ዘፍጥረት 43:13-14
ዘፍጥረት 43:13-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወንድማችሁንም ከእናንተ ጋር ውሰዱ፤ ተነሥታችሁም ወደዚያ ሰው ውረዱ። አምላኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገስን ይስጣችሁ፤ ያን ወንድማችሁንና ብንያምንም ይመልስላችሁ፤ እኔም ልጆችን እንዳጣሁ አጣሁ።”
ዘፍጥረት 43:13-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወንድማችሁንም ይዛችሁ ወደ ሰውየው በቶሎ ሂዱ። ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ይዛችሁ ለመመለስ እንድትችሉ ሁሉን ቻይ አምላክ በምሕረቱ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እንግዲህ ልጆቼንም ባጣ ምን አደርጋለሁ፤ ያመጣውን እቀበላለሁ።”
ዘፍጥረት 43:13-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ወንድማችሁንም ውሰዱ ተነሥታችሁም ወደዚያ ሰው ተመለሱ። ሁሉን የሚችል አምላክም ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ከእናንተ ጋር ይሰድድ ዘንድ በዚያ ሰው ፊት ምሕረትን ይስጣችሁ እኔም ልጆቼን እንዳጣሁአጣሁ።