ዘፍጥረት 7:17-24

ዘፍጥረት 7:17-24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ነበረ፤ ውኃ​ውም በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱ​ንም አነሣ፤ ከም​ድ​ርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች። ውኃ​ውም አሸ​ነፈ፤ በም​ድር ላይም እጅግ በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም በውኃ ላይ ተን​ሳ​ፈ​ፈች። ውኃ​ውም በም​ድር ላይ እጅግ በጣም አሸ​ነፈ፤ ከሰ​ማይ በታች ያሉ ረዣ​ዥም ተራ​ሮ​ችን ሁሉ ሸፈነ። ውኃው ወደ ላይ ዐሥራ አም​ስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ፤ ረዣ​ዥም ተራ​ሮ​ች​ንም ሸፈነ። በም​ድር ላይ ሥጋ ያለው የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ ወፉም፥ እን​ስ​ሳ​ውም፥ አራ​ዊ​ቱም፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሹ​ም​ሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ። የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋስ ያለው ሁሉ፥ በየ​ብ​ስም ያለው ሁሉ ሞተ። በም​ድር ላይ የነ​በ​ረ​ውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ፥ እስ​ከ​ሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰ​ውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደ​መ​ሰሰ፤ ከም​ድ​ርም ተደ​መ​ሰሱ። ኖኅም አብ​ረ​ውት በመ​ር​ከብ ከነ​በ​ሩት ጋር ብቻ​ውን ቀረ። ውኃ​ውም መቶ አምሳ ቀን በም​ድር ላይ ሞላ።