ዘፍጥረት 2:1-25

ዘፍጥረት 2:1-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሰማ​ይና ምድር ዓለ​ማ​ቸ​ውም ሁሉ ተፈ​ጸሙ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሠ​ራ​ውን ሥራ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸመ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከሠ​ራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰባ​ተ​ኛ​ዋን ቀን ባረ​ካት፤ ቀደ​ሳ​ትም፤ ሊፈ​ጥ​ረው ከጀ​መ​ረው ሥራ ሁሉ በእ​ር​ስዋ ዐር​ፎ​አ​ልና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በፈ​ጠ​ረ​በት ቀን፥ በተ​ፈ​ጠሩ ጊዜ የሰ​ማ​ይና የም​ድር ፍጥ​ረት ይህ ነው። የሜዳ ቍጥ​ቋጦ ሁሉ በም​ድር ላይ ከመ​ኖሩ በፊት፥ የሜ​ዳ​ውም ቡቃያ ሁሉ ከመ​ብ​ቀሉ በፊት፥ አዳ​ምም ከመ​ፈ​ጠሩ በፊት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በም​ድር ላይ አላ​ዘ​ነ​በም ነበር፤ ምድ​ር​ንም የሚ​ሠ​ራ​ባት ሰው አል​ነ​በ​ረም። ነገር ግን የውኃ ምንጭ ከም​ድር ይወጣ ነበር፤ የም​ድ​ር​ንም ፊት ሁሉ ያጠጣ ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ከም​ድር አፈር ፈጠ​ረው፤ በፊ​ቱም የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋ​ስን እፍ አለ​በት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም በኤ​ዶም በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ ገነ​ትን ተከለ፤ የፈ​ጠ​ረ​ው​ንም ሰው በዚያ አኖ​ረው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለማ​የት ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን፥ ለመ​ብ​ላ​ትም መል​ካም የሆ​ነ​ውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከም​ድር አበ​ቀለ፤ በገ​ነ​ትም መካ​ከል የሕ​ይ​ወ​ትን ዛፍ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ሳ​የ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀ​ው​ንም ዛፍ አበ​ቀለ። ወን​ዝም ገነ​ትን ያጠጣ ዘንድ ከኤ​ዶም ይወጣ ነበር፤ ከዚ​ያም ለዐ​ራት መዓ​ዝን ይከ​ፈል ነበር። የአ​ን​ደ​ኛው ወንዝ ስም ኤፌ​ሶን ነው፤ እር​ሱም ወርቅ የሚ​ገ​ኝ​በ​ትን የኤ​ው​ላጥ ምድ​ርን ይከ​ብ​ባል። የዚ​ያ​ችም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው። በዚ​ያም የሚ​ያ​በራ ዕን​ቍና የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ አለ። የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እር​ሱም የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያን ምድር ሁሉ ይከ​ብ​ባል፤ የሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ጤግ​ሮስ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሶር ላይ የሚ​ሄድ ነው። አራ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ኤፍ​ራ​ጥስ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ወስዶ ያበ​ጃ​ትም፥ ይጠ​ብ​ቃ​ትም ዘንድ በኤ​ዶም ገነት አኖ​ረው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አዳ​ምን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “በገ​ነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤ ነገር ግን መል​ካ​ም​ንና ክፉን ከሚ​ያ​ሳ​የ​ውና ከሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀው ዛፍ አት​ብላ፤ ከእ​ርሱ በበ​ላህ ቀን ሞትን ትሞ​ታ​ለ​ህና።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አለ፥ “ሰው ብቻ​ውን ይኖር ዘንድ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ረ​ዳ​ውን ጓደኛ እን​ፍ​ጠ​ር​ለት እንጂ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም የም​ድር አራ​ዊ​ት​ንና የሰ​ማይ ወፎ​ችን ሁሉ ደግሞ ከም​ድር ፈጠረ፤ በምን ስም እን​ደ​ሚ​ጠ​ራ​ቸ​ውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመ​ጣ​ቸው፤ አዳ​ምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እን​ደ​ጠ​ራው ስሙ ያው ሆነ። አዳ​ምም ለእ​ን​ስ​ሳት ሁሉ፥ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም ሁሉ፥ ለም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ ስም አወ​ጣ​ላ​ቸው። ነገር ግን ለአ​ዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አል​ተ​ገ​ኘ​ለ​ትም ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም በአ​ዳም ላይ እን​ቅ​ል​ፍን አመጣ፤ አን​ቀ​ላ​ፋም ፤ ከጎ​ኑም አጥ​ን​ቶች አንድ አጥ​ን​ትን ወስዶ ስፍ​ራ​ውን በሥጋ መላው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ከአ​ዳም የወ​ሰ​ዳ​ትን አጥ​ንት ሴት አድ​ርጎ ሠራት፤ ወደ አዳ​ምም አመ​ጣት። ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥ​ንት ከአ​ጥ​ንቴ ናት፤ ሥጋ​ዋም ከሥ​ጋዬ ናት፤ እር​ስዋ ከባ​ልዋ ተገ​ኝ​ታ​ለ​ችና ሚስት ትሁ​ነኝ።” ስለ​ዚህ ሰው አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ሚስ​ቱ​ንም ይከ​ተ​ላል ፤ ሁለ​ቱም አንድ ሥጋ ይሆ​ናሉ። አዳ​ምና ሚስ​ቱም ዕራ​ቁ​ታ​ቸ​ውን ነበሩ፤ አይ​ተ​ፋ​ፈ​ሩም ነበር።

ዘፍጥረት 2:1-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የሰማያትና የምድር፣ በውስጣቸውም ያሉት ሁሉ አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ። እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራውን በሰባተኛው ቀን ላይ ፈጽሞ ነበር፤ ስለዚህ ይሠራ ከነበረው ሥራው ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ። እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም፤ ካከናወነው የመፍጠር ሥራው ሁሉ ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነውና። እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ የተከናወኑት እንደዚህ ነበረ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን ሲፈጥር፣ የሜዳ ቡቃያ ገና በምድር ላይ አልታየም፤ የሜዳ ተክልም ገና አልበቀለም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክ በመሬት ላይ ገና ዝናብ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚያለማ ሰው አልነበረም። ነገር ግን ውሃ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር። እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ። እግዚአብሔር አምላክ በምሥራቅ፣ በዔድን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፤ ያበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው። እግዚአብሔር አምላክም ለዐይን የሚያስደስት ለመብልም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በአትክልቱ ቦታ መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም መልካምና ክፉን መለየት የሚያስችለው የዕውቀት ዛፍ ነበረ። የአትክልት ስፍራውን የሚያጠጣ ወንዝ ከዔድን ይፈስስ ነበር፤ ከዚያም በአራት ተከፍሎ ይወጣ ነበር። የመጀመሪያው፣ ወርቅ በሚገኝበት በኤውላጥ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የፊሶን ወንዝ ነው። ኤውላጥ ምርጥ የሆነ ወርቅ፣ መልካም መዐዛ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ የሚገኙበት ምድር ነው። ሁለተኛው፣ በኢትዮጵያ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የግዮን ወንዝ ነው። ሦስተኛው፣ ከአሦር በስተምሥራቅ የሚፈስሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን፣ አራተኛው የኤፍራጥስ ወንዝ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወስዶ እንዲያለማትና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት በዔድን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው። እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ በማለት አዘዘው፤ “በአትክልት ስፍራው ውስጥ ከሚገኝ ከማንኛውም ዛፍ ፍሬ ትበላለህ። ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ምክንያቱም ከርሱ በበላህ ቀን በርግጥ ትሞታለህ።” ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ፣ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ” አለ። እግዚአብሔር አምላክ የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጥረታት ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ። ስለዚህ አዳም ለከብቶች፣ ለሰማይ ወፎች፣ ለዱር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው። ይሁን እንጂ ለአዳም ተስማሚ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐድኑ አንዲት ዐጥንት ወስዶ፣ ስፍራውን በሥጋ ሞላው። እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም የወሰዳትን ዐጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት። ከወንድ ተገኝታለችና ‘ሴት’ ትባል።” ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋራ ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። አዳምና ሚስቱ፣ ሁለቱም ዕራቍታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።

ዘፍጥረት 2:1-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሰማይና ምድር ሠራዊታቸዉም ሁሉ ተፈጸመ። እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኚው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኚውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። ፈጸመ፤ በሰባተኚውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። እግዚአብሔርም ሰባተኚውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረዉ ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና። እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ አምላክ ሰማይንና ምድርን ቀን፤ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው። የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልነበረም ነበር፤ እግዚአብሔር አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፤ ምድርም የሚሠራባት በምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፤ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም፤ ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፤ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር። እግዚአብሔር አምላክም ሰውንም ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ። እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው። እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያስኘውን፤ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፤ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ። ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ከአራት ክፍል ይከፈል ነበር። የአንደኚው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው። ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኚል። የሁለተኚውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል። የሦስተኚውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው። አራተኚውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገንት አኖረው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፤ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። እግዚእብሔር አምላክም አለ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረት እንፍጠርለት። እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎእን ሁሉ ከመሬት አደረገ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ እዳምም ሕያው ነፍስ ልስለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠርው ስሙ ያው ሆነ። አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፤ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፤ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላአው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፤ አንቀላዳም ከጎኑም አንዲት እጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚእብሔር አምልስክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም አለ፤ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፤ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰዉ አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ በሚስቱም ይጣበቃ፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፤ አይተፋፈሩም ነበር።

ዘፍጥረት 2:1-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የሰማይና የምድር፥ በውስጣቸው ያሉትም ነገሮች ሁሉ አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተፈጸመ። እግዚአብሔር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ። እግዚአብሔር የመፍጠር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ ያረፈው በዚህ ቀን ስለ ሆነ፥ ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም። የሰማይና የምድር አፈጣጠር እንዲህ ነበር። እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ፥ ዝናብን ባለማዝነቡና ምድርንም የሚያለማ ሰው ባለመኖሩ፥ በምድር ላይ ምንም ዐይነት ተክል አልነበረም፤ ምንም ዐይነት ቡቃያ አልበቀለም። ይሁን እንጂ፥ ከምድር ውስጥ ምንጭ ፈልቆ የብሱን ሁሉ ያጠጣ ነበር። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ። እግዚአብሔር አምላክ በስተምሥራቅ በኩል በዔደን የአትክልት ቦታን አዘጋጀ፤ የፈጠረውንም ሰው በዚያ እንዲኖር አደረገው። በዚያም ለዐይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ፤ ደግሞም በአትክልቱ ቦታ መካከል ሕይወት የሚሰጥ ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት የሚሰጥ ሌላ ዛፍ ነበረ። የአትክልት ቦታውን የሚያጠጣ ወንዝ ከዔደን ይፈስ ነበር፤ ይህም ወንዝ ከዔደን ከወጣ በኋላ በአራት ወንዞች ይከፈላል። የመጀመሪያው ወንዝ ፊሶን ይባላል፤ እርሱም ወርቅ በሚገኝበት ሐዊላ በሚባለው ምድር ሁሉ ላይ ይፈስሳል፤ የዚያ አገር ወርቅ ንጹሕ ነበር፤ በተጨማሪም በዚያ አገር ውድ የሆነ ሽቶና የከበሩ ድንጋዮች ይገኛሉ። ሁለተኛው ወንዝ ግዮን ይባላል፤ እርሱም ኢትዮጵያ በምትባል አገር ዙሪያ ይፈስሳል። ሦስተኛው ወንዝ ጤግሮስ ይባላል፤ እርሱም በአሦር በስተምሥራቅ ይፈስሳል፤ አራተኛው ወንዝ ኤፍራጥስ ይባላል። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በዔደን የአትክልት ቦታ አኖረው፤ ይህንንም ያደረገው ሰው የአትክልቱን ቦታ እንዲያለማና እንዲንከባከበው ነው። እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “በአትክልቱ ቦታ ከሚገኙት ዛፎች ሁሉ ፍሬ ልትበላ ትችላለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ በበላህበት ቀን በእርግጥ ስለምትሞት ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት ከሚሰጠው ዛፍ ፍሬ አትብላ።” ቀጥሎም እግዚአብሔር አምላክ “ሰው ብቻውን መኖሩ መልካም አይደለም፤ ስለዚህ ረዳት ጓደኛ እፈጥርለታለሁ” አለ። እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ እንስሶችንና ወፎችን ሁሉ ፈጠረ፤ ምን ዐይነት ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳም ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ያወጣለት ስም መጠሪያው ሆነ። በዚህ ዐይነት አዳም ለወፎቹና ለእንስሶቹ ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ለእርሱ ግን ረዳት ጓደኛ አልተገኘለትም ነበር። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐኑ አጥንቶች አንዱን ወሰደና ባዶውን ቦታ በሥጋ ሞላው፤ እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም ጐን የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም፥ “እነሆ በመጨረሻ እርስዋ ከአጥንቶቼ የተገኘች አጥንት ናት፤ ከሥጋዬም የተገኘች ሥጋ ናት፤ ከወንድ የተገኘች ስለ ሆነች ‘ሴት’ ትባል” አለ። ስለዚህ ወንድ አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይተባበራል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ። አዳምና ሚስቱ ራቊታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አያፍሩም ነበር።

ዘፍጥረት 2:1-25 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሰማያትና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ እነሆ ተፈጸሙ። እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፥ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና፥ ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም። ጌታ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን፥ የሰማያትና ምድር ልደት፥ በተፈጠሩበት ጊዜ፥ እንዲህ ነበር። የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ከመኖሩ በፊት፥ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ከመብቀሉ በፊት፥ ጌታ እግዚአብሔር በምድር ላይ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም። ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር። ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ። ጌታ እግዚአብሔርም፥ በስተ ምሥራቅ፥ በዔድን ገነትን ተከለ፤ የፈጠረውንም ሰው ከዚያ አኖረው። በዚያም፥ ጌታ እግዚአብሔር ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፥ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ። ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፥ ይህም ወንዝ ከዔደን ከወጣ በኋላ በአራት ወንዞች ይከፈላል። የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፥ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የሐዊላን ምድር ይከብባል፥ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፥ ሉልና የከበረም ድንጋይ በዚያ ይገኛል። የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፥ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል። የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፥ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው። አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። ጌታ እግዚአብሔርም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔደን ገነት አኖረው። ከዚያም ጌታ እግዚአብሔር ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፥ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” ጌታ እግዚእብሔርም፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ የምትሆነውን ረዳት እፈጥርለታለሁ” አለ። የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ፥ ጌታ እግዚአብሔር፥ ከምድር ፈጠረ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፥ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ። አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፥ ነገር ግን አዳም ለእርሱ ሁነኛ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። ጌታ እግዚአብሔርም አዳምን ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጎኑ አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። ከአዳም የወሰዳትንም አጥንት፥ ጌታ እግዚእብሔር፥ ሴት አድርጎ ሠራት፥ ወደ አዳምም አመጣለት። አዳምም አለ፥ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ የተገኘች ናት፥ ከሥጋዬም የተገኘች ሥጋ ናት፤ ሴት ተብላ ትጠራ፥ ከወንድ የተገኘች ስለ ሆነች ‘ሴት’ ትባል” አለ። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይተባበራል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ። አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩምም ነበር።