ዘፍጥረት 25:32-33
ዘፍጥረት 25:32-33 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዔሳውም፥ “እነሆ፥ እኔ ልሞት ነኝ፤ ይህች ብኵርና ለምኔ ናት?” አለ። ያዕቆብም፥ “ብኵርናህን ትሰጠኝ ዘንድ እስኪ ዛሬ ማልልኝ” አለው። ዔሳውም ማለለት፤ ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ።
ዘፍጥረት 25:32-33 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ዔሳውም፣ “እነሆ፤ ልሞት ደርሻለሁ፤ ታዲያ ብኵርናው ምን ያደርግልኛል!” አለ። ያዕቆብም ዔሳውን፣ “እንግዲያማ፣ አስቀድመህ ማልልኝ” አለው፤ ስለዚህም ማለለት፤ ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠለት።
ዘፍጥረት 25:32-33 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዔሳውም፦ እነሆ እኔ ልሞት ነኝ ይህች ብኵርና ለምኔ ናት? አለ። ያዕቆብም፦ እስኪ በመጀመሪያ ማልልኝ አለው። ማለለትም ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ።