ገላትያ 6:8-9 - Compare All Versions

ገላትያ 6:8-9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን።

ገላትያ 6:8-9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሥጋውን ለማስደሰት የሚዘራ ከሥጋው ሞትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ከመንፈስ የዘለዓለም ሕይወትን ያጭዳል። ተስፋ ካልቈረጥን ወቅቱ ሲደርስ መከር ስለምንሰበስብ መልካም ሥራን ከመሥራት አንስነፍ።

ገላትያ 6:8-9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በሥ​ጋው የሚ​ዘራ ሞትን ያጭ​ዳል፤ በመ​ን​ፈ​ሱም የሚ​ዘራ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ያጭ​ዳል። በጎ ሥራ መሥ​ራ​ትን ቸል አን​በል፥ በጊ​ዜው እና​ገ​ኘ​ዋ​ለ​ንና።

ገላትያ 6:8-9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።

ገላትያ 6:8-9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ምክንያቱም ወደ ገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፥ በመንፈስ የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘለዓለምን ሕይወት ያጭዳል። መልካምን ሥራ ለመሥራት አንታክት፥ ካልዛልን ወቅቱ በደረሰ ጊዜ እናጭዳለንና።