ዘፍጥረት 49:8-10 - Compare All Versions
ዘፍጥረት 49:8-10 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
“ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል፤ እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው፤ የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ። ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመሰማሪያህ ወጣህ፤ እንደ አንበሳ ተኛህ፤ አንቀላፋህም፤ እንደ አንበሳም ደቦል የሚቀሰቅስህ የለም። መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ዘፍጥረት 49:8-10 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“ይሁዳ፣ ወንድሞችህ ይወድሱሃል፤ እጅህም የጠላቶችህን ዐንገት ዐንቆ ይይዛል፤ የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይሰግዱልሃል። አንተ የአንበሳ ደቦል ይሁዳ፤ ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣ እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ በምድርም ላይ ይተኛል፤ እንደ እንስት አንበሳም ያደባል፤ ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል? በትረ መንግሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤ የገዢነት ምርኵዝም ከእግሮቹ መካከል። ገዥነት የሚገባው እስኪመጣ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙታል።
ዘፍጥረት 49:8-10 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ይሁዳ ወንድሞችህ አንተን ያመስግኑሃል እጅህ በጠላቶችህ ደንድስ ላይ ነው የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ። ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ ከአደንህ ወጣሁ እንደ አንበሳ አሸመቀ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፤ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል? በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።
ዘፍጥረት 49:8-10 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
“ይሁዳ፥ ወንድሞችህ ያመሰግኑሃል፤ እጅህ በጠላቶችህ አንገት ላይ ይበረታል፤ ወንድሞችህ በፊትህ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው እጅ ይነሡሃል። ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፤ ልጄ መብል የሚሆነውን አድኖ፥ ወደ ዋሻው ይመለሳል፤ እንደ አንበሳ ተዝናንቶ ይተኛል፤ ሊቀሰቅሰው የሚደፍር ማነው? ‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ዘፍጥረት 49:8-10 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል፥ እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው፥ የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ። ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፥ ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ፥ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፥ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል? በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ፥ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።