ዘፍጥረት 18:10-14 - Compare All Versions

ዘፍጥረት 18:10-14 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እግዚአብሔርም፣ “ጊዜው ሲደርስ በርግጥ በዚህ ጊዜ በሚቀጥለው ዓመት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው። ሣራም በዚህ ጊዜ ከበስተጀርባው ካለው ከድንኳኑ ደጃፍ ሆና ትሰማ ነበር። በዚያ ጊዜ አብርሃምና ሣራ አርጅተው፣ ዕድሜያቸው ገፍቶ ነበር፤ ሣራም ልጅ የመውለጃዋ ዕድሜ ዐልፎ ነበር። ሣራ በልቧ፣ “ካረጀሁና ጌታዬም ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛል?” ብላ ሣቀች። እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሣራ፣ ‘ካረጀሁ በኋላ ልጅ እንዴት አድርጌ እወልዳለሁ’ ስትል ለምን ሣቀች? ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? ጊዜው ሲደርስ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅ ይኖራታል።”

ዘፍጥረት 18:10-14 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከሦስቱም እንግዶች አንዱ አብርሃምን “የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው። እርሱም ይህን በሚናገርበት ጊዜ ሣራ በስተኋላው በድንኳኑ ደጃፍ ቆማ ታዳምጥ ነበር፤ አብርሃምና ሣራ በዕድሜአቸው መግፋት አርጅተው ነበር፤ የሣራም፥ ልጅ የመውለጃ ዕድሜዋ አልፎ ነበር። ስለዚህ ሣራ “እኔ አሁን እንዲህ ካረጀሁ በኋላ ጌታዬ አብርሃምም ካረጀ በኋላ እንዲህ ያለ ደስታ ሊኖረኝ ይችላልን?” ብላ በማሰብ ሳቀች። እግዚአብሔርም አብርሃምን “ሣራ ‘እንደዚህ ካረጀሁ በኋላ ልጅ መውለድ እችላለሁን’ በማለት ስለምን ሳቀች? ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።

ዘፍጥረት 18:10-14 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እር​ሱም፥ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመ​ልሼ እመ​ጣ​ለሁ፤ ሚስ​ትህ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች” አለ። ሣራም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆማ ሳለች ይህን ሰማች። አብ​ር​ሃ​ምና ሣራም በዕ​ድ​ሜ​ያ​ቸው ሸም​ግ​ለው ፈጽ​መው አር​ጅ​ተው ነበር፤ በሴ​ቶች የሚ​ሆ​ነ​ውም ልማድ ከሣራ ተቋ​ርጦ ነበር። ሣራም ለብ​ቻዋ በል​ብዋ እን​ዲህ ስትል ሳቀች፥ “እስከ ዛሬ ገና ነኝን? ጌታ​ዬም ፈጽሞ ሽም​ግ​ሎ​አል።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ሣራን ለብ​ቻዋ በል​ብዋ ምን አሳ​ቃት? እስከ ዛሬ ገና ነኝን? በእ​ው​ነ​ትስ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ጌታ​ዬም አር​ጅ​ት​ዋል እነሆ፥ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ ብላ​ለ​ችና። በውኑ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች።”

ዘፍጥረት 18:10-14 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እርሱም፥ የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኍላው ሳለች ይህንን ሰማች። አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር። ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፤ ካረጀሁ በኍላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል። እግዚአብሔርም አብርሃምም አለው፤ ካረጀሁ በኍላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች? በውኑ ለእግዚአሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንድ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታግኝለች።

ዘፍጥረት 18:10-14 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እርሱም፦ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፥ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች” አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኋላው ሳለች ይህንን ሰማች። አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር፥ በሴቶች የሚሆነውም ልማድ ከሣራ ተቋርጦ ነበር። ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል።” እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች? በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፥ ሣራም ልጅን ታገኛለች።”