ዘፍጥረት 39:11-12
ዘፍጥረት 39:11-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በአንዲትም ቀን እንዲህ ሆነ፤ በዚያ ቀን ሥራውን እንዲሠራ ዮሴፍ ወደ ቤቱ ገባ፤ በቤትም ውስጥ ከቤተ ሰዎች ማንም አልነበረም። ልብሱን ይዛ፥ “ና ከእኔ ጋር ተኛ” አለችው፤ እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ።
ዘፍጥረት 39:11-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አንድ ቀን ዮሴፍ የዕለት ተግባሩን ለማከናወን ወደ ቤት ገባ፤ ከቤቱ አገልጋዮችም አንድም ሰው በቤት ውስጥ አልነበረም። እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ “በል ዐብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ ከቤት ወጣ።
ዘፍጥረት 39:11-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንዲህም ሆነ በዚያን ጊዜ ሥራውን እንዲሠራ ወደ ቤቱ ገባ በቤትም ውስጥ ከቤት ሰዎች ማንም አልነበረም። ከእኔ ጋር ተኛ ስትል ልብሱን ተጠማጥማ ያዘች እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ።