ዕንባቆም 3:1-19

ዕንባቆም 3:1-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት በመዝሙር። አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፣ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፣ በዓመታት መካከል ትታወቅ፣ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ። እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል። ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፣ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፣ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል። ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል። ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው። የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፣ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። በውኑ እግዚአብሔር በወንዞች ላይ ተቈጥቶአልን? ቍጣህ በወንዞች ላይ፥ መዓትህም በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህና በማዳንህ ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና። በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፣ ቀስትህንም ገተርህ፣ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ። ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ፣ የውኃ ሞገድ አልፎአል፣ ቀላዩም ድምፁን ሰጥቶአል፥ እጁንም ወደ ላይ አንሥቶአል። ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሃን የተነሣ፥ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሣ፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ። በምድር ላይ በመዓት ተራመድህ፣ አሕዛብን በቍጣ አሄድሃቸው። ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፣ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፣ መሠረቱን እስከ አንገቱ ድረስ ገለጥህ። የአለቆችን ራስ በገዛ በትራቸው ወጋህ፣ እኔን ይበትኑ ዘንድ እንደ ዐውሎ ነፋስ መጡ፣ ችግረኛውን በስውር ለመዋጥ ደስታቸው ነው። ፈረሶችህን በባሕር፥ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ። እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ። ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፣ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፣ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፣ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።

ዕንባቆም 3:1-19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ሆይ፤ ዝናህን ሰምቻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህም አስፈራኝ፤ በእኛ ዘመን አድሳቸው፤ በእኛም ጊዜ እንዲታወቁ አድርግ፤ በመዓት ጊዜ ምሕረትን ዐስብ። አምላክ ከቴማን፣ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ መጣ። ሴላ ክብሩ ሰማያትን ሸፈነ፤ ውዳሴውም ምድርን ሞላ። ጸዳሉ እንደ ፀሓይ ብርሃን ነው፤ ጨረር ከእጁ ወጣ፤ ኀይሉም በዚያ ተሰውሯል። መቅሠፍት በፊቱ ሄደ፤ ቸነፈርም እግር በእግር ተከተለው። ቆመ፤ ምድርን አንቀጠቀጠ፤ ተመለከተ፤ ሕዝቦችን አብረከረከ፤ የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ፤ የጥንት ኰረብቶችም ፈራረሱ፤ መንገዱ ዘላለማዊ ነው። የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣ የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ በወንዞች ላይ ተቈጣህን? መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን? በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሠረገሎችህ በጋለብህ ጊዜ፣ በባሕር ላይ ተቈጥተህ ነበርን? ቀስትህን አዘጋጀህ፤ ፍላጻም እንዲመጣልህ አዘዝህ፤ ሴላ ምድርን በወንዞች ከፈልህ፤ ተራሮች አዩህ፤ ተጨነቁም፤ የውሃ ሞገድ ዐልፎ ሄደ፤ ቀላዩ ደነፋ፤ ማዕበሉንም ወደ ላይ አነሣ። ከሚወረወሩ ፍላጾችህ፣ ከሚያብረቀርቅ የጦርህ ነጸብራቅ የተነሣም፣ ፀሓይና ጨረቃ በቦታቸው ቆሙ። በምድር ላይ በመዓት ተመላለስህ፤ ሕዝቦችንም በቍጣ ረገጥሃቸው። ሕዝብህን ለመታደግ፣ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤ የክፋትን ምድር መሪ ቀጠቀጥህ፤ ከራስ ጠጕሩ እስከ እግር ጥፍሩም ዕርቃኑን አስቀረኸው። ሴላ እንደ ዐውሎ ነፋስ ሊበታትነን የመጣውን፣ ምስኪኑን በስውር በመዋጥ የሚደሰተውን፣ የሰራዊት አለቃ ራስ፣ በገዛ ጦሩ ወጋህ። ታላላቅ ውሆችን በመናጥ፣ ባሕሩን በፈረሶችህ ረገጥህ። እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤ እግሬም ተብረከረከ፤ ሆኖም በሚወርረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣ የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ። ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣ የበጎች ጕረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በድነቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኀይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።

ዕንባቆም 3:1-19 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት በመዝሙር። አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፥ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፥ በዓመታት መካከል ትታወቅ፥ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ። እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል። ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፥ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፥ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል። ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል። ቆመ፥ ምድርንም አወካት፥ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፥ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፥ መንገዱ ከዘላለም ነው። የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፥ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። በውኑ እግዚአብሔር በወንዞች ላይ ተቈጥቶአልን? ቍጣህ በወንዞች ላይ፥ መዓትህም በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህና በማዳንህ ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና። በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፥ ቀስትህንም ገተርህ፥ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ። ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ፥ የውኃ ሞገድ አልፎአል፥ ቀላዩም ድምፁን ሰጥቶአል፥ እጁንም ወደ ላይ አንሥቶአል። ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሃን የተነሣ፥ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሣ፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ። በምድር ላይ በመዓት ተራመድህ፥ አሕዛብን በቍጣ አሄድሃቸው። ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፥ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፥ መሠረቱን እስከ አንገቱ ድረስ ገለጥህ። የአለቆችን ራስ በገዛ በትራቸው ወጋህ፥ እኔን ይበትኑ ዘንድ እንደ ዐውሎ ነፋስ መጡ፥ ችግረኛውን በስውር ለመዋጥ ደስታቸው ነው። ፈረሶችህን በባሕር፥ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ። እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፥ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፥ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ። ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፥ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፥ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፥ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።

ዕንባቆም 3:1-19 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በመዝሙር የቀረበ የነቢዩ ዕንባቆም ጸሎት ይህ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ! ስላደረግኸው አስደናቂ ሥራ ሁሉ ሰምቼ እጅግ ፈራሁ፤ አሁንም በዘመናችን የቀድሞውን ሥራህን ደግመህ አድርግ፤ በየዘመናቱም እንዲታወቅ አድርግ፤ በምትቈጣበት ጊዜ እንኳ ምሕረትህን አታርቅ። እግዚአብሔር በቅድስናው ከቴማን አገርና፥ ከፋራን ተራራ እንደገና ይመጣል፤ መለኮታዊ ክብሩ ሰማያትን ሸፍኖአል፤ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል። ብርሃኑ እንደ ፀሐይ ብርሃን ነው ኀይሉን ከሸፈነው እጁም የብርሃን ጮራ ይወጣል፤ ቸነፈር ፊት ፊቱ ይሄዳል፤ መቅሠፍትም ከኋላው ይከተለዋል። እርሱ ሲቆም ምድር ትናወጣለች፤ እርሱ ሲመለከታቸው ሕዝቦች ይንቀጠቀጣሉ፤ የጥንቱ ተራራዎች ይናዳሉ፤ ከጥንት ጀምሮ የእርሱ መረማመጃ የነበሩት ኰረብቶች ወደ ታች ይሰጥማሉ። የኢትዮጵያ ሰፈር ሲጨነቅ፥ የምድያምም ሰዎች ሲንቀጠቀጡ አየሁ። እግዚአብሔር ሆይ! ፈረሶችህንና ሠረገላዎችህን ወደ ድል በመራኸቸው ጊዜ፥ ኀይለኛው ቊጣህ በወንዞች ላይ ነበርን? ወይስ በባሕሩ ላይ ተቈጥተህ ነበርን? ቀስትህን ከሰገባው አወጣህ፤ ፍላጻህንም ለመወርወር አነጣጠርህ፤ ምድሪቱንም ሰንጥቀህ ወንዞች አስገኘህ። ተራራዎች አንተን አይተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ የዝናብም ጐርፍ ምድርን እየጠራረገ አለፈ፤ ውቅያኖስ ከፍተኛ ድምፅ አሰማ፤ ማዕበሉም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ። እንደ ፍላጻ ከሚወረወረውና እንደ ጦር ከሚያንጸባርቀው መብረቅህ የተነሣ ፀሐይና ጨረቃ በየቦታቸው ቆሙ። በምድር ላይ ቆምክ፤ በቊጣህም ሕዝቦችን ረጋገጥካቸው። ሕዝብህን ለመታደግ፥ ቀብተህ ያነገሥከውንም ንጉሥ ለማዳን ወጣህ፤ የጥፋት አገር መሪ የሆነውን ቀጠቀጥከው፤ ተከታዮቹንም አጥፍተህ እርቃኑን አስቀረኸው። ከእግር እስከ ራሱም አራቈትከው። እኛን ለመበታተን እንደ ዐውሎ ነፋስ የመጣውን የጦረኞቹን አለቃ በገዛ ቀስቱ ወጋኸው። ደካማ እንስሶችን ለመቦጨቅ እንደሚጓጓ አውሬ እርሱም የተደበቁትን ድኾች ለማጥቃት የተዘጋጀ ነበር። አንተ ባሕሩን በፈረሶችህ በምትረጋግጥበት ጊዜ ጥልቁ ባሕር ይናወጣል። ይህን ሁሉ ስሰማ ሰውነቴ ይርበደበዳል፤ ድምፁም ከንፈሮቼን ያንቀጠቅጣል፤ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼ ከታች ይብረከረካሉ፤ በጠላቶቻችን ላይ መከራ የሚደርስበትን ጊዜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ። ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፥ በወይን ተክል ላይም ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ዛፍም ምንም ፍሬ ባይሰጥ፥ በእርሻዎች ላይ ሰብል ቢጠፋ፥ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፥ በበረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፥ ይህም ሁሉ ቢሆን፥ እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በአምላኬ፥ በመድኃኒቴ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴ ነው፤ እግሮቼንም እንደ ዋልያ እግሮች ያጠነክርልኛል፤ በተራሮችም ላይ እንድራመድ ያደርገኛል።

ዕንባቆም 3:1-19 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት በሺግዮኖት። ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ። እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፓራን ተራራ መጣ። (ሴላ) ውበቱ ሰማያትን ሸፍኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል። ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፥ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፤ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል። ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ መቅሠፍትም ከእግሩ ይወጣል። ቆመ፥ ምድርንም አንቀጠቀጣት፥ ተመለከተ፥ ሕዝቦችንም አስደነገጠ፥ የዘለዓለም ተራሮች ተናጉ፥ የጥንት ኮረብቶች አጎነበሱ፥ የጥንት መንገዶች የእርሱ ናቸው። የኢትዮጵያ ድንኳኖች በጭንቀት ላይ ሆነው አየሁ፥ የሚድያን ምድር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። ጌታ ሆይ ንዴትህ በወንዞች ላይ ነውን? ወይስ ቁጣህ በወንዞች ላይ ወይም መዓትህ በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህ፥ በማዳን ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና። ቀስትህን ገለጥህ በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፤ ቀስትህንም ገተርህ፤ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ። ተራሮች አንተን አይተው ተወራጩ፥ የውኃ ወጀብ አለፈ፥ ጥልቁም ድምፁን ሰጠ፥ እጁንም ወደ ላይ አነሳ። በቀስቶችህ ብርሃን፥ በጦርህ መብረቅ ፀዳል፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቀጥ ብለው ቆሙ። በቁጣ ምድርን ረገጥሃት፥ አሕዛብን በንዴት አሄድሃቸው። ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፥ ከመሠረቱ እስከ አንገቱ ድረስ አራቆትህ። ደስታቸው የተደበቁ ችግረኞችን እንደሚውጥ የሆነውን፥ እኛን ሊበትኑ እንደ ዐውሎ ነፋስ የመጡትን፤ የጦረኛውን ራስ በገዛ ጦሩ ወጋህ፤ በፈረሶችህ በባሕር ላይ ተራመድህ፥ ብዙ ውኆችንም ረገጥህ። እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ። የበለስ ዛፍ ባታብብም፥ በወይን ተክሎች ላይ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ምርት ቢቋረጥ፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ከብቶችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በጌታ ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎቼም ላይ ያስሄደኛል። ለመዘምራን አለቃ፥ በባለ አውታር መሣሪያዎቼ።