ዘፍጥረት 27:39-40
ዘፍጥረት 27:39-40 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ይስሐቅም እንዲህ አለው፤ “በረከት ከሞላበት ለምለም ምድር ርቀህ ትኖራለህ፤ የሰማይ ጠልም አታገኝም፤ በሰይፍህ ኀይል ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ፤ በተቃወምከው ጊዜ ግን ከእርሱ ጭቈና ትላቀቃለህ።”
ዘፍጥረት 27:39-40 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አባቱ ይስሐቅም መለሰ፤ አለውም፥ “እነሆ መኖሪያህ ከላይ ከሰማይ ጠል፥ ከምድርም ስብ ይሁን፤ በሰይፍህም ትኖራለህ፤ ለወንድምህም ትገዛለህ፤ ነገር ግን ቀንበሩን ከአንገትህ ልትጥል ብትወድድ ከእርሱ ጋር ተስማማ።”
ዘፍጥረት 27:39-40 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አባቱ ይሥሐቅም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “መኖሪያህ ከምድር በረከት፣ ከላይም ከሰማይ ጠል የራቀ ይሆናል፤ በሰይፍ ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ። አምርረህ በተነሣህ ጊዜ ግን፣ ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ፣ ወዲያ ትጥላለህ።”
ዘፍጥረት 27:39-40 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አባቱ ይስሐቅም መለሰ አለውም፦ እነሆ መኖሪያህ ከምድር ስብ ከላይ ከሚገኝ ከሰማይም ጠል ይሆናል፤ በሰይፍህም ትኖራለህ፥ ለወንድምህም ትገዛለህ ነገር ግን በተቃወምኸው ጊዜ ቀንበሩን ከአንገትህ ትጥላለይ።