ዘፍጥረት 26:4-5
ዘፍጥረት 26:4-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ይህችንም ምድር ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤ አባትህ አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፤ ትእዛዜንና ፍርዴን፥ ሥርዐቴንና ሕጌንም ጠብቆአልና።”
ዘፍጥረት 26:4-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፤ ይህን ምድር በሙሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ። ይኸውም አብርሃም ቃሌን ሰምቶ፣ ድንጋጌዬን፣ ትእዛዜን፣ ሥርዐቴንና ሕጌን በመጠበቁ ነው።”
ዘፍጥረት 26:4-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ ይባረላሉ፤ አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴም ሕጌ፥ ጠብቆአልና።