ዘፍጥረት 1:1-27

ዘፍጥረት 1:1-27 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። ምድርም ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች። የምድርን ጥልቅ ስፍራ ሁሉ ጨለማ ውጦት ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር። እግዚአብሔርም “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ ብርሃኑን ከጨለማ ለየ። እግዚአብሔርም ብርሃኑን “ቀን”፣ ጨለማውን “ሌሊት” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ የመጀመሪያ ቀን። እግዚአብሔር፣ “ውሃን ከውሃ የሚለይ ጠፈር በውሆች መካከል ይሁን” አለ። ስለዚህ እግዚአብሔር ጠፈርን አድርጎ ከጠፈሩ በላይና ከጠፈሩ በታች ያለውን ውሃ ለየ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ ሁለተኛ ቀን። ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ ደረቁ ምድር ይገለጥ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር ደረቁን ምድር፣ “የብስ”፣ በአንድነት የተሰበሰበውን ውሃ፣ “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔር፣ “ምድር ዕፀዋትንም፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በምድር ላይ ዘር ያዘሉ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። ምድር ዕፀዋትን፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በውስጣቸው ዘር ያለባቸው ፍሬ የሚያፈሩትን ዛፎች በየወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። መሸ፤ ነጋም፤ ሦስተኛ ቀን። ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ቀኑን ከሌሊት እንዲለዩ፣ የዓመት ወቅቶች፣ ቀናትና ዓመታት የሚጀምሩበትንም እንዲያመለክቱ፣ ለምድር ብርሃን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ይሁኑ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር፣ ለምድር ብርሃን ይሰጡ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናት አደረገ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲሠለጥን አደረገ። እንዲሁም ከዋክብትን አደረገ። ለምድር ብርሃን እንዲሰጡ እግዚአብሔር እነዚህን በሰማይ ጠፈር አኖራቸው። ይኸውም በቀንና በሌሊት እንዲሠለጥኑ፣ ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። መሸ፤ ነጋም፣ አራተኛ ቀን። እግዚአብሔር፣ “ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጥረታት ይሞሉ፤ ወፎች ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። በዚህ መሠረት፣ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ታላላቅ ፍጥረታትን፣ በውሃ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ እንደየወገናቸው እንዲሁም ክንፍ ያላቸውን ወፎች ሁሉ እንደየወገናቸው ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕርንም ውሃ ሙሏት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። መሸ፤ ነጋም፤ ዐምስተኛ ቀን። እግዚአብሔር፣ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንደ ወገኑ ታስገኝ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔር፣ “ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን እንሥራ፤ በባሕር ዓሦች፣ በሰማይ ወፎች፣ በከብቶች፣ በምድር ሁሉ ላይ፣ እንዲሁም በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።

ዘፍጥረት 1:1-27 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በመ​ጀ​መ​ሪያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጠረ። ምድር ግን ባዶ ነበ​ረች፤ አት​ታ​ይ​ምም ነበር፤ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ችም አል​ነ​በ​ረ​ችም፤ ጨለ​ማም በው​ኃው ላይ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በው​ኃው ላይ ይሰ​ፍፍ ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ብር​ሃን ይሁን” አለ፤ ብር​ሃ​ንም ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃኑ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በብ​ር​ሃ​ኑና በጨ​ለ​ማው መካ​ከል ለየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃ​ኑን “ቀን፥” ጨለ​ማ​ው​ንም “ሌሊት” ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አን​ደኛ ቀንም ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በው​ኃው መካ​ከል ጠፈር ይሁን፤ በው​ኃና በውኃ መካ​ከ​ልም ይለይ” አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠፈ​ርን አደ​ረገ፤ ከጠ​ፈር በላ​ይና ከጠ​ፈር በታች ያሉ​ት​ንም ውኆች ለየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን ጠፈር “ሰማይ” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ሁለ​ተ​ኛም ቀን ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ማይ በታች ያለው ውኃ በአ​ንድ ስፍራ ይሰ​ብ​ሰብ፥ የብ​ሱም ይገ​ለጥ አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ። ከሰ​ማይ በታች ያለው ውኃም በመ​ጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያው ተሰ​በ​ሰበ፤ የብ​ሱም ተገ​ለጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የብ​ሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ የውኃ መጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያ​ው​ንም “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “ምድር በየ​ዘሩ፥ በየ​ወ​ገ​ኑና በየ​መ​ልኩ ዘር የሚ​ሰጥ ቡቃ​ያን፥ በም​ድ​ርም ላይ በየ​ወ​ገኑ ዘሩ በው​ስጡ የሚ​ገ​ኘ​ው​ንና ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ዛፍ ታብ​ቅል” አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ። ምድ​ርም በየ​ዘሩ፥ በየ​ወ​ገ​ኑና በየ​መ​ልኩ የሚ​ዘራ ቡቃ​ያን፥ በም​ድር ላይ በየ​ወ​ገኑ ዘሩ በው​ስጡ የሚ​ገ​ኘ​ው​ንና ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ዛፍ አበ​ቀ​ለች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ። ሦስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀ​ንና በሌ​ሊ​ትም ይለዩ ዘንድ ብር​ሃ​ናት በሰ​ማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለም​ል​ክ​ቶች፥ ለዘ​መ​ናት፥ ለዕ​ለ​ታት፥ ለዓ​መ​ታ​ትም ይሁኑ። በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በሰ​ማይ ጠፈር ለማ​ብ​ራት ይሁኑ፤” እን​ዲ​ሁም ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሁለት ታላ​ላቅ ብር​ሃ​ና​ትን አደ​ረገ፤ ትልቁ ብር​ሃን ቀንን እን​ዲ​መ​ግብ፥ ትንሹ ብር​ሃ​ንም ከከ​ዋ​ክ​ብት ጋር ሌሊ​ትን እን​ዲ​መ​ግብ አደ​ረገ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰ​ማይ ጠፈር አኖ​ራ​ቸው፤ መዓ​ል​ት​ንና ሌሊ​ት​ንም እን​ዲ​መ​ግቡ፥ በመ​ዓ​ል​ትና በሌ​ሊ​ትም መካ​ከል እን​ዲ​ለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አራ​ተ​ኛም ቀን ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ውኃ የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋስ ያላ​ቸ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችና በም​ድር ላይ ከሰ​ማይ በታች የሚ​በ​ርሩ አዕ​ዋ​ፍን ታስ​ገኝ፥” እን​ዲ​ሁም ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላ​ላቅ አን​በ​ሪ​ዎ​ችን፥ ውኃ ያስ​ገ​ኘ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሕያው ፍጥ​ረ​ትን ሁሉ በየ​ወ​ገኑ፥ የሚ​በ​ርሩ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ፈጠረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ባረ​ካ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባ​ዙም፤ የባ​ሕ​ር​ንም ውኃ ሙሉ​አት፤ ወፎ​ችም በም​ድር ላይ ይብዙ።” ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አም​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ምድር ሕያ​ዋን ፍጥ​ረ​ታ​ትን እንደ ወገኑ፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንና ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችን፥ የም​ድር አራ​ዊ​ት​ንም እን​ደ​የ​ወ​ገኑ ታውጣ፥” እን​ዲ​ሁም ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ድር አራ​ዊ​ትን እን​ደ​የ​ወ​ገኑ፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንም እን​ደ​የ​ወ​ገኑ፥ በም​ድር የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ እን​ደ​የ​ወ​ገኑ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ሰውን በአ​ር​ኣ​ያ​ች​ንና በአ​ም​ሳ​ላ​ችን እን​ፍ​ጠር፤ የባ​ሕር ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ችን፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንና ምድ​ርን ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትን ሁሉ ይግዛ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ሳል ፈጠ​ረው። ወን​ድና ሴት አድ​ርጎ ፈጠ​ራ​ቸው።

ዘፍጥረት 1:1-27 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። ምድርም ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች። የምድርን ጥልቅ ስፍራ ሁሉ ጨለማ ውጦት ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር። እግዚአብሔርም “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ ብርሃኑን ከጨለማ ለየ። እግዚአብሔርም ብርሃኑን “ቀን”፣ ጨለማውን “ሌሊት” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ የመጀመሪያ ቀን። እግዚአብሔር፣ “ውሃን ከውሃ የሚለይ ጠፈር በውሆች መካከል ይሁን” አለ። ስለዚህ እግዚአብሔር ጠፈርን አድርጎ ከጠፈሩ በላይና ከጠፈሩ በታች ያለውን ውሃ ለየ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ ሁለተኛ ቀን። ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ ደረቁ ምድር ይገለጥ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር ደረቁን ምድር፣ “የብስ”፣ በአንድነት የተሰበሰበውን ውሃ፣ “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔር፣ “ምድር ዕፀዋትንም፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በምድር ላይ ዘር ያዘሉ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። ምድር ዕፀዋትን፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በውስጣቸው ዘር ያለባቸው ፍሬ የሚያፈሩትን ዛፎች በየወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። መሸ፤ ነጋም፤ ሦስተኛ ቀን። ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ቀኑን ከሌሊት እንዲለዩ፣ የዓመት ወቅቶች፣ ቀናትና ዓመታት የሚጀምሩበትንም እንዲያመለክቱ፣ ለምድር ብርሃን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ይሁኑ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር፣ ለምድር ብርሃን ይሰጡ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናት አደረገ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲሠለጥን አደረገ። እንዲሁም ከዋክብትን አደረገ። ለምድር ብርሃን እንዲሰጡ እግዚአብሔር እነዚህን በሰማይ ጠፈር አኖራቸው። ይኸውም በቀንና በሌሊት እንዲሠለጥኑ፣ ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። መሸ፤ ነጋም፣ አራተኛ ቀን። እግዚአብሔር፣ “ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጥረታት ይሞሉ፤ ወፎች ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። በዚህ መሠረት፣ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ታላላቅ ፍጥረታትን፣ በውሃ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ እንደየወገናቸው እንዲሁም ክንፍ ያላቸውን ወፎች ሁሉ እንደየወገናቸው ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕርንም ውሃ ሙሏት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። መሸ፤ ነጋም፤ ዐምስተኛ ቀን። እግዚአብሔር፣ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንደ ወገኑ ታስገኝ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔር፣ “ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን እንሥራ፤ በባሕር ዓሦች፣ በሰማይ ወፎች፣ በከብቶች፣ በምድር ሁሉ ላይ፣ እንዲሁም በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።

ዘፍጥረት 1:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ስማይንና ምድርን ፈጠረ። ምድርም ባዶ ነበረች፤ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ስፍፎ ነበር። እግዚአብሔርም፤ ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ። እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ። እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራዉ። ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ አንድ ቀን። እግዚአብሔርም፤ በዉኖች መካከል ጠፈር ይሁን በዉኂ መካከል ይከፈል አለ። እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኖች ለየ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን ሰማይ ብሎ ጠራዉ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ ሁሉተኚ ቀን። እግዚአብሔርም፤ ከሰማይ በታች ያለዉ ውኂ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን ምድር ብሎ ጠራዉ የዉኂ መከማቻዉንም ባሕር አለዉ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም፤ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ። ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሦስተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፤ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ እንዲሁም ሆነ። እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን ከዋክብትም ደግሞ አደረገ። እግዚአሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፤ በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ አራተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፤ ዉኂ ሕያዉ ነፍስ ያላቸዉን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ። እግዚእብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን ውኂይቱ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚእብሔርም እንድህ ብሎ ባረካቸው፤ ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኂ ሙሉአት ውፎችም በምድር ላይ ይብዙ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ አምስተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ታዉጣ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ አደረገ እንስሳዉንም እንደ ወገኑ የመሬት ተንቀሳቃሾችም እንደ ወገኑ አደረገ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም አለ፤ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን እንስሳትንና ምድርን ሁ፤ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰዉን በመልኩ ፈጠረ በእግአብሔር መልክ ፈጠራቸዉ።

ዘፍጥረት 1:1-27 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። እግዚአብሔርም፥ ብርሃን መልካም መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔርም ብርሃንን ከጨለማ ለየ። እግዚአብሔር ብርሃኑን “ቀን” ብሎ ጠራው፤ ጨለማውንም “ሌሊት” ብሎ ሰየመው። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ ይህም አንድ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃውን ከውሃ የሚለይ ጠፈር ይሁን” አለ፤ በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ጠፈርን ፈጠረ፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉት ውሆች ይለያዩ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ፥ ሌሊቱም ነጋ፤ ሁለተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “የብሱ ግልጥ ሆኖ እንዲታይ ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ሁሉ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” ብሎ ሰየመው፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር አትክልትን፥ የእህል አዝርዕትን፥ ፍሬ የሚያፈሩ የፍሬ ዛፎችንና ተክሎችን በየዐይነቱ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። በዚህ ዐይነት ምድር አትክልትን፥ በየዐይነቱ የእህል አዝርዕትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን አበቀለች፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ ሦስተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ቀንን ከሌሊት ለመለየት ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ ይሁኑ፤ ለዕለታት፥ ለክፍላተ ዓመትና ለዓመታት መለያ ምልክት ይሁኑ፤ ለምድር ብርሃን ለመስጠት በሰማይ ጠፈር ላይ ሆነው ያብሩ” እንዲሁም ሆነ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን ፈጠረ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን፥ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲያበሩ አደረገ፤ እንዲሁም ከዋክብትን ፈጠረ፤ ለምድር ብርሃንን እንዲሰጡ እነዚህን ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ አኖራቸው፤ ይህንንም ያደረገው በቀንና በሌሊት ላይ ሥልጣን እንዲኖራቸውና ጨለማን ከብርሃን እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ አራተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃ ሕይወት ባላቸው በልዩ ልዩ ፍጥረቶች የተሞላ ይሁን፤ ወፎችም ከምድር በላይ ባለው በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ታላላቅ የባሕር አውሬዎችን፥ ሌሎችንም በውሃ ውስጥ የሚኖሩና የሚንቀሳቀሱ ልዩ ልዩ ፍጥረቶችን እንደየዐይነታቸው፥ እንዲሁም ልዩ ልዩ ወፎችን እንደየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። እግዚአብሔር “ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ የባሕርን ውሃ ይሙላ፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ አምስተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶችን፥ እንደየዐይነታቸው እንስሶችን፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችንና አራዊትን እንደየዐይነታቸው ታስገኝ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር የምድር አራዊትን በየዐይነቱ፥ እንስሶችን በየዐይነታቸው በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችን በየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ሰውን በመልካችንና በአምሳያችን እንፍጠር፤ ሰዎችም በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሣዎች፥ በሰማይ በሚበርሩ ወፎች፥ በእንስሶችና በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ በሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች፥ እንዲሁም በምድር ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎም ፈጠራቸው።

ዘፍጥረት 1:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። ምድርም ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር። እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ። እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ። እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንደኛ ቀን። እግዚአብሔርም፦ “በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል” አለ። እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ፥ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሁለተኛ ቀን ሆነ። እግዚአብሔርም፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፥ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” አለው፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። እግዚአብሔርም፦ “ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል” አለ፥ እንዲሁም ሆነ። ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሦስተኛ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፦ “ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፥ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፥ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ፥” እንዲሁም ሆነ። እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፥ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፥ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ። እግዚአሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፥ በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ፥ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አራተኛ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፦ “ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ።” እግዚእብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውን ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። እግዚእብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፥ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።” ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አምስተኛ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፦ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። እግዚአብሔርም አለ፦ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፥ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።” እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፥ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፥ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።