ዘፍጥረት 27:28-29
ዘፍጥረት 27:28-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል፥ ከምድርም ስብ፥ የእህልንም፥ የወይንንም፥ የዘይትንም ብዛት ይስጥህ፤ አሕዛብ ይገዙልህ፤ አለቆችም ይስገዱልህ፤ ለወንድምህ ጌታ ሁን፤ የአባትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
ዘፍጥረት 27:28-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር የሰማይን ጠል፣ የምድርንም በረከት፣ የተትረፈረፈ እህልና የወይን ጠጅ ይስጥህ። መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህ የተባረኩ ይሁኑ።”
ዘፍጥረት 27:28-29 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል ከምድርም የእህልንም የወይንንም ብዛት ይስጥህ አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ ለወንድሞችህ ጌት ሁን የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩም ይሁን።