ዘፍጥረት 32:13-21

ዘፍጥረት 32:13-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በዚ​ያ​ችም ሌሊት በዚ​ያው አደረ። ለወ​ን​ድሙ ለዔ​ሳ​ውም የሚ​ወ​ስ​ደ​ውን እጅ መንሻ አወጣ፤ ሁለት መቶ እን​ስት ፍየ​ሎ​ች​ንና ሃያ የፍ​የል አው​ራ​ዎ​ችን፥ ሁለት መቶ እን​ስት በጎ​ች​ንና ሃያ የበግ አው​ራ​ዎ​ችን፥ ሃምሳ የሚ​ያ​ጠቡ ግመ​ሎ​ችን ከግ​ል​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ጋር፥ አርባ ላም፥ ዐሥር በሬ፥ ሃያ እን​ስት አህያ፥ ዐሥ​ርም የአ​ህያ ውር​ን​ጫ​ዎች፤ መን​ጎ​ቹ​ንም ለየ​ብቻ ከፍሎ ለብ​ላ​ቴ​ኖቹ ሰጣ​ቸው፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም፥ “በፊቴ እለፉ፤ መን​ጋ​ውን ከመ​ን​ጋው አርቁ” አላ​ቸው። የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “ወን​ድሜ ዔሳው ያገ​ኘህ እንደ ሆነ፦ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴ​ትስ ትሄ​ዳ​ለሀ? በፊ​ትህ ያለው ይህስ መንጋ የማን ነው?’ ብሎ የጠ​የ​ቀ​ህም እን​ደ​ሆነ፥ በዚያ ጊዜ አንተ፦ ‘ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው እጅ መንሻ የላ​ከው የአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የያ​ዕ​ቆብ ነው፤ እር​ሱም ደግሞ እነሆ ከኋ​ላ​ችን ተከ​ት​ሎ​ናል’ በለው።” እን​ዲ​ሁም ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንና ሦስ​ተ​ኛ​ውን፥ በፊቱ የሚ​ሄ​ዱ​ት​ንና መን​ጋ​ውን የሚ​ነ​ዱ​ትን ሁሉ እን​ዲሁ ብሎ አዘዘ፦“ ወን​ድሜ ዔሳ​ውን ባገ​ኛ​ች​ሁት ጊዜ ይህ​ንኑ ነገር ንገ​ሩት፤ እን​ዲ​ህም በሉ፦ እነሆ አገ​ል​ጋ​ይህ ያዕ​ቆብ ከኋ​ላ​ችን ነው። በፊቴ በሚ​ሄ​ደው እጅ መንሻ እታ​ረ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ምና​ል​ባት ይራ​ራ​ል​ኛል፤ ፊቱ​ንም አያ​ለሁ ብሎ​አ​ልና።” እጅ መን​ሻ​ውን ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ላከ፤ እርሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሰ​ፈር አደረ።

ዘፍጥረት 32:13-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚያችም ሌሊት ያዕቆብ እዚያው ዐደረ፤ ካለው ሀብት ለወንድሙ ለዔሳው እጅ መንሻ እነዚህን መረጠ፦ ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችና ሃያ አውራ ፍየሎች፣ ሁለት መቶ እንስት በጎችና ሃያ አውራ በጎች፣ ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፣ አርባ ላሞችና ዐሥር ኰርማዎች፣ ሃያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባዕት አህዮች። እነዚህንም በየመንጋው ለይቶ፣ የሚነዷቸውን ጠባቂዎች መደበላቸው፤ ጠባቂዎቹንም፣ “እናንተ ቀድማችሁኝ ሂዱ፣ መንጋዎቹንም አራርቃችሁ ንዷቸው” አላቸው። ቀድሞ የሚሄደውንም እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ዔሳው አግኝቶህ፣ ‘የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፣ ‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ከበስተኋላችን እየመጣ ነው’ ብለህ ንገረው።” እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎችን የሚነዱትን ሌሎቹንም ሁሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “ዔሳውን ስታገኙት ይህንኑ ትነግሩታላችሁ፤ በተለይም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ ማለትን አትዘንጉ።” ይህንም ያዘዘው፣ “ዔሳው ከእኔ ጋራ ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል” ብሎ ስላሰበ ነበር። ስለዚህ የያዕቆብ እጅ መንሻ ከርሱ አስቀድሞ ተላከ፤ እርሱ ራሱ ግን እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።

ዘፍጥረት 32:13-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በዚይችም ሌሊት ከዚያው አደረ። ከያዘውም ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳ እጅ መንሻን አወጣ፤ ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችንና ሀያ የፍየል አውራዎችም ሁለት መቶ እንስት በጎችንና ሀያ የበግ አውራዎችን ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎችም ከግልገሎቻቸው ጋር አርባ ላም አሥር በሬ ሀያ እንስት አህያ አሥርም የእህያ ግልገሎችን። መንጎቹን፥ በየወገኑ ከፍሎ በባሪያዎቹ እጅ አደረጋቸ ባሪያዎቹን፦ በፊቴ እለፉ መንጋውንና መንጋውንም አራርቁት አለ። የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደሆነ፦ አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? በፊትህ ያለው ይህስ የማን ነው? ብሎ የጠየቀህም እንደ ሆነ፥ በዚያን ጊዜ አንተ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደደው የባሪያህ የያዕቆብ ነው እርሱም ደግሞ እነሆ ከኍላችን ነው በለው። እንዲሁም ሁለተኛውንና ሦስተኛውን ከመንጎችም በኍላ የሚሄዱትን ሁሉ እንዱሁ ብሎ አዘዘ፦ ዔሳውን ባገኛችሁት ጊዜ ይህንኑ ነገር ንገሩት እንዲህም በሉት፦ እነሆ ባሪያህ ያዕቆብ ከኍላችን ነው። በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፤ ከዚያም በኍላ ምናልባት ይራራልኛል ፊቱንም አያለሁ ብሎአልና። እጅ መንሻው ከእርሱ ቀድሞ አለፈ እርሱ ግን በዚያች ሌሊት በሰፈር አደረ።

ዘፍጥረት 32:13-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እዚያም ዐደረ፤ በማግስቱም ካለው ነገር ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን ነገር መርጦ አዘጋጀ፤ በዚህ ዐይነት ሁለት መቶ እንስት ፍየሎች፥ ኻያ ተባዕት ፍየሎች፥ ሁለት መቶ እንስት በጎች፥ ኻያ ተባዕት በጎች፤ ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፥ አርባ ላሞች፥ ዐሥር ኰርማዎች፥ ኻያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባዕት አህዮች መረጠ፤ እነዚህንም በየመንጋው ከፈለና ለእያንዳንዳቸው እረኞች መደበላቸው፤ እረኞቹንም “ከእኔ ቀድማችሁ ሂዱ፤ በየመንጋው መካከል ርቀት እንዲኖር አድርጋችሁ፥ በመከታተል ሂዱ” አላቸው። የመጀመሪያዎቹንም እረኞች እንዲህ በማለት አዘዛቸው፤ “ወንድሜ ዔሳው በመንገድ አግኝቶ ‘የማን ሰዎች ናችሁ? ወዴትስ ትሄዳላችሁ? እነዚህ የምትነዱአቸው ከብቶች የማን ናቸው?’ ብሎ የጠየቃችሁ እንደ ሆነ፥ ‘እነዚህ ከብቶች የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ እርሱ እነዚህን የላከው ለጌታዬ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን ነው፤ እነሆ ያዕቆብ ከኋላችን ነው’ ብላችሁ ንገሩት።” ለሁለተኛውም ለሦስተኛውም ክፍል እረኞችና ለቀሩትም የመንጋ ጠባቂዎች “እናንተም ዔሳውን ስታገኙት እንደዚሁ ንገሩት፤ ‘በተለይም አገልጋይህ ያዕቆብ ከበስተኋላ እየመጣ ነው’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። ይህንንም ያለበት ምክንያት “እኔ ከመድረሴ በፊት በሚደርስለት ስጦታ ቊጣውን አበርድ ይሆናል፤ በኋላም በማገኘው ጊዜ በደስታ ይቀበለኛል” በሚል ሐሳብ ነው። በዚህ ዐይነት ስጦታውን አስቀድሞ ከላከ በኋላ፥ እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።

ዘፍጥረት 32:13-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በዚያችም ሌሊት ከዚያው ሰፈረ። ከያዘውም ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን አወጣ፥ ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችንና ሀያ የፍየል አውራዎችን፥ ሁለት መቶ እንስት በጎችንና ሀያ የበግ አውራዎችን፥ ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎችን ከግልገሎቻቸው ጋር፥ አርባ ላም፥ ዐሥር በሬ፥ ሀያ እንስት አህያ፥ ዐሥርም እህዮችን፤ እነዚህንም መንጎቹ በየወገኑ ከፍሎ በአገልጋዮቹ እጅ አደረጋቸው፥ አገልጋዮቹንም፦ “ከእኔ ቀድማችሁ ሂዱ፥ በመንጋው እና መንጋው መካከልም እርቀት አኑሩ” አለ። የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደሆነ፥ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? በፊትህ ያለው ይህስ የማን ነው?’ ብሎ የጠየቀህም እንደሆነ፥ በዚያን ጊዜ አንተ፦ ‘ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የላከው የባርያህ የያዕቆብ ነው፥ እርሱም ደግሞ እነሆ ከኋላችን ነው’ በለው።” እንዲሁም ሁለተኛውንና ሦስተኛውን ከመንጎችም በኋላ የሚሄዱትን ሁሉ እንዱሁ ብሎ አዘዘ፦ “ዔሳውን ባገኛችሁት ጊዜ ይህንኑ ነገር ንገሩት። ‘እንዲሁም ባርያህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው’ እንድትሉት። እሱ ‘በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፥ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይቀበለኛል ፊቱንም አያለሁ’ ብሎ አስቧል።” ስለዚህ እጅ መንሻው ከእርሱ ቀድሞ አለፈ፥ እርሱ ግን በዚያች ሌሊት እዚያው በሰፈሩበት አደረ።