ዘፍጥረት 15:18 - Compare All Versions
ዘፍጥረት 15:18 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
በዚያችም ቀን እግዚአብሔር ለአብራም ተስፋ ያደረገለትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣታለሁ፤
ዘፍጥረት 15:18 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤
ዘፍጥረት 15:18 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፤
ዘፍጥረት 15:18 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
ዘፍጥረት 15:18 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥