ዕብራውያን 4:1-3
ዕብራውያን 4:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንግዲህ አንፍራ፤ ወደ ዕረፍቱም እንድንገባ ትእዛዙን አንተው፤ ከእናንተም ምንአልባት በተለመደ ስሕተት የሚገኝና የሚጸና ቢኖር ወደ ዕረፍቱ እንዲገባ የሚተዉት አይምሰለው። ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛም የምሥራች ተሰብኮልናል፤ ነገር ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። ሥራዉ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፥ “እንግዲህ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቍጣዬ ማልሁ” እንዳለ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።
ዕብራውያን 4:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንግዲህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት የተሰጠው ተስፋ አሁንም የተጠበቀ ስለ ሆነ፣ ከእናንተ ማንም ለዚያ ሳይበቃ እንዳይቀር እንጠንቀቅ። ለእነዚያ እንደ ተሰበከ ለእኛም ደግሞ ወንጌል ተሰብኮልናልና። ነገር ግን ሰሚዎቹ ቃሉን ከእምነት ጋራ ስላላዋሐዱት አልጠቀማቸውም። እኛ ያመንነው ግን ወደዚያ ዕረፍት እንገባለን፤ እግዚአብሔርም፣ “ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤ ‘ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም’ ” ብሏል። ይሁን እንጂ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የርሱ ሥራ ተከናውኗል።
ዕብራውያን 4:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንግዲህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት ተስፋ ገና ቀርቶልን ከሆነ፥ ምናልባት ከእናንተ ማንም የማይበቃ መስሎ እንዳይታይ እንፍራ። ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።
ዕብራውያን 4:1-3 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ስለዚህ እርሱ ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ ለመግባት የተቀበልነው ተስፋ ገና የጸና ስለ ሆነ ከእናንተ ማንም ወደዚህ የዕረፍት ቦታ የመግባት ዕድል ሳያገኝ እንዳይቀር ሁላችንም እንጠንቀቅ። መልካሙን ዜና እነርሱ እንደ ሰሙት እኛም ሰምተነዋል፤ ነገር ግን እነርሱ የሰሙትን ቃል በእምነት ስላልተቀበሉት አልጠቀማቸውም። የእርሱ ሥራ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ፦ “እኔ ወደምሰጣቸው የዕረፍት ቦታ ከቶ አይገቡም ብዬ በቊጣዬ ምዬአለሁ” እንዳለው አሁንም እኛ የምናምነው ወደዚያ እግዚአብሔር ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ እንገባለን፤
ዕብራውያን 4:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ስለዚህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት ገና ተስፋ ቀርቶልን ከሆነ፥ ከእናንተ ማንም የማይበቃ መስሎ እንዳይታይ እንጠንቀቅ። የምሥራቹ ዜና ለእነርሱም እንደ ተነገረ ለእኛ ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም “እንዲህ ‘ወደ ዕረፍቴ አይገቡም፤’ ብዬ በቁጣዬ ማልሁ፤” እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።