5-9

ሆሴዕ 2:5-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እና​ታ​ቸው አመ​ን​ዝ​ራ​ለ​ችና፤ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውም፥ “እን​ጀ​ራ​ዬ​ንና ውኃ​ዬን፥ ቀሚ​ሴ​ንና መደ​ረ​ቢ​ያ​ዬን፥ ዘይ​ቴ​ንና የሚ​ገ​ባ​ኝን ሁሉ የሚ​ሰ​ጡኝ ወዳ​ጆ​ችን እከ​ተ​ላ​ቸው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ” ብላ​ለ​ችና አሳ​ፈ​ረ​ቻ​ቸው። ስለ​ዚህ እነሆ ጎዳ​ና​ዋን በእ​ሾህ አጥ​ረ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ድ​ዋ​ንም እዘ​ጋ​ዋ​ለሁ፤ ማለ​ፊ​ያም ታጣ​ለች። ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም ትከ​ተ​ላ​ለች፤ ነገር ግን አት​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ውም፤ ትፈ​ል​ጋ​ቸ​ው​ማ​ለች፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኛ​ቸ​ውም፤ እር​ስ​ዋም፥ “ከዛሬ ይልቅ የዚ​ያን ጊዜ ይሻ​ለኝ ነበ​ርና ተመ​ልሼ ወደ ቀደ​መው ባሌ እሄ​ዳ​ለሁ” ትላ​ለች። እር​ስ​ዋም እህ​ል​ንና ወይ​ንን ዘይ​ት​ንም የሰ​ጠ​ኋት፥ ብር​ንና ወር​ቅን ያበ​ዛ​ሁ​ላት እኔ እንደ ሆንሁ አላ​ወ​ቀ​ችም። እር​ስዋ ግን ወር​ቁ​ንና ብሩን ለጣ​ዖት አደ​ረ​ገች። ስለ​ዚህ እህ​ሌን በጊ​ዜው፥ ወይ​ኔ​ንም በወ​ራቱ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ኀፍ​ረ​ቷ​ንም እን​ዳ​ት​ሸ​ፍን ልብ​ሴ​ንና መጎ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዬን እገ​ፍ​ፋ​ታ​ለሁ።