ዘፍጥረት 9:20-29

ዘፍጥረት 9:20-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፤ ወይ​ንም ተከለ። ከወ​ይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ ዕራ​ቁ​ቱን ሆነ። የከ​ነ​ዓን አባት ካምም የአ​ባ​ቱን ዕራ​ቁ​ት​ነት አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁ​ለቱ ወን​ድ​ሞቹ ነገ​ራ​ቸው። ሴምና ያፌ​ትም ልብስ ወስ​ደው በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ አደ​ረጉ፤ የኋ​ሊ​ትም ሄደው የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ዕራ​ቁ​ት​ነት አለ​በሱ፤ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ኋላ ነበር፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም ዕራ​ቁ​ት​ነት አላ​ዩም። ኖኅም ከወ​ይኑ ስካር በነቃ ጊዜ፥ ታናሹ ልጁ ያደ​ረ​ገ​በ​ትን ዐወቀ። ኖኅም እን​ዲህ አለ፥ “ከነ​ዓን ርጉም ይሁን፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የባ​ሪ​ያ​ዎች ባሪያ ይሁን።” እን​ዲ​ህም አለ፥ “የሴም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ረክ፤ ከነ​ዓ​ንም ለእ​ርሱ ባሪያ ይሁን። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የያ​ፌ​ትን ሀገር ያስፋ፤ በሴ​ምም ድን​ኳን ይደር፤ ከነ​ዓ​ንም ለእ​ርሱ ባሪያ ይሁን።” ኖኅም ከጥ​ፋት ውኃ በኋላ ሦስት መቶ አምሳ ዓመት ኖረ። ኖኅም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።

ዘፍጥረት 9:20-29 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኖኅ ገበሬ ነበረ፤ የወይን ተክልንም መትከል ጀመረ፤ ከዕለታት አንድ ቀን ኖኅ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰከረ፤ ልብሱንም አውልቆ ራቊቱን በድንኳን ውስጥ ተኛ። የከነዓን አባት የሆነው ካም፥ አባቱ ኖኅ እራቁቱን እንደ ሆነ ባየ ጊዜ ወደ ውጪ ወጥቶ፥ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ልብስ በስተኋላቸው፥ በትከሻቸው ያዙ፤ ወደ ድንኳኑም የኋሊት ሄዱና የአባታቸውን ራቊትነት እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው ራቊትነቱን ሸፈኑ፤ የአባታቸውንም ራቊትነት ኣላዩም። ኖኅ ስካሩ አልፎለት ሲነቃ፥ ትንሹ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤ እንዲህም አለ፤ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹ የአገልጋዮች አገልጋይ ይሁን፤ እንደገናም እንዲህ አለ፤ የሴም አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! ከነዓንም የሴም አገልጋይ ይሁን! እግዚአብሔር የያፌትን ምድር ያስፋ! የያፌት ዘሮች ከሴም ዘሮች ጋር አብረው ይኑሩ! ከነዓን የያፌት አገልጋይ ይሁን።” ከጥፋት ውሃ በኋላ ኖኅ 350 ዓመት ኖረ። ዕድሜውም 950 ዓመት ሲሆነው ሞተ።

ዘፍጥረት 9:20-29 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ኖኅ ቀዳሚ ገበሬ ነበረ፤ የወይን ተክልንም ተከለ። ከዕለታት አንድ ቀን ከወይን ጠጁም ጠጣ፥ ሰከረም፥ በድንኳኑም ውስጥ እራቁቱን ተኛ። የከነዓን አባት፥ ካምም፥ የአባቱን ዕራቁቱን መሆን አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ልብስ በትከሻቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም። ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፥ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ። እንዲህም አለ፦ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹም የባርያዎች ባርያ ይሁን።” ደግሞም እንዲህ አለ፦ “የሴም ጌታ እግዚእብሔር ይባረክ! ከነዓንም የሴም አገልጋይ ይሁን! “እግዚአብሔርም ያፌትን ያደርጀው! በሴምም ድንኳን ይደር! ከነዓንም የያፌት አገልጋይ ይሁን!” ከጥፋት ውኃ በኋላም ኖኅ ሦስት መቶ አምሳ ዓመት ኖረ። ኖኅም የኖረበት ዘመን በአጠቃላይ ዘጠኝ መቶ አምሳ ዓመት ሆነ፥ ሞተም።