ዘፍጥረት 27:34 - Compare All Versions

ዘፍጥረት 27:34 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ዔሳ​ውም የአ​ባ​ቱን ቃል በሰማ ጊዜ ታላቅ፥ እጅ​ግም መራራ ጩኸት ጮኸ፤ አባ​ቱ​ንም፥ “አባቴ ሆይ፥ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ከኝ” አለው።

ዘፍጥረት 27:34 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ዔሳው የአባቱን ቃል ሲሰማ፣ ድምፁን ከፍ በማድረግ ምርር ብሎ አለቀሰ፤ አባቱንም፣ “አባቴ ሆይ፤ እኔንም ደግሞ እባክህ መርቀኝ” አለው።

ዘፍጥረት 27:34 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ዔሳውም የአባቱን ቃል በሰማ ጊዜ ታላቅ እጅግም መራራ ጩኸት ጮኸ አባቱንም፦ አባቴ ሆይ እኔንም ደግሚ ባርከኝ አለው።

ዘፍጥረት 27:34 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ዔሳው ይህን በሰማ ጊዜ ድምፁን ከፍ በማድረግ ምርር ብሎ እያለቀሰ “አባቴ ሆይ! እኔንም መርቀኝ!” አለ።

ዘፍጥረት 27:34 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ዔሳውም የአባቱን ቃል በሰማ ጊዜ ታላቅ እጅግም መራራ ጩኸት ጮኸ፥ አባቱንም፦ “አባቴ ሆይ፥ እኔንም ደግሞ ባርከኝ” አለው።