ዘፍጥረት 49:22-23
ዘፍጥረት 49:22-23 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“ዮሴፍ የሚያድግ ልጅ ነው፤ ለእኔ በጣም የተወደደ የሚቀናልኝና የሚያድግልኝ ልጅ ነው፤ ወደ እኔ የሚመለስም ጐልማሳ ነው። በምክራቸው የሰደቡት ጌቶች ሆኑበት፤ ቀስተኞችም ወጉት፤
ዘፍጥረት 49:22-23 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣ በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው። ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ። ቀስተኞች በጭካኔ አጠቁት፤ በጥላቻም ነደፉት።
ዘፍጥረት 49:22-23 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ። ቀስተኞች አስቸገሩት ነደፋትም ተቃወሙትም ነገር ግም ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ፤