ዘፍጥረት 19:1-38
ዘፍጥረት 19:1-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰዶም ከተማ መግቢያ በር ተቀምጦ ነበር፤ ሎጥም መላእክቱን ሲያይ ሊቀበላቸው ብድግ አለ፤ በግንባሩም ወደ ምድር ተደፍቶ እጅ ነሣቸው። እርሱም፣ “ጌቶቼ፤ እባካችሁ ወደ እኔ ወደ ባሪያችሁ ቤት ጎራ በሉ፤ ከዚያም እግራችሁን ታጠቡ፤ ዐድራችሁም ጧት በማለዳ ጕዟችሁን ትቀጥላላችሁ” አላቸው። እነርሱም፣ “አይሆንም፤ እዚሁ አደባባይ ላይ እናድራለን” አሉት። ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው ዐብረውት ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸውና በሉ። ከመተኛታቸውም በፊት፣ የሰዶም ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወንድ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከየአካባቢው መጥተው ቤቱን ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው፣ “በዚህች ምሽት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን” አሉት። ሎጥም ሊያነጋግራቸው ወደ ውጭ ወጣ፤ መዝጊያውን ከበስተኋላው ዘግቶ፣ እንዲህ አለ፤ “ወዳጆቼ ሆይ፤ እባካችሁ እንዲህ ያለውን ክፉ ነገር አታድርጉ። እነሆ፤ ወንድ የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ። እነርሱን ላውጣላችሁና የፈለጋችሁትን አድርጉባቸው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ግን አንዳች ነገር አታድርጉባቸው፤ እኔን ብለው ወደ ቤቴ ገብተዋልና።” እነርሱም፣ “ዞር በል! ይህ ሰው ራሱ ትናንት ተሰድዶ የመጣ ነው፤ ዛሬ ደግሞ ዳኛ ልሁን ይላል። ዋ! በእነርሱ ካሰብነው የከፋ እንዳናደርስብህ!” አሉት፤ ከዚያም ሎጥን እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተንደረደሩ። ከቤቱ ውስጥ የነበሩት እንግዶች ግን እጃቸውን በመዘርጋት ሎጥን ስበው ወደ ውስጥ አስገቡት፤ በሩንም ዘጉ። ከዚያም በሩን እንዳያገኙት በቤቱ ደጃፍ ላይ የተሰበሰቡትን ወጣቶችና ሽማግሌዎች ዐይን አሳወሩ። ሁለቱ ሰዎችም ሎጥን እንዲህ አሉት፤ “በከተማዪቱ ውስጥ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ዐማቾች፣ ወንዶችና ሴቶች ወይም ሌሎች ዘመዶች ካሉህ ቶሎ ብለህ ከዚህ እንዲወጡ አድርግ፤ ይህን ስፍራ ልናጠፋው ነው። በሕዝቦቿ ላይ ወደ እግዚአብሔር የቀረበው ጩኸት ታላቅ በመሆኑ፣ እንድናጠፋት እግዚአብሔር ልኮናል።” ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹ እጮኞች የሆኑትን ዐማቾቹን፣ “እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ሊያጠፋት ነውና በፍጥነት ከዚህ ስፍራ ውጡ” አላቸው፤ ዐማቾቹ ግን የሚቀልድ መሰላቸው። ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥን፣ “ከከተማዪቱ ጋራ ዐብራችሁ እንዳትጠፉ፣ ሚስትህንና ሁለቱን ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ” ብለው አቻኰሉት። ሎጥ ሲያመነታም፣ እግዚአብሔር ስለ ራራላቸው ሰዎቹ የርሱን፣ የሚስቱንና የሁለት ሴቶች ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዪቱ በደኅና አወጧቸው። እንዳወጧቸውም፣ መልአኩ፣ “ሕይወታችሁን ለማትረፍ ፈጥናችሁ ሽሹ፤ መለስ ብላችሁ ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ከረባዳው ስፍራ እንኳ ቆም አትበሉ፤ ወደ ተራራው ሽሹ፤ አለዚያ ትጠፋላችሁ” አላቸው። ሎጥም እንዲህ አላቸው፤ “ጌቶቼ ሆይ፤ እባካችሁ እንደዚህስ አይሁን፤ እነሆ፤ እኔ ባሪያህ አንዴ በፊትህ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርገህልኛል፤ እኔ እንደ ሆንሁ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል። እነሆ፤ ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ የሆነች ትንሽ ከተማ አለች፤ ወደ እርሷ ልሽሽ፤ በጣም ትንሽ አይደለችም እንዴ? ወደዚያ ብሸሽ እኮ ሕይወቴ ትተርፋለች።” እርሱም እንዲህ አለው፤ “ይሁን ዕሺ፣ ልመናህን ተቀብያለሁ፤ ያልካትንም ከተማ አላጠፋትም። አንተ እዚያ እስክትደርስ ድረስ አንዳች ማድረግ ስለማልችል ቶሎ ብለህ ወደዚያ ሽሽ።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ። ሎጥ ዞዓር ሲደርስ ፀሓይ በምድሩ ላይ ወጥታ ነበር። ከዚያም እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ላይ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያቃጥል ዲንና እሳት አዘነበባቸው። እነዚያንም ከተሞችና ረባዳውን ምድር በሙሉ፣ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ፣ የምድሩን ቡቃያ ሳይቀር ገለባበጠው። የሎጥ ሚስት ግን ወደ ኋላዋ ስለ ተመለከተች የጨው ዐምድ ሆና ቀረች። አብርሃም በማግስቱም፣ ማለዳ ተነሥቶ ከዚህ ቀደም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ። ሰዶምንና ገሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የሚገኘውን ምድር ሁሉ ቍልቍል ተመለከተ፤ ከእቶን የሚወጣ የመሰለ ጥቅጥቅ ያለ ጢስ ከምድሪቱ ወደ ላይ ሲትጐለጐል አየ። እንደዚህ አድርጎ እግዚአብሔር በረባዳው ስፍራ የነበሩትን ከተሞች ሲያጠፋ አብርሃምን ዐሰበው፤ ስለዚህም የሎጥ መኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ካጠፋው መዓት ሎጥን አወጣው። ሎጥ በዞዓር መኖርን ስለ ፈራ፣ ከዚያ ተነሥቶ ከሁለቱ ሴት ልጆቹ ጋራ በአቅራቢያው ወደሚገኙት ተራሮች ሄደ፤ መኖሪያውንም ከሁለት ሴት ልጆቹ ጋራ በዋሻ ውስጥ አደረገ። አንድ ቀን ታላቂቱ ልጅ፣ ታናሺቱን እንዲህ አለቻት፤ “አባታችን አርጅቷል፤ በምድር ሁሉ እንደሚኖሩ ሰዎች ወግ ዐብሮን የሚተኛ ወንድ በአካባቢያችን የለም። ስለዚህ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከርሱ ጋራ እንተኛ፤ የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ዘር ከአባታችን እናትርፍ።” በዚያችም ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ከዚያም ትልቋ ልጁ ሄዳ ከአባቷ ጋራ ተኛች፤ እርሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም ነበር። በማግስቱም ታላቂቱ ልጅ ታናሺቱን፣ “እኔ ትናንትና ማታ ከአባቴ ጋራ ተኝቻለሁ፤ ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፤ አንቺም ደግሞ ከርሱ ዘንድ ገብተሽ ተኚ፤ በዚህም የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር ማትረፍ እንችላለን” አለቻት። በዚያችም ምሽት ደግሞ አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ትንሿ ልጁም ሄዳ ከአባቷ ጋራ ተኛች፤ እርሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም ነበር። ስለዚህ ሁለቱም የሎጥ ሴት ልጆች ከአባታቸው አረገዙ። ትልቋ ልጁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ እርሱም የዛሬዎቹ ሞዓባውያን አባት ነው። ትንሿ ልጁም እንደዚሁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ ብላ ጠራችው፤ እርሱም የዛሬዎቹ አሞናውያን አባት ነው።
ዘፍጥረት 19:1-38 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰዶም ከተማ በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ወደ ምድር ደፍቶ ሰገደላቸው፤ አላቸውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት ገብታችሁ እደሩ፤ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገም ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት። እርሱም ግድ አላቸው፤ ወደ እርሱም አቀኑ፤ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ቂጣንም አስጋገረላቸው፤ እነርሱም በሉ። ገና ሳይተኙም የዚያች ከተማ ሰዎች፥ ታናሹም፥ ታላቁም ቤቱን በአንድነት ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፥ “በሌሊት ወደ አንተ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።” ሎጥም ወደ እነርሱ ወደ ደጅ ፊት ለፊት ወጣ፤ መዝጊያውንም በስተኋላው ዘጋው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ወንድሞች ሆይ፥ ለእናንተ አግባባችሁ አይደለም፤ በእነዚህ ላይ ክፉ አታድርጉ፤ እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፤ እንደ ወደዳችሁም አድርጉአቸው፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም በደል አታድርጉ፤ እነርሱ በቤቴ ጥላ ሥር ገብተዋልና።” እነርሱም፥ “ወዲያ ሂድ፤ ከእኛ ጋር ልትኖር መጣህ እንጂ ልትገዛን አይደለም፤ አሁንም ከእነርሱ ይልቅ አንተን እናሠቃይሃለን” አሉት። እጅግም ተጋፉት፤ የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ። እነዚያም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት ስበው አገቡት፤ መዝጊያውንም ዘጉት። በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስክ ታላቃቸው ድረስ ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ ደጃፉንም ሲፈልጉ ደከሙ፤ አጡትም። እነዚያም መላእክት ሎጥን አሉት፥ “ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን፥ ወንድ ልጅም ቢሆን፥ ሴት ልጅም ብትሆን፥ በዚህ ከተማ የምታውቀው ወዳጅ ቢኖርህ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸው፤ እኛ ይህችን ስፍራ እናጠፋታለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፤ እናጠፋትም ዘንድ እግዚአብሔር ልኮናል።” ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው። ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ “ተነሣ፤ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፤ አንተም በከተማዪቱ ሰዎች ኀጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር። እርሱም በዘገየ ጊዜ እነዚያ መላእክት የእርሱን እጅ፥ የሚስቱንም እጅ፥ የሁለቱን ሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ራርቶላቸዋልና። ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፥ “ራስህን አድን፤ ወደ ኋላም አትመልከት፤ አንተንም መከራ እንዳታገኝህ በዚች ሀገር በዳርቻዋና በተራራዋ አትቁም።” ሎጥም አላቸው፥ “ጌቶች ሆይ፥ በጀ በሉኝ፤ እነሆ፥ ባሪያህ በፊትህ ምሕረትን አግኝቼ እንደሆነ፥ ሰውነቴንም ታድናት ዘንድ፥ ቸርነትህን አብዝተህልኝ እንደ ሆነ፥ መከራ አግኝቶኝ እንዳልጠፋ ወደ ተራራ ሸሽቼ ራሴን ማዳን አልችልም። እነሆ፥ ይህች ከተማ ወደ እርስዋ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ናት፤ እርስዋም ትንሽ ናት፤ ነፍሴን ለማዳን ወደ እርስዋ ሸሽቼ ራሴን ላድን፤ ሰውነቴም ከዳነች ትንሽ አይደለችም፤” እርሱም አለው፥ “ስለ እርስዋ የነገርኸኝን ያችን ከተማ እንዳላጠፋት እነሆ፥ እንዳልኸው ልመናህን ተቀብዬሃለሁ፤ እንግዲህ ፍጠንና በዚያ ራስህን አድን፤ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ። ፀሐይ በምድር ላይ ወጣች፤ ሎጥም ወደ ሴጎር ገባ። እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤ እነዚያንም ከተሞች፥ በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞችም የሚኖሩትን ሁሉ፥ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ። የሎጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመለከተች፤ የጨው ሐውልትም ሆነች። አብርሃምም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ስፍራ ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፤ ወደ ሰዶምና ገሞራ፥ ወደ አውራጃዎችዋም ሁሉ ተመለከተ፤ እነሆም፥ ነበልባል ከምድር እንደ ምድጃ ጢስ ሲወጣ አየ። እግዚአብሔርም እነዚያን ከተሞችና ሎጥ የሚኖርባቸውን አውራጃዎችዋን ሁሉ ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን ዐሰበው፤ ሎጥንም ከጥፋት መካከል አወጣው። ሎጥም ከሴጎር ወጣ፤ ከሁለቱም ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ፤ በሴጎር መቀመጥን ፈርቶአልና እርሱና ሁለቱ ሴቶች ልጆቹ በዋሻ ተቀመጡ። ታላቂቱም ታናሺቱን አለቻት፥ “አባታችን ሽማግሌ ነው፤ በምድርም ሁሉ እንዳለው ልማድ ሊገናኘን የሚችል ሰው በምድር ላይ የለም። ነዪ፥ አባታችንን ወይን እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፤ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” በዚያችም ሌሊት አባታቸውን ወይን አጠጡት፤ ታላቂቱም ገባች፤ በዚያችም ሌሊት ከአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛም፥ ስትነሣም አላወቀም። በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፥ “እነሆ፥ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፤ ዛሬ ሌሊት ደግሞ ወይን እናጠጣው፤ አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፤ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ ወይን አጠጡት፤ ታናሺቱም ገብታ ከአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛም ስትነሣም አላወቀም። የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ ይህም ከአባቴ የወለድሁት ማለት ነው። እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው። ታናሺቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም የወገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራችው፤ እርሱም እስከ ዛሬ የአሞናውያን አባት ነው።
ዘፍጥረት 19:1-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰዶም ከተማ መግቢያ በር ተቀምጦ ነበር፤ ሎጥም መላእክቱን ሲያይ ሊቀበላቸው ብድግ አለ፤ በግንባሩም ወደ ምድር ተደፍቶ እጅ ነሣቸው። እርሱም፣ “ጌቶቼ፤ እባካችሁ ወደ እኔ ወደ ባሪያችሁ ቤት ጎራ በሉ፤ ከዚያም እግራችሁን ታጠቡ፤ ዐድራችሁም ጧት በማለዳ ጕዟችሁን ትቀጥላላችሁ” አላቸው። እነርሱም፣ “አይሆንም፤ እዚሁ አደባባይ ላይ እናድራለን” አሉት። ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው ዐብረውት ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸውና በሉ። ከመተኛታቸውም በፊት፣ የሰዶም ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወንድ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከየአካባቢው መጥተው ቤቱን ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው፣ “በዚህች ምሽት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን” አሉት። ሎጥም ሊያነጋግራቸው ወደ ውጭ ወጣ፤ መዝጊያውን ከበስተኋላው ዘግቶ፣ እንዲህ አለ፤ “ወዳጆቼ ሆይ፤ እባካችሁ እንዲህ ያለውን ክፉ ነገር አታድርጉ። እነሆ፤ ወንድ የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ። እነርሱን ላውጣላችሁና የፈለጋችሁትን አድርጉባቸው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ግን አንዳች ነገር አታድርጉባቸው፤ እኔን ብለው ወደ ቤቴ ገብተዋልና።” እነርሱም፣ “ዞር በል! ይህ ሰው ራሱ ትናንት ተሰድዶ የመጣ ነው፤ ዛሬ ደግሞ ዳኛ ልሁን ይላል። ዋ! በእነርሱ ካሰብነው የከፋ እንዳናደርስብህ!” አሉት፤ ከዚያም ሎጥን እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተንደረደሩ። ከቤቱ ውስጥ የነበሩት እንግዶች ግን እጃቸውን በመዘርጋት ሎጥን ስበው ወደ ውስጥ አስገቡት፤ በሩንም ዘጉ። ከዚያም በሩን እንዳያገኙት በቤቱ ደጃፍ ላይ የተሰበሰቡትን ወጣቶችና ሽማግሌዎች ዐይን አሳወሩ። ሁለቱ ሰዎችም ሎጥን እንዲህ አሉት፤ “በከተማዪቱ ውስጥ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ዐማቾች፣ ወንዶችና ሴቶች ወይም ሌሎች ዘመዶች ካሉህ ቶሎ ብለህ ከዚህ እንዲወጡ አድርግ፤ ይህን ስፍራ ልናጠፋው ነው። በሕዝቦቿ ላይ ወደ እግዚአብሔር የቀረበው ጩኸት ታላቅ በመሆኑ፣ እንድናጠፋት እግዚአብሔር ልኮናል።” ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹ እጮኞች የሆኑትን ዐማቾቹን፣ “እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ሊያጠፋት ነውና በፍጥነት ከዚህ ስፍራ ውጡ” አላቸው፤ ዐማቾቹ ግን የሚቀልድ መሰላቸው። ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥን፣ “ከከተማዪቱ ጋራ ዐብራችሁ እንዳትጠፉ፣ ሚስትህንና ሁለቱን ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ” ብለው አቻኰሉት። ሎጥ ሲያመነታም፣ እግዚአብሔር ስለ ራራላቸው ሰዎቹ የርሱን፣ የሚስቱንና የሁለት ሴቶች ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዪቱ በደኅና አወጧቸው። እንዳወጧቸውም፣ መልአኩ፣ “ሕይወታችሁን ለማትረፍ ፈጥናችሁ ሽሹ፤ መለስ ብላችሁ ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ከረባዳው ስፍራ እንኳ ቆም አትበሉ፤ ወደ ተራራው ሽሹ፤ አለዚያ ትጠፋላችሁ” አላቸው። ሎጥም እንዲህ አላቸው፤ “ጌቶቼ ሆይ፤ እባካችሁ እንደዚህስ አይሁን፤ እነሆ፤ እኔ ባሪያህ አንዴ በፊትህ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርገህልኛል፤ እኔ እንደ ሆንሁ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል። እነሆ፤ ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ የሆነች ትንሽ ከተማ አለች፤ ወደ እርሷ ልሽሽ፤ በጣም ትንሽ አይደለችም እንዴ? ወደዚያ ብሸሽ እኮ ሕይወቴ ትተርፋለች።” እርሱም እንዲህ አለው፤ “ይሁን ዕሺ፣ ልመናህን ተቀብያለሁ፤ ያልካትንም ከተማ አላጠፋትም። አንተ እዚያ እስክትደርስ ድረስ አንዳች ማድረግ ስለማልችል ቶሎ ብለህ ወደዚያ ሽሽ።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ። ሎጥ ዞዓር ሲደርስ ፀሓይ በምድሩ ላይ ወጥታ ነበር። ከዚያም እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ላይ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያቃጥል ዲንና እሳት አዘነበባቸው። እነዚያንም ከተሞችና ረባዳውን ምድር በሙሉ፣ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ፣ የምድሩን ቡቃያ ሳይቀር ገለባበጠው። የሎጥ ሚስት ግን ወደ ኋላዋ ስለ ተመለከተች የጨው ዐምድ ሆና ቀረች። አብርሃም በማግስቱም፣ ማለዳ ተነሥቶ ከዚህ ቀደም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ። ሰዶምንና ገሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የሚገኘውን ምድር ሁሉ ቍልቍል ተመለከተ፤ ከእቶን የሚወጣ የመሰለ ጥቅጥቅ ያለ ጢስ ከምድሪቱ ወደ ላይ ሲትጐለጐል አየ። እንደዚህ አድርጎ እግዚአብሔር በረባዳው ስፍራ የነበሩትን ከተሞች ሲያጠፋ አብርሃምን ዐሰበው፤ ስለዚህም የሎጥ መኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ካጠፋው መዓት ሎጥን አወጣው። ሎጥ በዞዓር መኖርን ስለ ፈራ፣ ከዚያ ተነሥቶ ከሁለቱ ሴት ልጆቹ ጋራ በአቅራቢያው ወደሚገኙት ተራሮች ሄደ፤ መኖሪያውንም ከሁለት ሴት ልጆቹ ጋራ በዋሻ ውስጥ አደረገ። አንድ ቀን ታላቂቱ ልጅ፣ ታናሺቱን እንዲህ አለቻት፤ “አባታችን አርጅቷል፤ በምድር ሁሉ እንደሚኖሩ ሰዎች ወግ ዐብሮን የሚተኛ ወንድ በአካባቢያችን የለም። ስለዚህ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከርሱ ጋራ እንተኛ፤ የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ዘር ከአባታችን እናትርፍ።” በዚያችም ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ከዚያም ትልቋ ልጁ ሄዳ ከአባቷ ጋራ ተኛች፤ እርሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም ነበር። በማግስቱም ታላቂቱ ልጅ ታናሺቱን፣ “እኔ ትናንትና ማታ ከአባቴ ጋራ ተኝቻለሁ፤ ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፤ አንቺም ደግሞ ከርሱ ዘንድ ገብተሽ ተኚ፤ በዚህም የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር ማትረፍ እንችላለን” አለቻት። በዚያችም ምሽት ደግሞ አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ትንሿ ልጁም ሄዳ ከአባቷ ጋራ ተኛች፤ እርሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም ነበር። ስለዚህ ሁለቱም የሎጥ ሴት ልጆች ከአባታቸው አረገዙ። ትልቋ ልጁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ እርሱም የዛሬዎቹ ሞዓባውያን አባት ነው። ትንሿ ልጁም እንደዚሁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ ብላ ጠራችው፤ እርሱም የዛሬዎቹ አሞናውያን አባት ነው።
ዘፍጥረት 19:1-38 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ አለቸውም ጌቶቼ ሆይ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ ከዚያም እደሩ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁም ትሄዳላችሁ። እነርሱም፤ በአደባባዩ እናድራለን እንጂ አይሆንም አሉት። እጅግም ዘበዝባቸው ወደ እርሱም አቀኑ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ። ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ ቤቱን ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፤ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናችው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው። ሎጥም ወደ እነርሱ ወደ ደጅ ወጣ መዝጊያውንም በኍላው ዘጋው እንዲህም አለ፤ ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ እነሆ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ እነርሱን ላውጣላች እንደ ወደዳችሁም አደርጓቸው በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና። እነርሱም፤ ወዲያ ሂድ አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ፤ ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን። ሎጥንም እጅግ ተጋፉት የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ። ሁለቱም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት። በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታለቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው ደጃፉንም ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ። ሁለቱም ሰዎች ሎጥን አሉት ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን ውንድ ልጅም ቢሆን ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ ብትሆን በከተማይቱ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸ እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል። ሎጥ፥ ወጣ ልጆቹም ለሚያገቡት ለአማቶቹም ነገራቸው አላቸውም፥ ተነሡ ከዚህ ስፍራ ውጡ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። ለአማቶቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ ተነሣ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውስድ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፉ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር። እርሱም በዘገያ ጊዜ እግዚአብሔር ስላዘነለት እነዚያ ስዎች የእርሱን እጅ የሚስቱን፥ እጅ የሁለቱን የሴትፕች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡትና በከተማይቱ ውጭ አስቀመጡት። ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኍላ እንዲህ አለው ራስህን አድን ወደ ኍላህ አትይ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ። ሎጥም አላቸው ጌቶቼ ሆይ እንዲህስ አይሁን እነሆ ባሪያህ በፊትህ ሞገስን አግኝቶአል ነፍሴን ለማዳን ያደረግህልኝን ምሕረትህንም አብዝተሃል ክፋ እንዳያጋኘኝና እንዳልሞት ወደ ተራራ ሸሽቼ አመልጥ ዘንድ አልችልም እነሆ ይህች ከተማ ወደ እርስዋ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ናት እርስዋም ትንሽ ናት ነፍሴን ለማዳን ወደ እርስዋ ሸሽቼ ላምልጥ እርስዋ ትንሽ ከተም አይደለችምን? እርሱም አለው፤ የተናገርሃትን ከተማ እንዳላጠፋት እነሆ በዚህ ነገር የለመንኸኝን ተቀብዬሃለሁ፤ በቶሎ ወደዚያ ሸሽትህ አምልጥ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና። ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ። ሎጥ ወደ ዞዓር በገብ ጊዜ ፀሐይ በምድር ላይ ወጣች። እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤ እነዚያንም ከተሞች በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ። የሎጥም ሚስት ወደ ኍላዋ ተመለከተች የጨው ሐውልት፥ ሆነች። አብርሃምም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ስፍራ ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ በዚያች አገር ወዳላውም ምድር ሁሉ ተመለከት እነሆም የአገሪቱ ጢስ እንድ እቶን ጢስ ሲነሣ አየ። እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፤ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚይ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው። ሎጥም ከዞዓር ወጣ በዞዓር ይቀመጥ ዘንድ ስል ፈራም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ። ታላቂቱም ታናሺቱን አለቻት፤ አባታችን ሸመገለ በምድርም ሁሉ እንዳለው ልማድ ሊገናኘን የሚችል ሰው ከምድር ላይ የለም ነዩ አባታቻንንም የወይን ጠጅ እንጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ ከአባታችንም ዘር እንስቀር። በዚያችም ሌሊት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት ታላቂቱም ገባች፥ ከአባትዋ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፤ እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ ከአባታችንም ዘር እናስቀር። አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ አጠጡት ታናሺቱም ገብታ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። ታላቂቱም ውንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው። ታናሺቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም፤ የወገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራችው እርሱም እስከ ዛሬ የአሞናውያን አባት ነው።
ዘፍጥረት 19:1-38 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በዚያኑ ምሽት ሁለቱ መላእክት ወደ ሰዶም መጡ፤ በዚያን ጊዜ ሎጥ በከተማይቱ በር ተቀምጦ ነበር፤ መላእክቱን ባያቸው ጊዜ ሊያነጋግራቸው ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሄደ፤ ጐንበስ ብሎም እጅ ነሣቸውና፥ “ጌቶቼ ሆይ፥ ተቀብዬ ላስተናግዳችሁ ዝግጁ ነኝ፤ እባካችሁ ወደ ቤቴ ግቡ፤ እግራችሁንም ታጥባችሁ እዚሁ ዕደሩ፤ ጠዋት በማለዳ ተነሥታችሁ ጒዞአችሁን ትቀጥላላችሁ” አላቸው። እነርሱ ግን “አይሆንም፤ እኛ እዚሁ በከተማይቱ አደባባይ እናድራለን” አሉት። ነገር ግን ወደ ቤቱ እንዲገቡ አጥብቆ ስለ ለመናቸው፥ ከእርሱ ጋር ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚህም በኋላ ሎጥ እንጀራ ጋግረው መልካም ራት እንዲያዘጋጁ ለአገልጋዮቹ ነገራቸው፤ ራትም በተዘጋጀ ጊዜ እንግዶቹ በሉ። እንግዶቹ ከመተኛታቸው በፊት የሰዶም ሰዎች ቤቱን ከበቡት፤ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ሳይቀሩ የከተማይቱ ወንዶች ሁሉ እዚያ ተሰበሰቡ። ሎጥንም ጠርተው “ከአንተ ጋር ለማደር ወደዚህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ስለምንፈልግ ወደ እኛ አውጣቸው!” አሉት። ሎጥ ግን ወደ ውጪ ወጥቶ በሩን ከበስተኋላው ዘጋው፤ እንዲህም አላቸው “ወዳጆቼ ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ! እነሆ፥ ሁለት ያላገቡ ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ወደ እናንተ ላምጣላችሁና በእነርሱ ላይ የፈለጋችሁትን ነገር አድርጉ፤ በእነዚህ ሰዎች ግን ምንም ነገር አታድርጉ፤ እነርሱ የእኔ እንግዶች ስለ ሆኑ ልጠነቀቅላቸው ይገባኛል።” ሰዎቹ ግን “አንተ ስደተኛ፥ ሂድ ወዲያ! ለመሆኑ ልናደርገው የሚገባንን ነገር የምትነግረን አንተ ማን ነህ? ሂድ ወዲያ፤ አለበለዚያ በእነርሱ ላይ ልናደርግ ካሰብነው የከፋ ነገር በአንተ ላይ እናደርጋለን” አሉት። በዚህ ዐይነት ሎጥን ወዲያ ገፍትረው በሩን ለመስበር ተነሣሡ፤ ከቤቱ ውስጥ ያሉት ሁለቱ እንግዶች ግን እጆቻቸውን ወደ ውጪ አውጥተው ሎጥን ስበው ወደ ቤቱ ውስጥ አስገቡትና በሩን ዘጉ። ከዚያ በኋላ ውጪ የነበሩት ወጣቶችና ሽማግሌዎች ሁሉ በሩን ማየት እንዳይችሉ ዐይናቸውን አሳወሩአቸው። ሁለቱም እንግዶች ሎጥን እንዲህ አሉት፤ “በዚህች ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ የልጆችህ እጮኛዎችና ሌሎች ዘመዶች ቢኖሩህ ከዚህች ከተማ በፍጥነት እንዲወጡ አድርግ፤ ይህችን ከተማ ልናጠፋት ነው፤ የእነዚህ ሰዎች ኃጢአት እጅግ መብዛቱን እግዚአብሔር ሰምቶአል፤ ሰዶምንም እንድናጠፋ ልኮናል።” ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ። በማግስቱ ጠዋት በማለዳ መላእክቱ ሎጥን “ፍጠን! ከተማይቱ ስትጠፋ አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ውጣ” እያሉ አጣደፉት። ሎጥ ግን አመነታ፤ ሆኖም እግዚአብሔር ለእርሱና ለቤተሰቡ ስለ ራራ መላእክቱ ሎጥንና ሚስቱን፥ ሁለቱን ሴቶች ልጆቹን፥ እጆቻቸውን ይዘው ከከተማዋ እንዲያወጡአቸው አደረገ። ካወጡአቸውም በኋላ ከመላእክቱ አንዱ “ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ! በሸለቆው ውስጥ አትዘግዩ፤ እንዳትሞቱ ወደ ተራራው ሽሹ!” አላቸው። ሎጥ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ጌቶቼ፥ እባካችሁ ወደዚያ እንድንወጣ አታደርጉ፤ እኔ አገልጋያችሁ በፊታችሁ ሞገስ ስላገኘሁ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርዳታ አድርጋችሁልኛል፤ ነገር ግን ይህ ጥፋት ደርሶብኝ እሞታለሁ ብዬ ስለምሰጋ ወደዚያ ተራራ መሸሽ አልችልም። እኔ በፍጥነት ሸሽቼ ላመልጥበት የምችል እነሆ አንዲት ትንሽ ከተማ በቅርብ አለች፤ ስለዚህ ሸሽቼ ወደ እርሷ እንድሄድ ፍቀዱልኝ፤ እንደምታዩአት ትንሽ ከተማ ናት፤ ወደ እርስዋ ብሄድ ሕይወቴ ከጥፋት ይድናል።” መልአኩም “እሺ አንተ ባልከው እስማማለሁ፤ ይህችን አንተ የምትላትን ከተማ አላጠፋትም፤ ወደዚያች ከተማ እስከምትደርስ ምንም ማድረግ ስለማልችል ፈጥነህ ወደ እርስዋ ሽሽ!” አለው። ሎጥ ያቺን ከተማ ትንሽ ብሎአት ስለ ነበር ጾዓር ተባለች። ሎጥ ወደ ጾዓር ሲደርስ ገና ፀሐይ መውጣትዋ ነበር፤ እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ከተሞች ላይ እሳትና ዲን ከራሱ (ከእግዚአብሔር ዘንድ) ከሰማይ አዘነበ። በዚህ ዐይነት እነዚያን ከተሞችና ሸለቆዎች፥ እዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ፥ በምድሩም ላይ የበቀለውን ነገር ሁሉ ደመሰሰ። የሎጥ ሚስትም ወደ ኋላዋ ስለ ተመለከተች የጨው ዐምድ ሆና ቀረች። አብርሃም በማግስቱ ማለዳ ተነሥቶ ከዚህ ቀደም ከእግዚአብሔር ጋር ወደተገናኘበት ቦታ ሄደ። ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ ወደ ሸለቆውም ቊልቊል በተመለከተ ጊዜ ከታላቅ ምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ከባድ የእሳት ጢስ ከዚያ ሲወጣ አየ። ሎጥ ይኖርባቸው የነበሩትን፥ በሸለቆ የሚገኙትን ከተሞች፥ እግዚአብሔር ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አስታወሰ፤ ስለዚህም ሎጥን ከጥፋት ወደሚድንበት ቦታ መራው። ሎጥ በጾዓር መቀመጥ ስለ ፈራ እርሱና ሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ወደ ተራራዎቹ ወጥተው መኖሪያቸውን በዋሻ ውስጥ አደረጉ። አንድ ቀን ታላቂቱ ልጁ እኅትዋን እንዲህ አለቻት፦ “አባታችን ማርጀቱ ነው፤ ልጆች እንድንወልድ እኛን የሚያገቡ ወንዶች በዙሪያችን የሉም፤ ከእርሱ ጋር ተኝተን ከእርሱ ልጆች እንድናገኝ አባታችንን የወይን ጠጅ አጠጥተን እናስክረው።” በዚያን ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጥተው አሰከሩት፤ ታላቂቱ ልጁም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አደረገች። ሎጥ ግን በጣም ሰክሮ ስለ ነበር ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም። በማግስቱ ታላቂቱ ልጅ እኅቷን “ትናንት ማታ እኔ ከእርሱ ጋር ተኝቼአለሁ፤ ዛሬም እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተን እናስክረውና አንቺም አብረሽው ተኚ፤ በዚህ ዐይነት ሁለታችንም ከአባታችን ልጆች ወልደን ዘራችን እንዳይጠፋ እናድርግ” አለቻት። ስለዚህ በዚያን ምሽት አባታቸውን እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተው አሰከሩት፤ ታናሽቱ ልጁም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አደረገች፤ አሁንም እጅግ ሰክሮ ስለ ነበር ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም። በዚህ ሁኔታ ሁለቱም የሎጥ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። ታላቂቱ ወንድ ልጅ ወለደችና ስሙን ሞአብ አለችው፤ እርሱ ዛሬ ሞአባውያን ተብለው ለሚጠሩት ሕዝቦች ቅድመ አያት ነው። ታናሽቱም ወንድ ልጅ ወለደችና ስሙን ቤንዐሚ አለችው፤ እርሱ ዛሬ ዐሞናውያን ተብለው ለሚጠሩት ሕዝቦች ቅድመ አያት ነው።
ዘፍጥረት 19:1-38 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፥ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ። ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም፦ “ጌቶቼ ሆይ፥ ወደ ባርያችሁ ቤት አቅኑ፥ ከዚያም እደሩ፥ እግራችሁንም ታጠቡ፥ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፦ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት። እጅግም ዘበዘባቸው፥ ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ፥ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ። ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች፥ ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ፥ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ፥ ቤቱን ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፦ “በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።” ሎጥም ወደ እነርሱ ወደ ደጅ ወጣ፥ መዝጊያውንም በኋላው ዘጋው፥ እንዲህም አለ፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፥ እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፥ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው፥ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና።” እነርሱም፦ “ወዲያ ሂድ” አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ፥ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል፥ አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን።” ሎጥንም እጅግ ተጋፉት፥ የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ። ሁለቱም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት። በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው፥ ሰዎቹም ደጃፉን ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ። ሁለቱም ሰዎች ሎጥን አሉት፦ “ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ ብትሆን በከተማይቱ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸው፥ እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፥ እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል።” ሎጥም ወጣ፥ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም ነገራቸው፥ አላቸውም፦ ተነሡ፥ ከዚህ ስፍራ ውጡ፥ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። አማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው። ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፦ “ተነሣ፥ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፥ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር። እርሱም በዘገየ ጊዜ እግዚአብሔር ስላዘነለት እነዚያ ሰዎች የእርሱን እጅ የሚስቱንም እጅ የሁለቱን የሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡትና በከተማይቱ ውጭ አስቀመጡት። ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኋላ እንዲህ አሉት፦ “ራስህን አድን፥ ወደ ኋላህ አትይ፥ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ።” ሎጥም፥ አላቸው፦ “ጌቶቼ ሆይ፥ እንዲህስ አይሁን፥ እነሆ ባርያህ በፊትህ ሞገስን አግኝቶአል፥ ነፍሴን ለማዳን ያደረግህልኝን ምሕረትህንም አብዝተሃል፥ ክፉ እንዳያገኘኝና እንዳልሞት ወደ ተራራ ሸሽቼ አመልጥ ዘንድ አልችልም፥ እነሆ ይህች ከተማ ወደ እርሷ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ናት፥ እርሷም ትንሽ ናት፥ ነፍሴን ለማዳን ወደ እርሷ ሸሽቼ ላምልጥ፥ እርሷ ትንሽ ከተማ አይደለችምን?” እርሱም አለው፦ “የተናገርሃትን ከተማ እንዳላጠፋት እነሆ በዚህ ነገር የለመንኸኝን ተቀብዬሃለሁ፥ በቶሎ ወደዚያ ሸሽትህ አምልጥ፥ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ጾዓር ተባለ። ሎጥ ወደ ዞዓር በገባ ጊዜ ፀሐይ በምድር ላይ ወጣች። እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፥ እነዚያንም ከተሞች፥ በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ፥ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ። የሎጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመለከተች፥ የጨው ሐውልትም ሆነች። አብርሃምም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ስፍራ ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፥ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ በዚያች አገር ወዳለውም ምድር ሁሉ ተመለከተ፥ እነሆም የአገሪቱ ጢስ እንደ እቶን ጢስ ሲነሣ አየ። እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፥ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው። ሎጥም ከዞዓር ወጣ፥ በዞዓር ይቀመጥ ዘንድ ስለ ፈራም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ፥ በዋሻም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር ተቀመጠ። ታላቂቱም ታናሺቱን አለቻት፦ “አባታችን ሸመገለ፥ በምድርም ሁሉ እንዳለው ልማድ ሊገናኘን የሚችል ሰው ከምድር ላይ የለም፥ ነዪ አባታቻንንም የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፥ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” በዚያችም ሌሊት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፥ ታላቂቱም ገባች፥ ከአባትዋም ጋር ተኛች፥ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። በማግስቱም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፦ “እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፥ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፥ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ አጠጡት፥ ታናሺቱም ገብታ ከእርሱ ጋር ተኛች፥ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፥ እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው። ታናሺቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም፦ የወገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራችው፥ እርሱም እስከ ዛሬ የአሞናውያን አባት ነው።