ዘፍጥረት 2:18-20
ዘፍጥረት 2:18-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር አምላክም አለ፥ “ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።” እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ደግሞ ከምድር ፈጠረ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደጠራው ስሙ ያው ሆነ። አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው። ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር።
ዘፍጥረት 2:18-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ፣ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ” አለ። እግዚአብሔር አምላክ የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጥረታት ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ። ስለዚህ አዳም ለከብቶች፣ ለሰማይ ወፎች፣ ለዱር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው። ይሁን እንጂ ለአዳም ተስማሚ ረዳት አልተገኘለትም ነበር።
ዘፍጥረት 2:18-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚእብሔር አምላክም አለ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረት እንፍጠርለት። እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎእን ሁሉ ከመሬት አደረገ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ እዳምም ሕያው ነፍስ ልስለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠርው ስሙ ያው ሆነ። አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፤ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፤ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላአው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር።
ዘፍጥረት 2:18-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ቀጥሎም እግዚአብሔር አምላክ “ሰው ብቻውን መኖሩ መልካም አይደለም፤ ስለዚህ ረዳት ጓደኛ እፈጥርለታለሁ” አለ። እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ እንስሶችንና ወፎችን ሁሉ ፈጠረ፤ ምን ዐይነት ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳም ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ያወጣለት ስም መጠሪያው ሆነ። በዚህ ዐይነት አዳም ለወፎቹና ለእንስሶቹ ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ለእርሱ ግን ረዳት ጓደኛ አልተገኘለትም ነበር።
ዘፍጥረት 2:18-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ጌታ እግዚእብሔርም፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ የምትሆነውን ረዳት እፈጥርለታለሁ” አለ። የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ፥ ጌታ እግዚአብሔር፥ ከምድር ፈጠረ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፥ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ። አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፥ ነገር ግን አዳም ለእርሱ ሁነኛ ረዳት አልተገኘለትም ነበር።