ዘፍጥረት 1:30
ዘፍጥረት 1:30 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እንዲሁም በምድር ላይ ለሚኖሩ እንስሶች ሁሉ፥ በሰማይ ለሚበርሩ ወፎች ሁሉ፥ በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ ለሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ፥ በአጠቃላይ የሕይወት እስትንፋስ ላለው ፍጥረት ሁሉ ምግብ እንዲሆናቸው ልምላሜ ያለውን ሣርና ቅጠል ሁሉ ሰጥቻቸዋለሁ።” እንዲሁም ሆነ።
ያጋሩ
ዘፍጥረት 1 ያንብቡዘፍጥረት 1:30 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ለምድር አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ ሐመልማሉ ሁሉ መብል ይሁንላችሁ።” እንዲሁም ሆነ።
ያጋሩ
ዘፍጥረት 1 ያንብቡዘፍጥረት 1:30 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንዲሁም ለምድር አራዊት ሁሉ፣ ለሰማይ ወፎች ሁሉ፣ በምድር ላይ ለሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ” እንዳለውም ሆነ።
ያጋሩ
ዘፍጥረት 1 ያንብቡዘፍጥረት 1:30 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ለምድርም አራዊት ሁሉ ለሰማይም ወፎች ሁሉ ሕያዉ ነፍስ ላላቸዉ ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸዉ እንዲሁም ሆነ።
ያጋሩ
ዘፍጥረት 1 ያንብቡ