ዕብራውያን 10:17-18
ዕብራውያን 10:17-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከእንግዲህ ወዲህ ኀጢአታቸውንና በደላቸውን ደግሜ አላስብባቸውም” ብሏል። እንዲህም ኀጢአት የሚሰረይ ከሆነ፥ እንግዲህ ወዲህ ስለ ኀጢአት መሥዋዕት አያስፈልግም።
ዕብራውያን 10:17-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ደግሞም፣ “ኀጢአታቸውንና ዐመፃቸውን፣ ከእንግዲህ አላስብም” ይላል። እነዚህ ይቅር ከተባሉ በኋላ ከእንግዲህ ስለ ኀጢአት የሚቀርብ መሥዋዕት አይኖርም።
ዕብራውያን 10:17-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ብሎ ከተናገረ በኋላ፥ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል። የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም።