ዘፍጥረት 38:19-23
ዘፍጥረት 38:19-23 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እርስዋም ተነሥታ ሄደች፤ መጐናጸፊያዋንም አውልቃ የመበለትነቷን ልብስ ለበሰች። ይሁዳም መያዣውን ከሴቲቱ እጅ ይቀበል ዘንድ በበግ ጠባቂው በዓዶሎማዊው እጅ የፍየሉን ጠቦት ላከላት፤ እርስዋንም አላገኛትም። እርሱም የሀገሩን ሰዎች፥ “በኤናይም በመንገድ ዳር ተቀምጣ የነበረች ዘማ ወዴት ናት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፥ “በዚህ ዘማ አልነበረችም” አሉት። ወደ ይሁዳም ተመልሶ እንዲህ አለው፥ “አላገኘኋትም፤ የሀገሩ ሰዎች ደግሞ፦ ከዚህ ዘማ የለችም” አሉኝ። ይሁዳም፥ “እኛ መዘበቻ እንዳንሆን ትውሰደው፤ እነሆ፥ የፍየሉን ጠቦት ላክሁላት፤ አንተም አላገኘሃትም” አለ።
ዘፍጥረት 38:19-23 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፣ ሻሿን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች። ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶላማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፣ መልእክተኛው ግን ሴትዮዋን ሊያገኛት አልቻለም። “በኤናይም ከተማ መግቢያ ከመንገዱ ዳር የነበረች ያቺ ዝሙት ዐዳሪ የት ደረሰች?” ሲል ጠየቃቸው። ሰዎቹም፣ “በዚህ አካባቢ ኧረ ምንም ዝሙት ዐዳሪ ታይታ አትታወቅም” አሉት። መልእክተኛውም ወደ ይሁዳ ተመልሶ፣ “ሴቲቱን ላገኛት አልቻልሁም፤ ነዋሪዎቹም ‘በዚህ አካባቢ እንደዚህች ያለች ዝሙት ዐዳሪ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው። ይሁዳም፣ “እንግዲህ መያዣውን እንደ ያዘች ትቅር፣ አለዚያ መሣቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፤ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ።
ዘፍጥረት 38:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኤስውም ተነሥታ ሄደች መጎናጸፊያዋንም አውልቃ የመበለትነትዋን ልብስ ለበስች። ይሁዳም መያዣውን ከሴቲቱ እጅ ይቀበል ዘንድ በወዳጁ በዓዶሎማዊው እጅ የፍየሉን ጠቦት ላከላት እርስዋንም፥ አላገኛትም። እርሱም የአገሩን ሰዎች፦ በኤናይም በመንገድ ዳር ተቀምጣ የነበረች ጋለሞታ ወዴት ናት? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፦ በዚህ ጋለሞታ አልነበረችም አሉት። ወደ ይሁዳም ተመልሶ እንዲህ አለው፦ አላገኘኍትም የአገሩም ሰዎች ደግሞ፦ ከዚህ ጋለሞታ አልነበረችም አሉኝ። ይሁዳም፦ እኛ መዘበቻ እንዳንሆን ትውሰደው እነሆ የፍየሉን ጠቦት ሰደድሁላት አንተም አላገኘሃትም አለ።
ዘፍጥረት 38:19-23 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚያ በኋላ ሻሽዋን ከፊቷ ላይ አንሥታ የመበለትነት ልብሷን እንደገና ለበሰች። ይሁዳ በመያዥያ መልክ የሰጣትን ነገሮች ለማስመለስ የፍየል ጠቦት በዐዱላማዊው ሰው እጅ ወደ ሴትዮዋ ላከ፤ ሰውየው ግን ሊያገኛት አልቻለም። ሰውየውም እዚያ የሚኖሩትን ሰዎች “በዔናይም ደጅ በመንገድ ዳር የነበረችው አመንዝራ ሴት ወዴት ሄደች?” ብሎ ጠየቀ። ሰዎቹም “በዚህ አካባቢ እንደዚህ ያለች አመንዝራ ሴት የለችም” አሉት። ስለዚህ ሰውየው ወደ ይሁዳ ተመልሶ ሄደና “ላገኛት አልቻልኩም፤ በዚያ የሚኖሩትም ሰዎች ‘እንደዚህ ያለች አመንዝራ ሴት እዚህ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው። ይሁዳም “እንግዲህ ጠቦቱን ልኬላት ነበር፤ ነገር ግን ልታገኛት አልቻልክም፤ ስለዚህ ሰዎች መሳቂያ እንዳያደርጉን የወሰደችውን መያዣ እዚያው ታስቀረው” አለ።
ዘፍጥረት 38:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፥ ሻሽዋን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች። ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶሎማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፥ መልእክተኛው ግን ሴትዮዋን ሊያገኛት አልቻለም። “በኤናይም ከተማ መግቢያ ከመንገዱ ዳር የነበረች ያቺ ዝሙት ዐዳሪ የት ደረሰች?” ሲል ጠየቃቸው። ሰዎቹም፥ “በዚህ አካባቢ ኧረ ምንም ዝሙት ዐዳሪ ታይታ አትታወቅም” አሉት። መልእክተኛውም ወደ ይሁዳ ተመልሶ፥ “ሴቲቱን ላገኛት አልቻልኩም፤ ነዋሪዎቹም ‘በዚህ አካባቢ እንደዚህች ያለች ዝሙት ዐዳሪ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው። ይሁዳም፥ “እንግዲህ መያዣውን እንደ ያዘች ትቅር፤ አለዚያ መሣቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፤ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ።