ዘፍጥረት 6:9-21

ዘፍጥረት 6:9-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው፤ ኖኅ በዘመኑ ምንም በደል የማይሠራና የእግዚአብሔርን መንገድ የሚከተል ደግ ሰው ነበር፤ ኖኅም ሴም፥ ካምና ያፌት የሚባሉትን ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ። በዚያን ጊዜ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉዎች ነበሩ፤ ምድርም በዐመፅ ተሞልታ ነበር። እግዚአብሔር ዓለምን ተመለከተ፤ የተበላሸች እንደ ሆነችና በውስጧም ያሉት ሰዎች ሁሉ በክፋት እንደሚኖሩ አየ። እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “የሰውን ዘር ለማጥፋት ወስኛለሁ፤ ምድር በሰዎች የዐመፅ ሥራ ስለ ተሞላች ሰዎችን ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ፤ አንተ ግን ከጥሩ እንጨት መርከብ ሥራ፤ በውስጡም ብዙ ክፍሎች እንዲኖሩት አድርግ፤ መርከቡን ከውስጥና ከውጪ በቅጥራን ለቅልቀው። ርዝመቱን 133 ሜትር፥ የጐኑን ስፋት 22 ሜትር፥ የከፍታውን ቁመት 13 ሜትር አድርግ፤ ለመርከቡ ጣራ አብጅለት፤ ጣራውና ግድግዳው በሚጋጠሙበት ቦታ ላይ 44 ሳንቲ ሜትር ባዶ ቦታ ተውለት፤ መርከቡ ባለሦስት ፎቅ እንዲሆን አድርግ፤ በጐኑም በኩል በር አድርግለት፤ እነሆ፥ ከሰማይ በታች ሕይወት ያለውን ነገር ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት የጥፋት ውሃ አመጣለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ይጠፋል። ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፥ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ወደ መርከቡ ግቡ። “ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲጠበቁ ሥጋ ከለበሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ከየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት እየወሰድህ ወደ መርከቡ አስገባ፤ በሕይወት እንዲኖሩ ከየዐይነቱ ወፎች፥ ከየዐይነቱ እንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ከልዩ ልዩ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች በየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወደ አንተ ይምጡ። እንዲሁም ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዐይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።”

ዘፍጥረት 6:9-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የኖኅ ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ኖኅም በት​ው​ልዱ ጻድቅ፥ ፍጹ​ምም ሰው ነበረ፤ ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው። ኖኅም ሦስት ልጆ​ችን ሴምን፥ ካምን ያፌ​ት​ንም ወለደ። ምድ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተበ​ላ​ሸች፤ ምድ​ርም ግፍን ተመ​ላች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን እንደ ተበ​ላ​ሸች፥ ሥጋን የለ​በሱ ሁሉም በም​ድር ላይ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን እንደ አበ​ላሹ አየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “የሰው ሁሉ ጊዜው በፊቴ ደር​ሶ​አል፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ምድር በግፍ ተመ​ል​ታ​ለ​ችና፤ እኔም እነሆ፥ ከም​ድር ጋር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ። ባለ አራት መዓ​ዝን የዕ​ን​ጨት መር​ከ​ብን ለአ​ንተ ሥራ፤ በመ​ር​ከ​ቢ​ቱም ክፍ​ሎ​ችን አድ​ርግ፤ በው​ስ​ጥም፥ በው​ጭም በቅ​ጥ​ራን ለቅ​ል​ቃት። መር​ከ​ብ​ዋ​ንም እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ታ​ለህ፤ የመ​ር​ከ​ቢቱ ርዝ​መት ሦስት መቶ ክንድ፥ ወር​ድዋ አምሳ ክንድ፥ ከፍ​ታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን። ለመ​ር​ከ​ቢ​ቱም መስ​ኮ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ከቁ​መ​ቷም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨር​ሳት፤ የመ​ር​ከ​ቢ​ቱ​ንም በር በጎ​ንዋ አድ​ርግ፤ ታች​ኛ​ው​ንም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም፥ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም ደርብ ታደ​ር​ግ​ላ​ታ​ለህ። እኔም እነሆ፥ ከሰ​ማይ በታች የሕ​ይ​ወት ነፍስ ያለ​ውን ሥጋ ሁሉ ለማ​ጥ​ፋት በም​ድር ላይ የጥ​ፋት ውኃን አመ​ጣ​ለሁ፤ በም​ድር ያለው ሁሉ ይጠ​ፋል። ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ወደ መር​ከ​ብም አንተ ልጆ​ች​ህ​ንና ሚስ​ት​ህን፥ የል​ጆ​ች​ህ​ንም ሚስ​ቶች ይዘህ ትገ​ባ​ለህ። ከእ​ን​ስሳ ሁሉ፥ ከተ​ን​ቀ​ሳ​ቃሽ አራ​ዊ​ትም ሁሉ፥ ሥጋ ካለው ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ትመ​ግ​ባ​ቸው ዘንድ ከሁ​ሉም ሁለት ሁለት ወደ መር​ከብ ታገ​ባ​ለህ፤ ተባ​ትና እን​ስት ይሁን። ከወ​ፎች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ከእ​ን​ስ​ሳም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በም​ድር ላይ ከሚ​ሳቡ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከአ​ንተ ጋር ይመ​ገቡ ዘንድ ከሁ​ሉም ሁለት ሁለት ወን​ድና ሴት እየ​ሆኑ ወደ አንተ ይግቡ። ከሚ​በ​ላ​ውም የመ​ብል ዓይ​ነት ሁሉ ለአ​ንተ ውሰድ፤ ወደ አንተ ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ፤ እር​ሱም ለአ​ንተ፥ ለእ​ነ​ር​ሱም መብል ይሆ​ናል።”

ዘፍጥረት 6:9-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው። ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት ሰው ነበር፤ አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋራ አደረገ። ኖኅም ሴም፣ ካምና ያፌት የሚባሉ ሦስት ወንዶች ልጆች ነበሩት። ምድር በእግዚአብሔር ፊት በክፉ ሥራ ረከሰች፤ በዐመፅም ተሞላች። እግዚአብሔር ምድር ምን ያህል በክፉ ሥራ እንደ ረከሰች አየ። እነሆ፤ ሰው ሁሉ አካሄዱን አበላሽቶ ነበርና ስለዚህ እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “ሰውን ሁሉ ላጠፋ ነው፤ ምድር በሰው ዐመፅ ስለ ተሞላች በርግጥ ሰውንም ምድርንም አጠፋለሁ። አንተ ግን በጎፈር ዕንጨት መርከብ ሥራ፤ ለመርከቧም ክፍሎች አብጅላት፤ ውስጧንና ውጭዋን በቅጥራን ለብጠው። እንዲህ አድርገህ ሥራት፦ ርዝመቷ መቶ አርባ ሜትር፣ ወርዷ ሃያ ሦስት ሜትር፣ ከፍታዋ ዐሥራ ሦስት ነጥብ ዐምስት ሜትር ይሁን። ለመርከቧ ጣራ አብጅላት፣ ጣራና ግድግዳው በሚጋጠምበት ቦታ ግማሽ ሜትር ክፍተት ተው፤ ከጐኗ በር አውጣላት፤ ባለሦስት ፎቅ አድርገህ ሥራት። እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸውን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ለማጥፋት እነሆ፤ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል። ከአንተ ጋራ ግን ቃል ኪዳን እመሠርታለሁ። አንተና ወንዶች ልጆችህ፣ ሚስትህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋራ ወደ መርከቧ ትገባላችሁ። ከአንተ ጋራ በሕይወት እንዲቈዩ ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ተባዕትና እንስት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ። ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ። ለአንተና ለእነርሱ የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ አከማች።”

ዘፍጥረት 6:9-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የኖኅ ትውልድ እንዲህ ነው። ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ስው ነበረ ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረግ። ኖኅም ሦስት ልጆችን ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ። ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ተበላሸ ምድርም ግፍን ተሞላች። እግዚአብሔርም ምድርን አየ፤ እነሆም ተበላሸች ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበርና። እግዚእብሔርም ኖኅን አለው፤ የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችን እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ። ከጎፈር እንጨት መርከብን ለአንተ ሥራ በመርከቢቱም ጉርጆችን አድርግ በውስጥን በውጭም በቅጥራን ለቅልቃት። እርስዋንም እንዲህ ታደርጋታለህ የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፤ ወርድዋ አምሳ ክንድ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን። ለመርከቢቱ መስኮትን ታድርጋለህ ከቁመትዋም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨርሳት የመርከቢቱንም በር በጎንዋ አድርግ ታችኛውንም ሁለተኛውንም ሦስተኛውንም ደርብ ታደርግላታለህ። እኔም እነሆ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኂን አመጣለሁ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል። ቃል ኪዳኔም ከአንተ ጋር አቆማለሁ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ። ከአንተ ጋር በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሥጋ ካለው ከሕያው ሁሉ ሁለት ሁለር እያደረግህ ወደ መርከብ ታገባለህ ተባትና እንስት ይሁን። ከወፍ እንደ ወገኑ ከእንስሳም እንደ ወገኑ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንድ ወገኑ በሕይውር ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆን ወደ አንተ ይግቡ። ከሚበላውም መብል ሁሉ ለአንተ ውሰድ፤ ወደ አንተም ትሰበስባለህ እርሱም ለአንተም ለእነርሱም መብል ይሆናል።

ዘፍጥረት 6:9-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው፤ ኖኅ በዘመኑ ምንም በደል የማይሠራና የእግዚአብሔርን መንገድ የሚከተል ደግ ሰው ነበር፤ ኖኅም ሴም፥ ካምና ያፌት የሚባሉትን ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ። በዚያን ጊዜ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉዎች ነበሩ፤ ምድርም በዐመፅ ተሞልታ ነበር። እግዚአብሔር ዓለምን ተመለከተ፤ የተበላሸች እንደ ሆነችና በውስጧም ያሉት ሰዎች ሁሉ በክፋት እንደሚኖሩ አየ። እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “የሰውን ዘር ለማጥፋት ወስኛለሁ፤ ምድር በሰዎች የዐመፅ ሥራ ስለ ተሞላች ሰዎችን ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ፤ አንተ ግን ከጥሩ እንጨት መርከብ ሥራ፤ በውስጡም ብዙ ክፍሎች እንዲኖሩት አድርግ፤ መርከቡን ከውስጥና ከውጪ በቅጥራን ለቅልቀው። ርዝመቱን 133 ሜትር፥ የጐኑን ስፋት 22 ሜትር፥ የከፍታውን ቁመት 13 ሜትር አድርግ፤ ለመርከቡ ጣራ አብጅለት፤ ጣራውና ግድግዳው በሚጋጠሙበት ቦታ ላይ 44 ሳንቲ ሜትር ባዶ ቦታ ተውለት፤ መርከቡ ባለሦስት ፎቅ እንዲሆን አድርግ፤ በጐኑም በኩል በር አድርግለት፤ እነሆ፥ ከሰማይ በታች ሕይወት ያለውን ነገር ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት የጥፋት ውሃ አመጣለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ይጠፋል። ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፥ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ወደ መርከቡ ግቡ። “ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲጠበቁ ሥጋ ከለበሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ከየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት እየወሰድህ ወደ መርከቡ አስገባ፤ በሕይወት እንዲኖሩ ከየዐይነቱ ወፎች፥ ከየዐይነቱ እንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ከልዩ ልዩ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች በየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወደ አንተ ይምጡ። እንዲሁም ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዐይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።”

ዘፍጥረት 6:9-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የኖኅ ትውልድ እንደሚከተለው ነው። ኖኅም ጻድቅ፥ በትውልዱም በደል ያልተገኘበት ሰው ነበረ፥ ኖኅም እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው። ሴም፥ ካምና ያፌት የሚባሉትን ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ። በዚያን ጊዜ ምድር በእግዚአብሔር ፊት የተበላሸች ነበረች፥ ምድርም ግፍን ተሞላች። እግዚአብሔርም ምድርን አየ፥ እነሆም፥ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በምድር ላይ መንገዳቸውን አበላሽተው ነበርና፥ ምድር የተበላሸች ነበረች። እግዚእብሔርም ኖኅን አለው፦ “የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል፥ ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችና፥ እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ። ለአንተ ከጎፈር እንጨት መርከብን ሥራ፥ በመርከቢቱም ክፍሎችን አድርግ፥ በውስጥም፥ በውጭም በቅጥራን ለቅልቃት። የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፥ ወርድዋ አምሳ ክንድ፥ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ አድርግ፤ ለመርከቢቱም ጣራን አብጅለት፤ ከቁመትዋም አርባ አራት ሳንቲ ሜትር ትተህ ጨርሳት፥ መርከቡ ባለ ሦስት ፎቅ እንዲሆን አድርግ፤ በጎኑም በኩል በር አድርግለት። እነሆ፥ እኔ ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት፥ በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፥ በምድር ያለ ሁሉ ይጠፋል። ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፥ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ይዘህ ወደ መርከቡ ትገባለህ። ከአንተ ጋር በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሥጋ ካለው ከሕያው ሁሉ ሁለት ሁለት እያደረግህ ወደ መርከብ ታስገባለህ፥ ተባዕትና እንስት ይሁኑ፤ ከወፍ እንደ ወገኑ፥ ከእንስሳም እንደ ወገኑ፥ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንደ ወገኑ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይግቡ። እንዲሁም ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።”