ዕብራውያን 13:5-6
ዕብራውያን 13:5-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ገንዘብ ሳትወዱ ኑሩ፤ ያላችሁም ይበቃችኋል፤ እርሱ “አልጥልህም፤ ቸልም አልልህም” ብሎአልና። አሁንም አምነን፥ “እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንበል።
ዕብራውያን 13:5-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር፣ “ከቶ አልተውህም፤ በፍጹም አልጥልህም” ብሏል። ስለዚህ በሙሉ ልብ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።
ዕብራውያን 13:5-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤ ስለዚህ በድፍረት፦ ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን።
ዕብራውያን 13:5-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከገንዘብ ፍቅር ራቁ፤ ያላችሁ ይብቃችሁ፤ እግዚአብሔር “ከቶ አልጥልህም፤ ፈጽሞም አልተውህም” ብሎአል። ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።