ገላትያ 3:6-8
ገላትያ 3:6-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አብርሃም በእግዚአብሔር እንደ አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ እንደ ተቈጠረለት፥ እንግዲህ ያመኑት የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ ታውቃላችሁ። እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቃቸው መጽሐፍ አስቀድሞ ገልጦአልና፤ አሕዛብም ሁሉ በእርሱ እንዲባረኩ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለአብርሃም ተስፋ ሰጠው።
ያጋሩ
ገላትያ 3 ያንብቡገላትያ 3:6-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ልክ እንደዚሁ፣ አብርሃም “እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።” እንግዲህ እነዚያ የሚያምኑት የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ አስተውሉ። መጽሐፍ፣ እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቅ አስቀድሞ በማየት፣ “አሕዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ” በማለት ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ አስታወቀው።
ያጋሩ
ገላትያ 3 ያንብቡገላትያ 3:6-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንዲሁ አብርሃም በእግዚአብሔር አመነና ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። እንኪያስ ከእምነት የሆኑት እነዚህ የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ እወቁ። መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ።
ያጋሩ
ገላትያ 3 ያንብቡ