ሆሴዕ 1:2-11

ሆሴዕ 1:2-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ወደ ሆሴዕ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃሉ መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆሴ​ዕን፥ “ምድ​ሪቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቃ ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለ​ችና ሂድ፤ ዘማ​ዊ​ቱን ሴትና የዘ​ማ​ዊ​ቱን ልጆች ለአ​ንተ ውሰድ” አለው። እር​ሱም ሄዶ የዴ​ብ​ላ​ይ​ምን ልጅ ጎሜ​ርን አገባ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደ​ች​ለት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከጥ​ቂት ዘመን በኋላ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልን ደም በይ​ሁዳ ቤት ላይ እበ​ቀ​ላ​ለ​ሁና፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት መን​ግ​ሥ​ትን እሽ​ራ​ለ​ሁና ስሙን ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ብለህ ጥራው፤ በዚ​ያም ጊዜ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ሸለቆ ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቀስት እሰ​ብ​ራ​ለሁ” አለው። ደግሞ ፀነ​ሰች፤ ሴት ልጅ​ንም ወለ​ደች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “መለ​የ​ትን እለ​ያ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ ይቅር እላ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​ም​ራ​ቸ​ው​ምና ስም​ዋን ኢሥ​ህ​ልት ብለህ ጥራት፤ ነገር ግን የይ​ሁ​ዳን ልጆች ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ በቀ​ስት ወይም በሰ​ይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠ​ረ​ገላ፥ ወይም በፈ​ረ​ሶች፥ ወይም በፈ​ረ​ሰ​ኞች የማ​ድ​ና​ቸው አይ​ደ​ለም” አለው። ኢሥ​ህ​ል​ት​ንም ጡት ባስ​ጣ​ሏት ጊዜ፥ ደግሞ ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሕዝቤ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና፥ እኔም አም​ላክ አል​ሆ​ና​ች​ሁ​ምና ስሙን ኢሕ​ዝ​ብየ ብለህ ጥራው” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ቍጥር እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​ፈ​ርና እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ “እና​ንተ ሕዝቤ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም” ተብሎ በተ​ነ​ገ​ረ​በት በዚያ ስፍራ የሕ​ያው አም​ላክ ልጆች ይባ​ላሉ። የይ​ሁዳ ልጆ​ችና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አንድ አለቃ ይሾ​ማሉ፤ ከም​ድ​ሪ​ቱም ይወ​ጣሉ፤ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ቀን ታላቅ ይሆ​ና​ልና።

ሆሴዕ 1:2-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር በሆሴዕ መናገር በጀመረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ተለይታ ታላቅ ምንዝርና እያደረገች ስለ ሆነ፣ ሄደህ አመንዝራ ሴት አግባ፤ የምንዝርና ልጆችንም ለራስህ ውሰድ” አለው። ስለዚህ እርሱ የዴቤላይምን ሴት ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት። እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፤ “በኢይዝራኤል ስለ ተፈጸመው ግድያ የኢዩን ቤት በቅርቡ ስለምቀጣና የእስራኤልንም መንግሥት እንዲያከትም ስለማደርግ፣ ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው። በዚያም ቀን በኢይዝራኤል ሸለቆ፣ የእስራኤልን ቀስት እሰብራለሁ።” ጎሜር እንደ ገና ፀነሰች፤ ሴት ልጅም ወለደች፤ እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፤ “ይቅር እላቸው ዘንድ ለእስራኤል ቤት ከእንግዲህ ስለማልራራላቸው፣ ስሟን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት። ነገር ግን ለይሁዳ ቤት እራራለሁ፤ በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶችና በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በእግዚአብሔር አድናቸዋለሁ።” ጎሜር፣ ሎሩሃማን ጡት ካስጣለች በኋላ ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ሎዓሚ ብለህ ጥራው፤ ምክንያቱም እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም፤ እኔም አምላካችሁ አይደለሁምና። “ይሁን እንጂ እስራኤላውያን ሊሰፈርና ሊቈጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናሉ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ በተባሉበት ቦታ፣ ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ። የይሁዳ ሕዝብና የእስራኤል ሕዝብ እንደ ገና አንድ ይሆናሉ፤ አንድ መሪም ይሾማሉ፤ አንድ ሆነውም በምድሪቱ ይገንናሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።

ሆሴዕ 1:2-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር በሆሴዕ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን ማስተላለፍ ሲጀምር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቤ ከእኔ ተለይቶ አጸያፊ የሆነ የዝሙት ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፤ እንግዲህ አንተም ሂድና ዘማዊት ሴት አግባ፤ ከእርስዋም የዝሙት ልጆችን ውለድ።” ስለዚህ ሆሴዕ ሄዶ የዲብላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደችለት። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ኢዩና ዘሮቹ በኢይዝራኤል በገደሉአቸው ሰዎች ምክንያት የኢዩን ቤተሰብ የምቀጣበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፤ የእስራኤልም መንግሥት እንዲያከትም አደርጋለሁ፤ በዚያን ጊዜ በኢይዝራኤል ሸለቆ የእስራኤልን ጦር እደመስሳለሁ፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ኢይዝራኤል’ ብለህ ጥራው።” ጎሜር ዳግመኛ ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፤ እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ ከእንግዲህ ወዲህ ፍቅር አላሳያቸውም፤ ይቅርታም አላደርግላቸውም፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ሎሩሐማ’ ብለህ ጥራት። ለይሁዳ ሕዝቦች ግን ፍቅር አሳያቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ፤ የማድናቸውም በጦርነት ኀይል አይደለም፤ በሰይፍ፥ በቀስትና በፍላጻ ወይም በፈረስና በፈረሰኛ አይደለም።” ጎሜር ሎሩሐማን ጡት ካስጣለች በኋላ እንደገና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። እግዚአብሔርም ሆሴዕን “ከእንግዲህ ወዲህ የእስራኤል ሕዝብ ወገኖቼ አይደሉም፤ እኔም የእነርሱ አምላክ አይደለሁም፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ሎዓሚ’ ብለህ ጥራው አለው።” የእስራኤል ሕዝብ ብዛት ሊቈጠር ወይም ሊለካ እንደማይቻል የባሕር አሸዋ ይሆናል፤ አሁን እግዚአብሔር “ሕዝቤ አይደላችሁም” ቢላቸው በዚሁ ስፍራ “የሕያው እግዚአብሔር ልጆች!” ተብለው የሚጠሩበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ አንድ ይሆናሉ፤ ሁለቱንም የሚያስተዳድር አንድ መሪ ይመርጣሉ፤ እንደገናም በገዛ ምድራቸው ላይ በዕድገትና በብልጽግና ይኖራሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናል።