ዘፍጥረት 7:1-24

ዘፍጥረት 7:1-24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተ​ሰ​ቦ​ች​ህን ሁሉ ይዘህ ወደ መር​ከብ ግባ፤ በዚህ ትው​ልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይ​ች​ሃ​ለ​ሁና። ከን​ጹሕ እን​ስሳ ሁሉ ሰባት ስባት ተባ​ትና እን​ስት፥ ንጹሕ ካል​ሆ​ነም እን​ስሳ ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት፤ ከን​ጹሕ የሰ​ማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባ​ትና እን​ስት፥ ንጹሕ ካል​ሆነ የሰ​ማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት እያ​ደ​ረ​ግህ በም​ድር ላይ ለም​ግ​ብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ። ከሰ​ባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በም​ድር ላይ ዝናብ አዘ​ን​ባ​ለ​ሁና፤ የፈ​ጠ​ር​ሁ​ት​ንም ፍጥ​ረት ሁሉ ከም​ድር ሁሉ ላይ አጠ​ፋ​ለ​ሁና።” ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ። ኖኅም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ በሆነ ጊዜ የስ​ድ​ስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ። ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆ​ቹ​ንና ሚስ​ቱን፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ይዞ ወደ መር​ከብ ገባ። ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችና ንጹ​ሓን ካል​ሆኑ ወፎች፥ ከን​ጹሕ እን​ስሳ፥ ንጹ​ሕም ካል​ሆ​ነው እን​ስሳ፥ በም​ድር ላይ ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኖኅን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት እየ​ሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መር​ከብ ውስጥ ገቡ። ከሰ​ባት ቀን በኋ​ላም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ ሆነ። በኖኅ ዕድሜ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው መቶ ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዕለት፥ በዚ​ያው ቀን የታ​ላቁ ቀላይ ምን​ጮች ሁሉ ተነ​ደሉ፤ የሰ​ማይ መስ​ኮ​ቶ​ችም ተከ​ፈቱ፤ ዝና​ቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በም​ድር ላይ ሆነ። በዚ​ያ​ውም ቀን ኖኅ ወደ መር​ከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆ​ችም ሴም፥ ካም፥ ያፌ​ትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስ​ቱም የል​ጆቹ ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ገቡ። አራ​ዊ​ትም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ እን​ስ​ሳ​ትም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ወፎ​ችም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ የሚ​በሩ ወፎ​ችም ሁሉ፥ ሥጋ ያላ​ቸው ሕያ​ዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየ​ሆኑ ወደ ኖኅ መር​ከብ ውስጥ ገቡ። ሥጋ ካለው ሁሉ የገ​ቡ​ትም ተባ​ትና እን​ስት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኖኅን እን​ዳ​ዘ​ዘው ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መር​ከ​ብ​ዋን በስ​ተ​ውጭ ዘጋት። የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ነበረ፤ ውኃ​ውም በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱ​ንም አነሣ፤ ከም​ድ​ርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች። ውኃ​ውም አሸ​ነፈ፤ በም​ድር ላይም እጅግ በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም በውኃ ላይ ተን​ሳ​ፈ​ፈች። ውኃ​ውም በም​ድር ላይ እጅግ በጣም አሸ​ነፈ፤ ከሰ​ማይ በታች ያሉ ረዣ​ዥም ተራ​ሮ​ችን ሁሉ ሸፈነ። ውኃው ወደ ላይ ዐሥራ አም​ስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ፤ ረዣ​ዥም ተራ​ሮ​ች​ንም ሸፈነ። በም​ድር ላይ ሥጋ ያለው የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ ወፉም፥ እን​ስ​ሳ​ውም፥ አራ​ዊ​ቱም፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሹ​ም​ሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ። የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋስ ያለው ሁሉ፥ በየ​ብ​ስም ያለው ሁሉ ሞተ። በም​ድር ላይ የነ​በ​ረ​ውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ፥ እስ​ከ​ሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰ​ውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደ​መ​ሰሰ፤ ከም​ድ​ርም ተደ​መ​ሰሱ። ኖኅም አብ​ረ​ውት በመ​ር​ከብ ከነ​በ​ሩት ጋር ብቻ​ውን ቀረ። ውኃ​ውም መቶ አምሳ ቀን በም​ድር ላይ ሞላ።

ዘፍጥረት 7:1-24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ትውልድ መካከል አንተን ጻድቅ ሆነህ አግኝቼሃለሁና ቤተ ሰብህን በሙሉ ይዘህ ወደ መርከቧ ግባ። ከንጹሕ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፣ ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት ውሰድ፤ እንዲሁም ከወፎች ወገን ሁሉ ሰባት ተባዕትና ሰባት እንስት፣ በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋራ ታስገባለህ። ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ።” ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በወረደ ጊዜ ኖኅ የስድስት መቶ ዓመት ሰው ነበር። ኖኅና ወንዶች ልጆቹ፣ ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች ከጥፋት ውሃ ለመትረፍ ወደ መርከቧ ገቡ። ንጹሕ ከሆኑትና ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት፣ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ጥንድ ጥንድ፣ ተባዕትና እንስት ሆነው ወደ ኖኅ መጡ፤ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘውም መሠረት ወደ መርከቧ ገቡ። ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ። ኖኅ በተወለደ በስድስት መቶኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ቀን፣ በዚያ ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ ዘነበ። በዚያ ዕለት ኖኅና ልጆቹ ሴም፣ ካምና ያፌት፣ እንዲሁም ሚስቱና ሦስቱ የልጆቹ ሚስቶች ወደ መርከቧ ገቡ። ከዱር እንስሳት ከየወገኑ፣ ከቤት እንስሳት ከየወገኑ፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ከየወገናቸው፣ ከወፎችም ከየወገናቸውና ክንፍ ያላቸው ሁሉ ዐብረዋቸው ገቡ። የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸው ፍጥረታት በሙሉ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ወደ ኖኅ በመምጣት መርከቧ ውስጥ ገቡ። ከሕያዋንም ፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘው መሠረት ተባዕትና እንስት እየሆኑ ገቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ከውጭ ዘጋበት። የጥፋት ውሃም ለአርባ ቀናት ያለ ማቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ፤ ውሃው እየጨመረ በሄደ መጠን መርከቧን ከምድር ወደ ላይ አነሣት። ውሃው በምድር ላይ በጣም እየጨመረና ከፍ እያለ ሲሄድ፣ መርከቧ በውሃው ላይ ተንሳፈፈች። ውሃው በጣም ከፍ በማለቱ፣ ከሰማይ በታች ያሉትን ታላላቅ ተራሮች ሁሉ ሸፈናቸው። ውሃው ከተራሮቹ ጫፍ በላይ 7 ሜትር ያህል ከፍ አለ። በምድር ላይ የነበሩ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፦ ወፎች፣ የቤት እንሰሳት፣ የዱር እንስሳት በምድር የሚርመሰመሱ ፍጥረታት፣ ሰዎችም በሙሉ ጠፉ። በአፍንጫቸው የሕይወት እስትንፋስ ያላቸው በየብስ የነበሩ ፍጥረታት ሁሉ ሞቱ። ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት ሁሉ ከምድር ገጽ ጠፉ፤ ሰዎችና እንስሳት በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና የሰማይ ወፎች ከምድር ላይ ጠፉ፤ ኖኅና ከርሱ ጋራ በመርከቧ ውስጥ የነበሩት ብቻ ተረፉ። ውሃውም ምድርን ሸፍኖ መቶ ዐምሳ ቀን ቈየ።

ዘፍጥረት 7:1-24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፤ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይቼሃለሁና። ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት ንጽሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፤ ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት እያደረልግልህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትውስዳለህ። ከሰባት ቀን በኍላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ አጠፉለሁና። ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ። ኖኅም የጥፋት ውኂ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የስድስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ። ኖኅም ስለ ጥፋት ውኂ ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወደ መርከብ ገባ። ከንጽሕ እንስሳ ንጽሕም ካልሆነው እንስሳ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚንቀሳቀስውም ሁሉ፤ እግዚአብሔር ኖኅን እንዳዘዘው ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መርከብ ውስጥ ገቡ። ከሰባት ቀንም በኍላ የጥፋት ውኂ በምድር ላይ ሆነ። በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ስባተኛው ዕለት በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማይም መስኮቶች ተከፈቱ ዝናቡም አርባ ቀንም አርባ ሌሊት በምድት ላይ ሆነ። በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋር ገቡ። እነርሱ አራዊትም ሂሉ በየወገናቸው፤ እንስሳትም ሁሉ በየወገናቸው በንድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾችም ሁሉ በየወገናቸው ወፎችም ሁሉ በየወገናቸው የሚበሩ ወፎችም ሁሉ ሥጋ ያላቸው ሕያዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መርከብ ውስጥ ገቡ። ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔርም በስተ ኋላው ዘጋበት። የጥፋትም ውኂ በምድር ላይ አርባ ቀን ነበረ ውኂውም በዛ መርከቢቱንም አነሣ ከምድርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች። ውኂውም አሸነፈ፤ በምድር ላይም እጅግ በዛ መርከቢቱም በውኂ ላይ ሄደች። ውኂውም በምድር ላይ እጅግ በጣም አሽነፈ ከሰማይም በታች ያሉ ታላላቆች ተራሮች ሁሉ ተሸፈኑ። ውኂው ወደ ላይ አሥራ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ ተራሮችም ተሸፈኑ። በምድር ላይ ሥጋ ያለው የሚንቀሳቃሹም ሁሉ ሰውም ሁሉ ጠፉ። በየብስ የነበረው በአፍንጫው የሕይወት ነፍስ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ሞተ። በምድር ላይ የነበውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ፤ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፤ እስከ ሰማይ ወፍ ድረስ ተደመሰሰ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ። ውኅውም መቶ አምሳ ቀን በምድር ላይ አሸነፈ።

ዘፍጥረት 7:1-24 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ብቻ ሆነህ ስላገኘሁህ፥ ከመላው ቤተሰብህ ጋር ወደ መርከቡ ግባ። ንጹሕ ከሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ሰባት ወንድ፥ ሰባት ሴት ከአንተ ጋር ወደ መርከቡ አስገባ፤ ንጹሕ ካልሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ግን፥ አንድ ወንድ አንድ ሴት አስገባ። ከያንዳንዱ ዐይነት ወፍ ወንድና ሴት ሰባት ወንድ ሰባት ሴት አስገባ፤ ይህንንም የምታደርገው እያንዳንዱ ዐይነት እንስሳና ወፍ በሕይወት እንዲኖርና በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፍ ነው። የፈጠርኩትን ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ዝናብ አዘንባለሁ።” ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ የኖኅ ዕድሜ 600 ዓመት ነበር። ኖኅ፥ ሚስቱ፥ ልጆቹና ሚስቶቻቸው ከጥፋት ውሃ ለማምለጥ ወደ መርከቡ ገቡ። ንጹሕ ከሆኑትና ካልሆኑት ከያንዳንዱ ዐይነት እንስሶች ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ ጥንድ ወንድና ሴት እየሆኑ፥ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘውም መሠረት ወደ ኖኅ ወደ መርከቡ ገቡ። ከሰባትም ቀን በኋላ የጥፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ። ኖኅ 600 ዓመት በሆነው ጊዜ፥ በሁለተኛው ወር በዐሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ውሃ ምንጮች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፤ በሰማይ ያሉት የውሃ መስኮቶች ሁሉ ተከፈቱ። ዝናብም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዘነበ። ዝናቡ መዝነብ በጀመረበት ቀን፥ ኖኅና ሚስቱ ከልጆቻቸው ከሴም፥ ከካም፥ ከያፌትና ከሦስቱም ልጆቻቸው ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገቡ። ከአራዊት፥ ከእንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና በሰማይ ከሚበርሩ ወፎች ከእያንዳንዱ ዐይነት አብረዋቸው ገቡ። በዚህ ዐይነት እስትንፋስ ካላቸው ፍጥረቶች ከእያንዳንዱ ዐይነት ሁለት ሁለት እየሆኑ ከኖኅ ጋር ወደ መርከቡ ገቡ፤ ፍጥረት ሁሉ ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ የገቡት እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ነው፤ ከዚህ ቀጥሎ እግዚአብሔር ከኖኅ በስተኋላ የመርከቡን በር ዘጋ። የጥፋት ውሃ አርባ ቀን ድረስ በመዝነብ እየበረታ ሄደ፤ የውሃውም ጥልቀት እየጨመረ ስለ ሄደ መርከቡን ከምድር በላይ ከፍ አደረገው፤ ውሃ በምድር ላይ እያደገና እየበረታ በሄደ መጠን መርከቡ በውሃው ላይ መንሳፈፍ ጀመረ። ውሃውም ከሰማይ በታች ያሉትን ታላላቅ ተራራዎችን እንኳ እስከሚሸፍን ድረስ ጥልቅ ሆነ። ውሃው ከተራሮች ጫፍ በላይ ሰባት ሜትር ያኽል ከፍ አለ። ወፎችና እንስሶች፥ አራዊት፥ ሰዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ሞቱ። በምድር ላይ ያሉት ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ ጠፉ። በምድር ላይ የሚኖር እስትንፋስ ያለው ነገር ሁሉ ሞተ። እግዚአብሔር በምድር ላይ ያለውን ሕያው ፍጥረት ሁሉ፥ ሰዎችንም፥ እንስሶችንም፥ ወፎችንም፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሳይቀሩ ሁሉንም አጠፋ። ከሞት የተረፉት ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ብቻ ነበሩ። ውሃው እስከ መቶ ኀምሳ ቀን አልጐደለም ነበር።

ዘፍጥረት 7:1-24 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ሆነህ አይቼሃለሁና፥ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ። ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት፤ ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ። የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ።” ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ። የጥፋት ውኃ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ የኖኅ ዕድሜ ስድስት መቶ ዓመት ነበረ። ኖኅ፥ ሚስቱ፥ ልጆቹና ሚስቶቻቸው ከጥፋት ውሃ ለማምለጥ ወደ መርከቡ ገቡ። ከንጹሕ እንስሳ ንጹሕም ካልሆነው እንስሳ፥ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሰውም ሁሉ፥ ጥንድ ተባዕትና እንስት እየሆኑ፥ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘውም መሠረት ወደ ኖኅ ወደ መርከቡ ገቡ። ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውኃ በምድር ላይ መጣ። ኖኅ ስድስት መቶ ዓመት በሆነው፥ በሁለተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ፥ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ጥልቅ መፍለቂያዎች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፥ የሰማያትም መስኮቶች ተከፈቱ፥ ዝናቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዘነበ። በዚያውም ቀን ኖኅ፥ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋር ወደ መርከብ ገቡ። ከእነርሱ ጋር፥ ከአራዊት፥ ከእንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና በሰማይ ከሚበርሩ ወፎች ከእያንዳንዱ ዓይነት አብረዋቸው ገቡ። በዚህ ዓይነት እስትንፋስ ካላቸው ፍጥረቶች ከእያንዳንዱ ዓይነት ሁለት ሁለት እየሆኑ ከኖኅ ጋር ወደ መርከቡ ገቡ፤ ፍጥረት ሁሉ ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ የገቡት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ገቡ፤ ጌታም በስተ ኋላው ዘጋበት። የጥፋትም ውኃ በምድር ላይ አርባ ቀን አላቋረጠም፥ ውኃውም በዛ፥ መርከቢቱንም አነሣ፥ ከምድርም በላይ ከፍ አለች። ውሃ በምድር ላይ እያደገና እየበረታ በሄደ መጠን መርከቡ በውሃው ላይ መንሳፈፍ ጀመረ። ውሃውም ከሰማይ በታች ያሉትን ታላላቅ ተራራዎችን እንኳ እስከሚሸፍን ድረስ ጥልቅ ሆነ። ውሃው ከተራሮች ጫፍ በላይ ሰባት ሜትር ያኽል ከፍ አለ። ወፎችና እንስሶች፥ አራዊት፥ ሰዎችም ሁሉ ሞቱ። በምድር ላይ ያሉት ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ ጠፉ። በምድር ላይ የሚኖር የሕይወት እስትንፋስ ያለው ሁሉ ሞተ። እግዚአብሔር በምድር ላይ ያለውን ሕያው ፍጥረት ሁሉ፥ ሰዎችንም፥ እንስሶችንም፥ ወፎችንም፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሳይቀሩ ሁሉንም አጠፋ። ከሞት የተረፉት ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ብቻ ነበሩ። ውሃውም እስከ መቶ ኀምሳ ቀን አልጐደለም ነበር።