ዘፍጥረት 13:16 - Compare All Versions

ዘፍጥረት 13:16 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ዘር​ህ​ንም እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የባ​ሕር አሸ​ዋን ይቈ​ጥር ዘንድ የሚ​ችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈ​ጠ​ራል።

ዘፍጥረት 13:16 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ዘርህን እንደ ምድር ትቢያ አበዛዋለሁ፤ ማንም የምድርን ትቢያ ሊቈጥር እንደማይችል ሁሉ የአንተም ዘር የማይቈጠር ይሆናል።

ዘፍጥረት 13:16 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ የምድርን አሸዋን ይቆጥር ዘንድ የሚችል ስው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቆጠራል።

ዘፍጥረት 13:16 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ የምድር አሸዋ ሊቈጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር እንዲሁ ሊቈጠር የማይቻል ይሆናል።

ዘፍጥረት 13:16 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፥ የምድርን አሸዋን ይቈጥር ዘንድ የሚችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈጠራል።