ዘፍጥረት 22:15-16
ዘፍጥረት 22:15-16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የእግዚአብሔር መልአክ ሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ጠራውና እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ‘ብዙ በረከት እንደምሰጥህ በራሴ ስም እምላለሁ’ ይላል፤ ይህን ስላደረግህና አንድ ልጅህንም ለእኔ ለመስጠት ስላልተቈጠብክ፥
ዘፍጥረት 22:15-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የእግዚአብሔር መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠራው፤ እንዲህም አለው፦ “እግዚአብሔር በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ ለምትወድደው ልጅህም ከእኔ አልራራህምና መባረክን እባርክሃለሁ፤
ዘፍጥረት 22:15-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የእግዚአብሔርም መልአክ አብርሃምን ከሰማይ ዳግመኛ ጠራው፤ እንዲህም አለው፤ “እግዚአብሔርም በራሴ ማልሁ አለ፤ አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሣሣህምና፣
ዘፍጥረት 22:15-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የእግዚአብሔር መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለትኛ ጊዜ ጠራው፦ እንዲህም አለው፦ እንዴህም አለው፦ እግዜአብሔር፦ በራሴማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፦ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምን