ዘፍጥረት 39:20-21
ዘፍጥረት 39:20-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዮሴፍንም ወሰደው፤ የንጉሡ እስረኞች ወደሚታሰሩበት ስፍራ ወደ ግዞት ቤትም አገባው፤ ከዚያም በግዞት ነበረ። እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕረትንም አበዛለት፤ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው።
ዘፍጥረት 39:20-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ጌታውም ዮሴፍን ወስዶ፣ የንጉሥ እስረኞች ወደ ተጋዙበት እስር ቤት አስገባው። ይሁን እንጂ ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋራ ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት፤ በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው።
ዘፍጥረት 39:20-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የዮሴፍም ጌታ ወሰደው የንጉሠ እስረኞችም ወደሚታሰሩበት ስፍራ ወደ ግዞት ቤት አገባው፤ ከዚያም በግዞት ነበረ። እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ ምሕረትንም አበዛለት