ዘፍጥረት 10:9 - Compare All Versions
ዘፍጥረት 10:9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኀያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት ኀያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ።
ዘፍጥረት 10:9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ዐዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ ዐዳኝ” ይባል ነበር።
ዘፍጥረት 10:9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያክ አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፥ በእግዚአብሔር ፊት ኃያክ አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ።
ዘፍጥረት 10:9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ናምሩድ በእግዚአብሔር ድጋፍ ታላቅ አዳኝ ነበረ፤ ሰዎች “እንደ ናምሩድ ታላቅ አዳኝ ያድርግህ!” እያሉ የሚመርቁት ስለዚህ ነው።
ዘፍጥረት 10:9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
በጌታ ፊት ናምሩድ ኃያል አዳኝ ነበረ፥ ስለዚህም፦ “እንደ ናምሩድ በጌታ ፊት ኃያል አዳኝ” ይባላል።