ዘፍጥረት 1:25 - Compare All Versions

ዘፍጥረት 1:25 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ድር አራ​ዊ​ትን እን​ደ​የ​ወ​ገኑ፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንም እን​ደ​የ​ወ​ገኑ፥ በም​ድር የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ እን​ደ​የ​ወ​ገኑ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።

ዘፍጥረት 1:25 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።

ዘፍጥረት 1:25 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እግዚአብሔርም የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ አደረገ እንስሳዉንም እንደ ወገኑ የመሬት ተንቀሳቃሾችም እንደ ወገኑ አደረገ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።

ዘፍጥረት 1:25 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር የምድር አራዊትን በየዐይነቱ፥ እንስሶችን በየዐይነታቸው በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችን በየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።

ዘፍጥረት 1:25 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።