ዕብራውያን 11:1-2
ዕብራውያን 11:1-2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እምነትስ ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የምታረጋግጥ፥ የማናየውንም ነገር የምታስረዳ ናት። በዚህም ለሽማግሌዎች ተመሰከረላቸው።
ዕብራውያን 11:1-2 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እምነት ተስፋ ያደረግነው ነገር እንደሚፈጸም ርግጠኛ የምንሆንበት፣ የማናየውም ነገር እውን መሆኑን የምንረዳበት ነው። አባቶችም የተመሰከረላቸው በዚሁ ነው።
ዕብራውያን 11:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና።
ዕብራውያን 11:1-2 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እምነት ማለት በተስፋ የሚጠበቀውን ነገር “አዎን በእውነት ይሆናል” ብሎ መቀበል ነው፤ በዐይን የማይታየውንም ነገር እንደሚታይ አድርጎ መቊጠር ነው። የቀድሞ ሰዎች የተመሰገኑት በእምነት ምክንያት ነው።