ዘፍጥረት 42:21 - Compare All Versions

ዘፍጥረት 42:21 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ተባ​ባሉ፥ “በእ​ው​ነት ወን​ድ​ማ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ እኛን በመ​ማ​ጠን ነፍሱ ስት​ጨ​ነቅ አይ​ተን አል​ሰ​ማ​ነ​ው​ምና፤ ስለ​ዚህ ይህ መከራ መጣ​ብን።”

ዘፍጥረት 42:21 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እርስ በርሳቸውም፣ “ይኸው በወንድማችን ላይ ባደረስነው በደል ምክንያት ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማፀነን፣ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ።

ዘፍጥረት 42:21 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እንዲህም አደረጉ። እነርሱ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ በእውነት ወንድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።

ዘፍጥረት 42:21 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”

ዘፍጥረት 42:21 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እርስ በርሳቸውም፥ “ይኸው በወንድማችን ላይ ባደረስነው በደል ምክንያት ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማጠነን፥ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ።