ገላትያ 6:4-7
ገላትያ 6:4-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ለሌላ ያይደለ ለራሱ መመኪያ እንዲሆነው ሁሉም ሥራዉን ይመርምር። ሁሉም ሸክሙን ይሸከማልና። ይህንም ነገር ንኡሰ ክርስቲያን ይስማው፤ መልካሙንም ነገር ሁሉ ከሚያስተምረው ይማር። አያስቱአችሁ፤ በእግዚአብሔርም የሚዘብት አይኑር፤ ሰውም የሚዘራውን ያጭዳል።
ያጋሩ
ገላትያ 6 ያንብቡገላትያ 6:4-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እያንዳንዱ የራሱን ተግባር ይመርምር፤ ከዚያም በኋላ፣ ከሌላ ሰው ጋራ ራሱን ሳያወዳድር፣ ስለ ራሱ የሚመካበትን ያገኛል፤ እያንዳንዱ የራሱን ሸክም ሊሸከም ይገባዋልና። ማንም ቃሉን የሚማር፣ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ከመምህሩ ጋራ ይካፈል። አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል።
ያጋሩ
ገላትያ 6 ያንብቡገላትያ 6:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና። ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል። አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤
ያጋሩ
ገላትያ 6 ያንብቡ