ሆሴዕ 14:1-9

ሆሴዕ 14:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሰማ​ርያ በአ​ም​ላ​ክዋ ላይ ዐም​ፃ​ለ​ችና ፈጽማ ትጠ​ፋ​ለች፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ነ​ጥ​ቋ​ቸ​ዋል። እስ​ራ​ኤል ሆይ! በኀ​ጢ​አ​ትህ ወድ​ቀ​ሃ​ልና ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለስ። ከእ​ና​ንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተመ​ለሱ። እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ኀጢ​አ​ትን ሁሉ አስ​ወ​ግድ፤ በቸ​ር​ነ​ትም ተቀ​በ​ለን፤ በወ​ይ​ፈ​ንም ፈንታ የከ​ን​ፈ​ራ​ች​ንን ፍሬ ለአ​ንተ እን​ሰ​ጣ​ለን። አሦር አያ​ድ​ነ​ንም፤ በፈ​ረ​ስም ላይ አን​ቀ​መ​ጥም፤ ድሃ​አ​ደ​ጉም በአ​ንተ ዘንድ ይቅ​ር​ታን ያገ​ኛ​ልና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የእ​ጆ​ቻ​ች​ንን ሥራ አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን ናችሁ አን​ላ​ቸ​ውም።” ቍጣዬ ከእ​ርሱ ዘንድ ተመ​ል​ሶ​አ​ልና ሀገ​ራ​ቸ​ውን አድ​ና​ለሁ፤ በእ​ው​ነ​ትም እወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ። ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እንደ ጠል እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እንደ አበ​ባም ያብ​ባል፥ እንደ ሊባ​ኖ​ስም ሥሩን ይሰ​ድ​ዳል። ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ይዘ​ረ​ጋሉ፤ ውበ​ቱም እንደ ወይራ፥ ሽታ​ውም እንደ ሊባ​ኖስ ይሆ​ናል። ተመ​ል​ሰ​ውም ከጥ​ላው ሥር ይቀ​መ​ጣሉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖ​ራሉ፤ ከእ​ህ​ሉም የተ​ነሣ ይጠ​ግ​ባሉ፤ እንደ ወይ​ንም አረግ ያብ​ባሉ ፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውም እንደ ሊባ​ኖስ ወይን ይሆ​ናል። ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ድን ነው? እኔ አደ​ከ​ም​ሁት፤ አጸ​ና​ሁ​ትም፤ እኔ እንደ ተወ​ደደ አበባ አፈ​ራ​ዋ​ለሁ፤ ፍሬ​ህም በእኔ ዘንድ ይገ​ኛል።

ሆሴዕ 14:1-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እስራኤል ሆይ፤ በኀጢአትህ ምክንያት ስለ ወደቅህ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ። የምትሉትን ቃል ይዛችሁ፣ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እንዲህም በሉት፤ “ኀጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን፤ የከንፈራችንንም ፍሬ እንድናቀርብ፣ በምሕረትህ ተቀበለን። አሦር ሊያድነን አይችልም፤ በጦር ፈረሶችም ላይ አንቀመጥም፤ ከእንግዲህም የገዛ እጆቻችን የሠሯቸውን፣ ‘አምላኮቻችን’ አንላቸውም፤ ድኻ አደጉ ከአንተ ርኅራኄ ያገኛልና።” “እኔ ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ፤ እንዲሁ በፈቃደኛነት እወድዳቸዋለሁ፤ ቍጣዬ ከእነርሱ ተመልሷልና። እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤ እንደ ውብ አበባ ያብባል፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም፣ ሥር ይሰድዳል፤ ቅርንጫፉ ያድጋል፤ ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ዝግባ ይሆናል። ሰዎች እንደ ገና ከጥላው በታች ያርፋሉ፤ እርሱም እንደ እህል ይለመልማል፤ እንደ ወይን ተክል ያብባል፤ ዝናውም እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይወጣል። ኤፍሬም ሆይ፤ ከእንግዲህ ከጣዖት ጋራ ምን ጕዳይ አለኝ? የምሰማህና የምጠነቀቅልህ እኔ ነኝ፤ እኔ እንደ ለመለመ የጥድ ዛፍ ነኝ፤ ፍሬያማነትህም ከእኔ የተነሣ ነው።” ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤ አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል። የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።

ሆሴዕ 14:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እስራኤል ሆይ፥ በኃጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ። ከእናንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፥ ወደ እግዚአብሔርም ተመልሳችሁ፦ ኃጢአትን ሁሉ አስወግዱ፥ በቸርነትም ተቀበለን፥ በወይፈንም ፋንታ የከንፈራችንን ፍሬ እንሰጣለን። አሦር አያድነንም፥ በፈረስ ላይ አንቀመጥም፥ ድሀ አደጉም በአንተ ዘንድ ምሕረትን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ ለእጆቻችን ሥራ፦ አምላኮቻችን ናችሁ አንላቸውም በሉት። ቍጣዬ ከእርሱ ዘንድ ተመልሶአልና ዓመፃቸውን እፈውሳለሁ፥ በገዛ ፈቃዴ እወድዳቸዋለሁ። ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ፥ እንደ አበባም ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ሥሩን ይሰድዳል። ቅርንጫፎቹም ይዘረጋሉ፥ ውበቱም እንደ ወይራ፥ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ይሆናል። ከጥላውም በታች የሚቀመጡ ይመለሳሉ፥ ከእህሉም የተነሣ ይጠግባሉ፥ እንደ ወይንም አረግ ያብባሉ፥ መታሰቢያውም እንደ ሊባኖስ ወይን ጠጅ ይሆናል። ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም ምንድር ነው? እኔ ሰምቼዋለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፥ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፥ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል። ይህን ነገር የሚያስተውል ጠቢብ፥ የሚያውቃትም አስተዋይ ማን ነው? የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነው፥ ጻድቃንም ይሄዱበታል፥ ተላላፊዎች ግን ይወድቁበታል።

ሆሴዕ 14:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በኃጢአታችሁ ምክንያት የተሰናከላችሁ ስለ ሆነ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ። የኑዛዜ ቃል ይዛችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እንዲህም በሉት፦ “ኃጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን፤ በምሕረት ተቀበለን፤ እኛም የአንደበታችን መልካም ፍሬ የሆነውን ምስጋና እናቀርብልሃለን። አሦር አያድነንም፥ በጦር ፈረሶችም አንታመንም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በእጃችን የሠራነውን ጣዖት ሁሉ ‘አምላክ’ ብለን አንጠራም፤ አምላክ ሆይ! ወላጆቻቸው የሞቱባቸው በአንተ ምሕረትን ያገኛሉ።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የሕዝቤን አለመታመን ፈውሼ፤ ወደ እኔ እመልሳቸዋለሁ ቊጣዬ ከእነርሱ ስለ ተመለሰ፥ እኔ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ፤ ለእስራኤል ሕዝብ እንደሚወርድ ጠል እሆናለሁ። እነርሱ እንደ አበባ ይፈካሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥር ይሰዳሉ። ቡቃያዎቻቸው ይለመልማሉ፤ እንደ ወይራ ዛፍ የሚያምሩ ይሆናሉ፤ እንደ ሊባኖስ ደን መልካም መዓዛ ይሰጣሉ። ተመልሰውም በእኔ ጥላ ሥር ይሆናሉ፤ እንደ እህል ቡቃያ ይለመልማሉ፤ እንደ ወይን ተክልም ያብባሉ፤ መዓዛቸውም እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ዝነኛ ይሆናል። የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እኔ ከጣዖቶች ጋር ምን ግንኙነት አለኝ? ለጸሎታችሁ መልስ የምሰጥና የምንንከባከባችሁ እኔ ነኝ፤ እኔ ዘወትር ለምለም ሆኖ እንደሚታይ የጥድ ዛፍ ነኝ፤ ፍሬያማ የምትሆኑትም በእኔ አማካይነት ነው።” ጥበብ ያላቸው እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፤ አስተዋዮችም ያውቋቸዋል፤ የእግዚአብሔር መንገድ ትክክል ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ኃጢአተኞች ግን ይሰናከሉበታል።

ሆሴዕ 14:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሰማርያ በአምላክዋ ላይ ዐምፃለችና በደልዋን ትሸከማለች፤ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ሕፃኖቻቸውም ይፈጠፈጣሉ፥ እርጉዞቻቸውም ይቀደዳሉ። እስራኤል ሆይ! በኃጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ተመለስ። ከእናንተ ጋር ቃላትን ውሰዱ፥ ወደ ጌታም ተመለሱ፥ እንዲህም በሉት፦ “በደልን ሁሉ አስወግድ፥ በቸርነትም ተቀበለን፥ በእንቦሳም ፋንታ የከንፈራችንን ፍሬ እንሰጣለን። አሦር አያድነንም፤ በፈረስ ላይ አንቀመጥም፤ ድሀ አደጉም በአንተ ዘንድ ምሕረትን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ ለእጆቻችን ሥራ፦ ‘አምላኮቻችን’ ናችሁ አንላቸውም።” ቁጣዬ ከእርሱ ዘንድ ተመልሶአልና ከዳተኝነታቸውን እፈውሳለሁ፥ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ። ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ፤ እንደ አበባም ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ሥሮቹን ይሰድዳል። ቅርንጫፎቹም ይዘረጋሉ፥ ውበቱም እንደ ወይራ፥ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ይሆናል። ከጥላውም በታች የሚቀመጡ ይመለሳሉ፤ እንደ አትክልት ስፍራ ይለመልማሉ፤ እንደ ወይንም ተክል ያብባሉ፤ መዓዛቸውም እንደ ሊባኖስ ወይን ጠጅ ይሆናል። ኤፍሬም ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ከጣዖታት ጋር እኔ ምን አደርጋለሁ? እኔ እመልስለታለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።