ዘፍጥረት 25:29-33
ዘፍጥረት 25:29-33 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ለያዕቆብም የምስር ንፍሮ ቀቀለችለት፤ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ፤ ዔሳውም ያዕቆብን፥ “ከምስር ንፍሮህ አብላኝ፤ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና” አለው፤ ስለዚህም ስሙ ኤዶም ተባለ። ያዕቆብም ዔሳውን፥ “ዛሬ ብኵርናህን ስጠኝ” አለው። ዔሳውም፥ “እነሆ፥ እኔ ልሞት ነኝ፤ ይህች ብኵርና ለምኔ ናት?” አለ። ያዕቆብም፥ “ብኵርናህን ትሰጠኝ ዘንድ እስኪ ዛሬ ማልልኝ” አለው። ዔሳውም ማለለት፤ ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ።
ዘፍጥረት 25:29-33 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አንድ ቀን ያዕቆብ ወጥ እየሠራ ሳለ ዔሳው እጅግ ተርቦ ከዱር መጣ። ዔሳውም ያዕቆብን፣ “ቶሎ በል፤ በጣም ርቦኛልና ከዚህ ቀይ ወጥ አብላኝ” አለው። ስለዚህም ስሙ ኤዶም ተባለ። ያዕቆብም፣ “በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ” አለው። ዔሳውም፣ “እነሆ፤ ልሞት ደርሻለሁ፤ ታዲያ ብኵርናው ምን ያደርግልኛል!” አለ። ያዕቆብም ዔሳውን፣ “እንግዲያማ፣ አስቀድመህ ማልልኝ” አለው፤ ስለዚህም ማለለት፤ ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠለት።
ዘፍጥረት 25:29-33 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ያዕቆብም ወጥ ሠራ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ፤ ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው ስለዚህ ስሙ ኤዶም ተባለ። ያዕቆብም፦ በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ አለው። ዔሳውም፦ እነሆ እኔ ልሞት ነኝ ይህች ብኵርና ለምኔ ናት? አለ። ያዕቆብም፦ እስኪ በመጀመሪያ ማልልኝ አለው። ማለለትም ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ።
ዘፍጥረት 25:29-33 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ቀይ የምስር ወጥ በመሥራት ላይ እንዳለ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤ ስለዚህም ያዕቆብን “ከዚህ ከቀይ ወጥ ስጠኝ” አለው። ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር። ያዕቆብም “መጀመሪያ ብኲርናህን ሽጥልኝ” አለው። ዔሳውም “እኔ በራብ መሞቴ ነው፤ ታዲያ ብኲርና ምን ያደርግልኛል?” አለው። ያዕቆብም “እንግዲያውስ ብኲርናህን እንደምትሸጥልኝ መጀመሪያ ማልልኝ” አለው። ስለዚህ ዔሳው ምሎ ብኲርናውን ለያዕቆብ ሸጠ።
ዘፍጥረት 25:29-33 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ወጥ ሲሠራ፥ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤ ዔሳውም ያዕቆብን፥ “ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ እርቦኛልና!” አለው፤ (ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር።) ያዕቆብም፥ “በመጀመሪያ ብኩርናህን ሽጥልኝ” አለው። ዔሳውም “እኔ መሞቴ ነው፤ ታዲያ ብኲርና ምን ያደርግልኛል?” አለው። ያዕቆብም፥ “እስኪ በቅድሚያ ማልልኝ” አለው። ስለዚህ ዔሳው ምሎ ብኲርናውን ለያዕቆብ ሸጠ።