ዘፍጥረት 26:1-33

ዘፍጥረት 26:1-33 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በም​ድ​ርም ቀድሞ በአ​ብ​ር​ሃም ዘመን ከሆ​ነው ራብ ሌላ ራብ ሆነ፤ ይስ​ሐ​ቅም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ንጉሥ ወደ አቤ​ሜ​ሌክ ወደ ጌራራ ሄደ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ወደ ግብፅ አት​ው​ረድ፤ እኔ በም​ልህ ምድር ተቀ​መጥ። በዚ​ህች ምድር ተቀ​መጥ፤ ከአ​ንተ ጋርም እሆ​ና​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለ​ሁም፤ ይህ​ችን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተም፥ ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለ​ሁና፥ ለአ​ባ​ት​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ል​ሁ​ለ​ትን መሐላ ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ። ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም ምድር ሁሉ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤ አባ​ትህ አብ​ር​ሃም ቃሌን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ፍር​ዴን፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ሕጌ​ንም ጠብ​ቆ​አ​ልና።” ይስ​ሐ​ቅም በጌ​ራራ ተቀ​መጠ። የዚ​ያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ስለ ርብቃ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “እኅቴ ናት” አላ​ቸው፤ የዚህ ስፍራ ሰዎች ለር​ብቃ ሲሉ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ እር​ስ​ዋም ውብ ነበ​ረ​ችና። በዚ​ያም ብዙ ቀን ተቀ​መጠ። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ንጉሥ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በመ​ስ​ኮት ሆኖ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ ይስ​ሐ​ቅን ከሚ​ስቱ ከር​ብቃ ጋር ሲጫ​ወት አየው። አቤ​ሜ​ሌ​ክም ይስ​ሐ​ቅን ጠራ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ ሚስ​ትህ ናት፤ እን​ዴ​ትስ እር​ስ​ዋን፦ ‘እኅቴ ናት’ አልህ?” ይስ​ሐ​ቅም፥ “በእ​ር​ስዋ ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ል​ሞት ብዬ ነው” አለው። አቤ​ሜ​ሌ​ክም አለ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ከሕ​ዝቡ አንዱ ባለ​ማ​ወቅ ከሚ​ስ​ትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀ​ረው ነበር፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ልታ​መ​ጣ​ብን ነበር።” አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ይህን ሰው፥ ሚስ​ቱ​ንም የሚ​ነካ ፍርዱ ክፉ ሞት ነው” ብሎ አዘዘ። ይስ​ሐ​ቅም በዚ​ያች ምድር ዘርን ዘራ፤ በዚ​ያች ዓመ​ትም መቶ እጥፍ ገብስ አገኘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ከው። ከፍ ከፍም አለ፤ እጅ​ግም ታላቅ እስ​ኪ​ሆን ድረስ እየ​ጨ​መረ ይበዛ ነበር፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን፥ ብዙ በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ የእ​ርሻ መሬ​ት​ንም ገዛ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎ​ችም ቀኑ​በት። በአ​ባቱ በአ​ብ​ር​ሃም ዘመን የአ​ባቱ ሎሌ​ዎች የማ​ሱ​አ​ቸ​ውን ጕድ​ጓ​ዶች ሁሉ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎች ደፈ​ኑ​አ​ቸው፤ አፈ​ር​ንም ሞሉ​ባ​ቸው። አቤ​ሜ​ሌ​ክም ይስ​ሐ​ቅን፥ “ከእኛ ተለ​ይ​ተህ ሂድ፤ ከእኛ ይልቅ እጅግ በር​ት​ተ​ሃ​ልና” አለው። ይስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሄደ፤ በጌ​ራ​ራም ሸለቆ ሰፈረ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጠ። ይስ​ሐ​ቅም የአ​ባቱ የአ​ብ​ር​ሃም አገ​ል​ጋ​ዮች ቈፍ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን የውኃ ጕድ​ጓ​ዶች ደግሞ አስ​ቈ​ፈረ፤ አባቱ አብ​ር​ሃም ከሞተ በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎች ደፍ​ነ​ዋ​ቸው ነበ​ርና፤ አባ​ቱም አብ​ር​ሃም ይጠ​ራ​ቸው በነ​በ​ረው ስም ጠራ​ቸው። የይ​ስ​ሐቅ ሎሌ​ዎ​ችም በጌ​ራራ ሸለቆ ውስጥ ጕድ​ጓድ ቈፈሩ፤ በዚ​ያም ጣፋጭ የውኃ ምንጭ አገኙ። የጌ​ራራ እረ​ኞች ከይ​ስ​ሐቅ እረ​ኞች ጋር፥ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተጣሉ፤ የዚ​ያ​ች​ንም ጕድ​ጓድ ስም “ዐዘ​ቅተ ዐመፃ” ብሎ ጠራት፤ እነ​ርሱ በድ​ለ​ው​ታ​ልና። ይስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሄደ በዚ​ያም ሌላ ጕድ​ጓድ ማሰ፥ ስለ እር​ስ​ዋም ደግሞ ተጣ​ሉት፤ ስም​ዋ​ንም “ጽልእ” ብሎ ጠራት። ከዚ​ያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድ​ጓድ ቈፈረ፤ ስለ እር​ስ​ዋም አል​ተ​ጣ​ሉ​ትም፤ ስም​ዋ​ንም “መር​ኅብ” ብሎ ጠራት፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​ፋ​ልን፤ በም​ድ​ርም አበ​ዛን።” ከዚ​ያም ወደ ዐዘ​ቅተ መሐላ ሄደ። በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እኔ የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ነኝ፤ አት​ፍራ፤ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስለ አባ​ትህ ስለ አብ​ር​ሃም ዘር​ህን አበ​ዛ​ዋ​ለሁ።” በዚ​ያም ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ፤ በዚ​ያም ድን​ኳን ተከለ፤ የይ​ስ​ሐ​ቅም ሎሌ​ዎች በዚያ ጕድ​ጓድ ማሱ። አቤ​ሜ​ሌ​ክና ሚዜው አኮ​ዘት፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ፋኮል ከጌ​ራራ ወደ እርሱ ሄዱ። ይስ​ሐ​ቅም፥ “ለምን ወደ እኔ መጣ​ችሁ? እና​ንተ ጠል​ታ​ች​ሁ​ኛል፤ ከእ​ና​ን​ተም ለይ​ታ​ችሁ አሳ​ድ​ዳ​ች​ሁ​ኛ​ልና” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም አሉት፥ “እኛ የጠ​ላ​ንህ አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​ካም አኑ​ረን፥ በመ​ል​ካም አሰ​ና​በ​ት​ንህ እንጂ፥ አሁ​ንም አንተ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ነህ። አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር እንደ አለ በአ​የን ጊዜ በአ​ን​ተና በእኛ መካ​ከል መሐላ ይሁን፤ አንተ በእኛ ላይ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ፤ እኛም በአ​ንተ ላይ ክፉ እን​ዳ​ና​ደ​ርግ እን​ማ​ማ​ላ​ለን።” ይስ​ሐ​ቅም ማዕድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ በሉም፤ ጠጡም። ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተማ​ማሉ፤ ይስ​ሐ​ቅም አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ ከእ​ር​ሱም በደ​ኅና ሄዱ። በዚ​ያም ቀን የይ​ስ​ሐቅ ሎሌ​ዎች መጡ፤ ስለ ቈፈ​ሩ​አ​ትም ጕድ​ጓድ፥ ውኃ አገ​ኘን ብለው ነገ​ሩት። ስም​ዋ​ንም “መሐላ” ብሎ ጠራት፤ ስለ​ዚ​ህም የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ዐዘ​ቅተ መሐላ” ይባ​ላል።

ዘፍጥረት 26:1-33 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ፣ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። ይሥሐቅም የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ ወደሚኖርበት ወደ ጌራራ ሄደ። በዚያም እግዚአብሔር ለይሥሐቅ ተገልጦ እንዲህ አለው፤ “እኔ በምነግርህ ምድር ተቀመጥ እንጂ፣ ወደ ግብጽ አትውረድ፤ ለጥቂት ጊዜ እዚሁ አገር ተቀመጥ፤ እኔም ካንተ ጋራ እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘርህ በመስጠት ለአባትህ ለአብርሃም በመሐላ የገባሁለትን ቃል አጸናለሁ። ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፤ ይህን ምድር በሙሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ። ይኸውም አብርሃም ቃሌን ሰምቶ፣ ድንጋጌዬን፣ ትእዛዜን፣ ሥርዐቴንና ሕጌን በመጠበቁ ነው።” ስለዚህ ይሥሐቅ በጌራራ ተቀመጠ። የዚያም አገር ሰዎች ስለ ሚስቱ በጠየቁት ጊዜ፣ “እኅቴ ናት” አለ፤ ምክንያቱም፣ “ሚስቴ ናት ብል ርብቃ ቈንጆ ስለ ሆነች፣ ያገሬው ሰዎች በርሷ ምክንያት ይገድሉኛል” በማለት ፈርቶ ነበር። ይሥሐቅ ብዙ ጊዜ በዚያ ከኖረ በኋላ፣ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ አንድ ቀን ወደ ውጭ ሲመለከት፣ ይሥሐቅ ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ። አቢሜሌክም ይሥሐቅን ጠርቶ፣ “እርሷ ሚስትህ ሆና ሳለች፣ እንዴት ‘እኅቴ ናት’ ትላለህ?” አለው። ይሥሐቅም፣ “በርሷ ሰበብ፣ ሕይወቴን እንዳላጣ ብዬ ነው” አለው። አቢሜሌክም መልሶ፣ “እንዲህ ያለ ነገር ያደረግህብን ለምንድን ነው? ከሰዎቻችን አንዱ ሚስትህን ቢደፍራት ኖሮ በእኛ ላይ በደል አስከትለህብን ነበር እኮ!” አለው። አቢሜሌክም፣ “ይህን ሰው ወይም ሚስቱን የነካ በሞት ይቀጣል” የሚል ትእዛዝ ለሕዝቡ ሁሉ አወጣ። ይሥሐቅም በዚያች ምድር ዘር ዘራ፣ እግዚአብሔርም ባረከለትና በዚያ ዓመት መቶ ዕጥፍ አመረተ። ሰውየውም እጅግ ባለጠጋ እስኪሆን ድረስ ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረለት ሄደ። ብዙ የበግና የፍየል መንጋ፣ ብዙ ከብት፣ ብዙ አገልጋዮችም ስለ ነበሩት፣ ፍልስጥኤማውያን ተመቀኙት። ከዚህ የተነሣ ፍልስጥኤማውያን፣ አባቱ አብርሃም በሕይወት በነበረበት ጊዜ፣ የአብርሃም አገልጋዮች የቈፈሯቸውን የውሃ ጕድጓዶች በሙሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኗቸው። አቢሜሌክም ይሥሐቅን፣ “ከእኛ ይልቅ ኀያል ሆነሃልና አገራችንን ልቀቅልን” አለው። ይሥሐቅም ያን ቦታ ትቶ ሄደ፤ በጌራራ ሸለቆም ተቀመጠ። ይሥሐቅም በአባቱ በአብርሃም ጊዜ ተቈፍረው የነበሩትን፣ አባቱ ከሞተ በኋላ ፍልስጥኤማውያን የደፈኗቸውን የውሃ ጕድጓዶች እንደ ገና እንዲከፈቱ አደረገ፤ አባቱ ቀድሞ ባወጣላቸው ስምም መልሶ ጠራቸው። የይሥሐቅ አገልጋዮች በሸለቆው ውስጥ ሲቈፍሩ፣ ከጕድጓዱ የሚፈልቅ ውሃ አገኙ። የጌራራ እረኞች ግን፣ “ውሃው የእኛ ነው” በማለት ከይሥሐቅ እረኞች ጋራ ጠብ አነሡ፤ ከዚህ የተነሣ ይሥሐቅ ያን የውሃ ጕድጓድ ኤሴቅ ብሎ ጠራው፤ በጕድጓዱ ምክንያት ተጣልተውታልና። አሁንም እንደ ገና ሌላ የውሃ ጕድጓድ ቈፈሩ፤ አሁንም ሌላ ግጭት ተፈጠረ፤ ስለዚህ የውሃ ጕድጓዱን ስጥና ብሎ ጠራው። ይሥሐቅም ያን ቦታ ትቶ ሌላ ስፍራ ላይ የውሃ ጕድጓድ አስቈፈረ፤ በዚህ ጊዜ ግን አንድም ሰው ጠብ አላነሣበትም፤ ስለዚህ ያን የውሃ ጕድጓድ፣ “አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጥቶናል፤ እኛም በምድር ላይ እንበዛለን” ሲል ርኆቦት ብሎ ጠራው። ከዚያም ይሥሐቅ ወደ ቤርሳቤህ ወጣ። በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና፣ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ እባርክሃለሁ፤ ስለ አገልጋዬም ስለ አብርሃም ስል ዘርህን አበዛለሁ” አለው። ይሥሐቅም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ፤ ድንኳንም ተከለ፤ አገልጋዮቹም በዚያ የውሃ ጕድጓድ ቈፈሩ። አቢሜሌክም ከአማካሪው ከአዘኮትና ከሰራዊቱ አዛዥ ከፊኮል ጋራ ከጌራራ ተነሥቶ ይሥሐቅ ወዳለበት ስፍራ መጣ። ይሥሐቅም፣ “ጠልታችሁኝ ካባረራችሁኝ በኋላ፣ አሁን ደግሞ ለምን መጣችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ መሆኑን በግልጽ ተረድተናል፤ ስለዚህም፣ ‘በመሐላ የጸና ውል በመካከላችን መኖር አለበት’ አልን፤ ይህም በእኛና በአንተ መካከል የሚጸና ውል ነው፤ አሁንም ከአንተ ጋራ ስምምነት እናድርግ፤ አንተን እንዳልጐዳንህ፣ ነገር ግን በጎነትን እንዳሳየንህና በሰላም እንደ ሸኘንህ ሁሉ፣ አንተም ክፉ እንዳታደርግብን በመካከላችን ውል ይደረግ፤ አንተን እንደሆን መቼም እግዚአብሔር ባርኮሃል።” ይሥሐቅም ድግስ ደግሶ አበላቸው፤ አጠጣቸው። በማግስቱም በማለዳ ተነሥተው፣ በመካከላቸው መሐላ ፈጸሙ። ይሥሐቅም አሰናበታቸው፤ እነርሱም በሰላም ሄዱ። በዚያ ዕለት፣ የይሥሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቈፈሩት የውሃ ጕድጓድ ነገሩት፤ “ውሃ እኮ አገኘን!” አሉት። እርሱም የውሃውን ጕድጓድ ሳቤህ አለው፤ ከዚያም የተነሣ የከተማዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ተብሎ ይጠራል።

ዘፍጥረት 26:1-33 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ላይ ራብ ሆነ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወድ አቢሜሌክ ወደ ግውራራ ሄደ። እግዚአብሔር ተገለጠለት እንዲህም አለው፦ ወደ ግብፅ አትውረድ፥ እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ። በዚህች ምድር ተቀመጥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ። ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ ይባረላሉ፤ አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴም ሕጌ፥ ጠብቆአልና። ይስሐቅም በጌራራ ተቀመጠ። የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት እርሱም፦ እኅቴ ናት አለ የዚያም ስፍራ ስዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና እርስዋ ውብ ነበረችና። በዚያም ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኍላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌም በመስኮት ሆኖ ጎበኘ፥ ይስሐቅም ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ። አቢሜሌክም ይስሐቅን ጠራ እንዲህም አለው፦ እነሆ ሚስትህ ናት እንዴትስ እርስዋን፦ እኅቴ ናትአልህ? ይስሐቅም፦ በእርስዋ ምክንያት እንዳልሞት ብዬ ነው አለው። አቢሜልውክም አለ፦ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? ከሕዝብ አንዱ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀረው ነበር፥ ኃጢአትንም ልታመጣብን ነበር። አቢሜሌክም ሕዝቡን ሁሉ፦ ይህን ሰው ሚስቱንም የሚነካ ሞትን ይሙት ብሎ አዘዘ። ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ እግዚአብሔርም ባረከው። ባለ ጠጋ ሰውም ሆነ እጅግ እስኪበልጥ ድረስም እየጨመተ ይበዛ ነበር፤ የበግና የላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት። በአባቱ በአብርሃም ዘመን የአባቱ ሎሌዎች የማሱአቸውን ጕድጓዶች ሁሉ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፈኑአቸው አፈርንም ሞሉባቸው። አቢሜሌክም ይስሐቅን፦ ከእኛ ተለይተህ ሂድ ከእኛ ይልቅ እጅግ በርትተሃልና አለው። ይስሐቅም ከዚያ ሄደ በጌራራም ሸለቆ ሰፍሮ በዚያ ተቀመጠ። ይስሐቅም በአባቱ በአብርሃም ዘመን ቈፍረዋቸ የነበሩትን የውኃ ጕድጓዶች ደግሞ አስቈፈረ፤ አብርሃም ከሞተ በኍላ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፍነዋቸው ነበሩን አባቱም ይጠራቸው በነብረው ስም ጠራቸው። የይስሐቅ ሎሌዎችም በሸለቆው ውስጥ ቈፈሩ፥ በዚያም የሚመነጭ የውኃ ጕድጓድ አገኙ። የጌራራ አገር እረኞች ለይስሐቅ እረኞች ጋር፦ ውኃው የእኛ ነው ሲሉ ተከራከሩ፤ የዚይችንም ጕድጓድ ስም ኤሴቅ ብሎ ጠራት ለእርስዋ ሲሉ ተጣልተዋልና። ሌላ ጕድጓድም ማሱ ስለ እርስዋም ደግሞ ተጣሉ፤ ስምዋንም ስጥና ብሎ ጠራት። ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ አስቋፈረ ስለ እርስዋም አልተጣሉም፤ ስምዋንም፥ ርኖቦት ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን በምድርም እንበዛለን። ከዚያም ወደ ቤርሳቤህ ወጣ። በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና እባርክሃለሁ ስለ ባሪያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ። በዚያም መሠዊያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፥ በዚይም ድንኳን ተከለ፤ የይስሐቅም ሎሌዎች በዚያ ጕድጓድ ማሱ። አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱም አለቃ ፊኮል ከጌራራ ወደ እርሱ ሄዱ። ይስሐቅም፦ ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? እናንተ ጠልታችሁኛል ከእናንተም ለይታችሁ አሳድዳችሁኛል አላቸው። እነርሱም አሉት፦ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ በእርግጥ አየን፤ ስለዚህም፦ በእኛን በአንተ መካከል መሐላ ይሁን እኝ አንተን እንዳልነካንህ፥ በጎነትንም ብቻ እንዳሳየንህ፥ በደኅናም እንደ ሰደድንህ አንተም ክፉ እንዳትሠራብን ቃል ኪዳን ከአንተ ጋር እናድርግ አልን አንተ አሁን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተባረክህ ነህ። ይስሐቅም ማዕድ አቀረበላቸው በሉም ጠጡም። ማልደውም ተነሡ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ ይስሐቅም አሰናበታቸው ከእርሱም ወጥተው በደኅና ሄዱ። በዚይም ቀን የይስሐቅ ሎሌዎች መጡ፥ ስለቋፈሩአትም ጕድጓድ፦ ውኃ አገኘን ብለው ነገሩት። ስምዋንም ሳቤህ ብሎ ጠራት ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ነው።

ዘፍጥረት 26:1-33 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ ዳግመኛ ራብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቤሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤ በዚያም እግዚአብሔር ለይስሐቅ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፤ “ወደ ግብጽ አገር አትሂድ፤ እንድትኖርበት በምነግርህ በዚህ ምድር ተቀመጥ፤ እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈጽማለሁ፤ ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ይህንንም ሁሉ ምድር አወርሳቸዋለሁ፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ። አንተን የምባርክበትም ምክንያት አባትህ አብርሃም ለእኔ ታዛዥ በመሆን የሰጠሁትን ትእዛዞች፥ ድንጋጌዎችንና ሕጎችን ሁሉ ስለ ጠበቀ ነው።” ስለዚህ ይስሐቅ መኖሪያውን በገራር አደረገ፤ የዚያ አገር ሰዎችም ስለ ርብቃ “ምንህ ናት” ብለው በጠየቁት ጊዜ “እኅቴ ናት” አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቈንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው። ይስሐቅ እዚያ አገር ብዙ ጊዜ ከቈየ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቤሜሌክ በመስኮት ወደ ውጪ ሲመለከት ይስሐቅና ርብቃ እንደ ባልና ሚስት በመዳራት ሲጫወቱ አየ፤ ስለዚህ አቤሜሌክ ይስሐቅን አስጠርቶ “ለካስ ርብቃ ሚስትህ ናት! ታዲያ ‘እኅቴ ናት’ ያልከው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “ሚስቴ ነች ያልኩ እንደሆን ሰዎች ይገድሉኛል ብዬ ስለ ፈራሁ ነው” ብሎ መለሰ። አቤሜሌክም “ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? ከእኛ ሰዎች አንዱ በቀላሉ ሚስትህን ለመድፈር በቻለ ነበር፤ እኛንም ኃጢአተኞች ልታደርገን ነበር፤” ቀጥሎም አቤሜሌክ “ይህን ሰው ወይም ሚስቱን የሚነካ ሰው በሞት ይቀጣል” የሚል ማስጠንቀቂያ ለሕዝቡ ሰጠ። ይስሐቅ በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፤ እግዚአብሔር ስለ ባረከውም በዚያኑ ዓመት መቶ እጥፍ አመረተ፤ ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረለት ስለ ሄደ እጅግ ባለጸጋ ሆነ። ብዙ የበግና የከብት መንጋ፥ እንዲሁም ብዙ አገልጋዮች ስለ ነበሩት ፍልስጥኤማውያን ቀኑበት። ስለዚህ የይስሐቅ አባት አብርሃም በሕይወት በነበረበት ዘመን የእርሱ አገልጋዮች ቆፍረዋቸው የነበሩትን የውሃ ጒድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው። በዚያን ጊዜ አቤሜሌክ ይስሐቅን “ኀይልህ ከእኛ ይልቅ እየበረታ ስለ ሄደ፥ አገራችንን ለቀህ ውጣ” አለው። በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ያንን ቦታ ለቆ በገራር ሸለቆ ውስጥ ሰፈረ፤ እዚያም ተቀመጠ። አብርሃም በሕይወት ሳለ አስቈፍሮአቸው የነበሩትንና አብርሃም ከሞተ በኋላ ግን ፍልስጥኤማውያን የደፈኑአቸውን የውሃ ጒድጓዶች ይስሐቅ እንደገና እንዲቈፈሩ አደረገ፤ አባቱ ባወጣላቸው ስሞችም ጠራቸው። የይስሐቅ አገልጋዮች በሸለቆው ውስጥ የውሃ ጒድጓድ ቆፈሩና ጥሩ የምንጭ ውሃ አገኙ፤ የገራር እረኞች ግን “ይህ ውሃ የእኛ ነው” በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ተጣሉ። በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ጒድጓዱን “ዔሤቅ” ብሎ ሰየመው። የይስሐቅ አገልጋዮች ሌላ የውሃ ጒድጓድ ቈፈሩ፤ በዚህኛውም ጒድጓድ ምክንያት ሌላ ጠብ ተነሣ፤ ስለዚህ ይስሐቅ ይህን ጒድጓድ “ስጥና” ብሎ ሰየመው። ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጒድጓድ ቈፈረ፤ በዚህኛው የውሃ ጒድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተነሣ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል፥ ያንን ቦታ ‘ረሖቦት’ ” ብሎ ሰየመው። ከዚህ በኋላ ይስሐቅ ወደ ቤርሳቤህ ወጣ፤ በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ እኔ ከአንተ ጋር ስለ ሆንኩ አትፍራ፤ ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ” አለው። ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጒድጓድ ቈፈሩ። አቤሜሌክ ከአማካሪው ከአሑዘትና ከሠራዊቱ አዛዥ ከፊኮል ጋር ይስሐቅን ለመጐብኘት ከገራር መጣ፤ ስለዚህ ይስሐቅ “ከዚህ በፊት ጠልታችሁኝ ከአገራችሁ እንድወጣ አድርጋችሁኛል፤ ታዲያ አሁን ልትጐበኙኝ የመጣችሁት ለምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈጸም አስበናል፤ በዚህም መሠረት ቃል ኪዳን እንድትገባልን የምንፈልገው፥ እኛ በአንተ ላይ ምንም ግፍ እንዳልሠራን አንተም በእኛ ላይ ምንም ዐይነት በደል እንዳታደርስብን ነው፤ ዘወትር መልካም ነገር አደረግንልህ እንጂ ክፉ አላደረግንብህም፤ ከአገራችንም የወጣኸው በሰላም ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ባርኮሃል።” ከዚህ በኋላ፥ ይስሐቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ጠጡ። በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ተነሡና ተማማሉ፤ ይስሐቅ ካሰናበታቸው በኋላም በሰላም ሄዱ። በዚያኑ ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቆፈሩት ጒድጓድ ለይስሐቅ ነገሩት፤ “ውሃ አገኘን” ብለውም ነገሩት። እርሱም የውሃውን ጒድጓድ “ሳቤህ” ብሎ ጠራው፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ “ቤርሳቤህ” እየተባለ ይጠራል።

ዘፍጥረት 26:1-33 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ላይ ራብ ሆነ፥ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወደ አቢሜሌክ ወደ ጌራራ ሄደ። ጌታ ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ “ወደ ግብጽ አትውረድ፥ እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ። በዚህች ምድር ተቀመጥ፥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም፥ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ። ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፥ አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን ሕጌንም ጠብቆአልና።” ይስሐቅም በጌራራ ተቀመጠ። የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት፥ እርሱም፦ “እኅቴ ናት” አለ፥ የዚያም ስፍራ ስዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና፥ እርሷ ውብ ነበረችና። በዚያም ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ሆኖ ጎበኘ፥ ይስሐቅም ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ። አቢሜሌክም ይስሐቅን ጠራ እንዲህም አለው፦ “እነሆ ሚስትህ ናት፥ እንዴትስ እርሷን፦ ‘እኅቴ ናት’ አልህ?” ይስሐቅም፦ “በእርሷ ምክንያት እንዳልሞት ብዬ ነው” አለው። አቢሜሌክም አለ፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ከሕዝብ አንዱ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀረው ነበር፥ ኃጢአትንም ልታመጣብን ነበር።” አቢሜሌክም ሕዝቡን ሁሉ፦ “ይህን ሰው ሚስቱንም የሚነካ ሞትን ይሙት” ብሎ አዘዘ። ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ፥ እግዚአብሔርም ባረከው። ባለ ጠጋ ሰውም ሆነ፥ እጅግ እስኪበልጥ ድረስም እየጨመረ ይበዛ ነበር፥ በግና ላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት፥ የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት። በአባቱ በአብርሃም ዘመን የአባቱ ሎሌዎች የማሱአቸውን ጉድጓዶች ሁሉ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፈኑአቸው፥ አፈርንም ሞሉባቸው። አቢሜሌክም ይስሐቅን፦ “ከእኛ ተለይተህ ሂድ፥ ከእኛ ይልቅ እጅግ በርትተሃልና” አለው። ይስሐቅም ከዚያ ሄደ፥ በጌራራም ሸለቆ ተቀመጠ። ይስሐቅም በአባቱ በአብርሃም ዘመን ቈፍረዋቸው የነበሩትን የውኃ ጉድጓዶች ደግሞ አስቈፈረ፥ አብርሃም ከሞተ በኋላ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፍነዋቸው ነበሩና፥ አባቱም ይጠራቸው በነበረው ስም ጠራቸው። የይስሐቅ ሎሌዎችም በሸለቆው ውስጥ ቈፈሩ፥ በዚያም የሚመነጭ የውኃ ጉድጓድ አገኙ። የጌራራ አገር እረኞች ከይስሐቅ እረኞች ጋር፦ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተከራከሩ፥ የዚያችንም ጉድጓድ ስም “ኤሴቅ” ብሎ ጠራት፥ ለእርሷ ሲሉ ተጣልተዋልና። ሌላ ጉድጓድም ማሱ፥ ስለ እርሷም ደግሞ ተጣሉ፥ ስምዋንም “ስጥና” ብሎ ጠራት። ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጉድጓድ አስቈፈረ፥ ስለ እርሷም አልተጣሉም፥ ስምዋንም “ርኆቦት” ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ “አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።” ከዚያም ወደ ቤርሳቤህ ወጣ። በዚያችም ሌሊት ጌታ ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፥ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፥ እባርክሃለሁ፥ ስለ ባርያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።” በዚያም መሠዊያን ሠራ የጌታንም ስም ጠራ፥ በዚያም ድንኳን ተከለ፥ የይስሐቅም አገልጋዮች በዚያ ጉድጓድ ማሱ። አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱም አለቃ ፊኮል ከጌራራ ወደ እርሱ ሄዱ። ይስሐቅም፦ “ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? እናንተ ጠልታችሁኛል፥ ከእናንተም ለይታችሁ አሳድዳችሁኛል” አላቸው። እነርሱም፤ “ጌታ ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ አየን፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል መሐላ ይኑር፤ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንጋባ፥ እኛ አንተን እንዳልነካንህ፥ በጎነትንም ብቻ እንዳሳየንህ፥ በሰላምም እንደ ሰደድንህ፥ አንተም ክፉ እንዳትሠራብን፥ አንተ አሁንም ከጌታ ዘንድ የተባረክህ ነህ።” ይስሐቅም ማዕድ አቀረበላቸው፥ በሉም ጠጡም። ማልደውም ተነሡ፥ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ፥ ይስሐቅም አሰናበታቸው፥ ከእርሱም ወጥተው በሰላም ሄዱ። በዚያም ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጡ፥ ስለ ቈፈሩአትም ጉድጓድ፦ “ውኃ አገኘን ብለው ነገሩት።” ስምዋንም “ሳቤህ” ብሎ ጠራት፥ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ነው።