ሆሴዕ 1:2-3
ሆሴዕ 1:2-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር የቃሉ መጀመሪያ ይህ ነው፤ እግዚአብሔር ሆሴዕን፥ “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታመነዝራለችና ሂድ፤ ዘማዊቱን ሴትና የዘማዊቱን ልጆች ለአንተ ውሰድ” አለው። እርሱም ሄዶ የዴብላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርስዋም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደችለት።
ያጋሩ
ሆሴዕ 1 ያንብቡሆሴዕ 1:2-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር በሆሴዕ መናገር በጀመረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ተለይታ ታላቅ ምንዝርና እያደረገች ስለ ሆነ፣ ሄደህ አመንዝራ ሴት አግባ፤ የምንዝርና ልጆችንም ለራስህ ውሰድ” አለው። ስለዚህ እርሱ የዴቤላይምን ሴት ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት።
ያጋሩ
ሆሴዕ 1 ያንብቡሆሴዕ 1:2-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔር መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ሆሴዕን፦ ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለችና ሂድ፥ ጋለሞታን ሴትና የግልሙትናን ልጆች ለአንተ ውሰድ አለው። እርሱም ሄዶ የዴቤላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፥ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደችለት።
ያጋሩ
ሆሴዕ 1 ያንብቡ