ዘፍጥረት 6:1-8

ዘፍጥረት 6:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሰዎች በም​ድር ላይ መብ​ዛት በጀ​መሩ ጊዜ መልከ መል​ካ​ሞች ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ላ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “መን​ፈሴ በሰው ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ሥጋ ናቸ​ውና፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም መቶ ሃያ ዓመት ይሆ​ናል” አለ። በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ረዓ​ይት በም​ድር ላይ ነበሩ። ከዚ​ያም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆ​ችን ወለ​ዱ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በዱሮ ዘመን ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ኀያ​ላን ሰዎች ሆኑ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ዎች ክፉ ሥራ በም​ድር ላይ እን​ደ​በዛ፥ የል​ባ​ቸው ዐሳብ ምኞ​ትም ሁል ጊዜ ፈጽሞ ክፉ እን​ደ​ሆነ አየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰውን በም​ድር ላይ በመ​ፍ​ጠሩ ተጸ​ጸተ፤ በል​ቡም አዘነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን ሰው ከም​ድር ላይ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከሰው እስከ እን​ስ​ሳና አራ​ዊት፥ እስከ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠ​ር​ኋ​ቸው ተጸ​ጽ​ቻ​ለ​ሁና” አለ። ኖኅ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን አገኘ።

ዘፍጥረት 6:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሰዎች በምድር ላይ እየበዙ ሲሄዱ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው። የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ውብ ሆነው አዩአቸው፤ ከመካከላቸውም የመረጧቸውን አገቡ። እግዚአብሔርም፣ “ሰው ሟች ስለ ሆነ መንፈሴ እያዘነ ከርሱ ጋራ ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜው 120 ዓመት ይሆናል” አለ። የእግዚአብሔርም ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ተገናኝተው ልጆች በወለዱ ጊዜም ሆነ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንቱ ዘመን በጀግንነታቸው ከፍ ያለ ዝና ያተረፉ ናቸው። እግዚአብሔር አምላክ የሰው ዐመፅ በምድር ላይ የበዛና የልቡም ሐሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ። እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ ልቡም እጅግ ዐዘነ። ስለዚህም እግዚአብሔር፣ “የፈጠርሁትን የሰው ዘር ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት እስከ ሰማይ ወፎች አጠፋለሁ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ። ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አገኘ።

ዘፍጥረት 6:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እንዲህም ሆነ ሰዎች በምድር ላይ መብዛት በጀመሩ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ። እግዚአብሔርም፤ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፤ እርሱ ሥጋ ነውና፤ ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ አለ። በእነዚያ ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኂያላን ሆኑ። እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፤ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንድ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ በልቡም አዘነ። እግዚአብሔርም፤ የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ስለ ፈጠርኍቸው ተጸጽቼእለሁና አለ። ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ።

ዘፍጥረት 6:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የሰው ዘር በምድር ላይ እየበዛ በሄደ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱ፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ልጆች የእነዚህን የሰውን ሴቶች ልጆች ውበት ተመለከቱ፤ ከመካከላቸውም የሚወዱአቸውን እየመረጡ ወሰዱ። እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ። በዚያን ዘመንና ከዚያም በኋላ ከሰዎች ሴቶች ልጆችና ከእግዚአብሔር ልጆች ተዳቅለው የተወለዱ “ኔፊሊም” የሚባሉ ግዙፎች ሰዎች ነበሩ። እነርሱ በጥንት ዘመን በጀግንነታቸው የታወቁ ዝነኞች ሰዎች ነበሩ። እግዚአብሔር በምድር ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል ዐመፀኞች እንደ ሆኑና ሐሳባቸውም ዘወትር ክፋት ብቻ እንደ ሆነ ተመለከተ፤ ስለዚህ ሰዎችን በመፍጠሩና በምድር ላይ እንዲኖሩ በማድረጉ አዘነ፤ እጅግም ተጸጸተ። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር “እነርሱን በመፍጠሬ አዝኛለሁ፤ ስለዚህ እነዚህን የፈጠርኳቸውን ሰዎች፥ እንስሶችን፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችንና ወፎችንም ጭምር ከምድር ላይ አጠፋለሁ” አለ። ይሁን እንጂ ኖኅ የተባለው ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አግኝቶ ነበር።

ዘፍጥረት 6:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የሰው ዘር በምድር ላይ እየበዛ በሄደ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱ፥ የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፥ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ። ጌታም፦ “መንፈሴ በሰው ላይ ለዘለዓለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና፥ እድሜውም መቶ ሃያ ዓመት ይሆናል” አለ። በዚያን ዘመን ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፥ እና ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፥ እነርሱም በዱሮ ዘመን፥ ስማቸው የታወቀ፥ ኃያላን ሆኑ። ጌታም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ። ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩም ጌታ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ። በዚህ ምክንያት ጌታ፥ “ከምድር ላይ የፈጠርኩትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፥ ሰው እና አራዊትን፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችን እና የሰማይ አእዋፍንም፥ ስለ ፈጠርኳቸው ተጸጽቼአለሁና” አለ። ይሁን እንጂ ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ።