ገላትያ 1:1-5
ገላትያ 1:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና ከሙታን ለይቶ በአስነሣው በእግዚአብሔር አብ ነው እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ሐዋርያ ካልሆነ ከጳውሎስ፥ አብረውኝ ካሉ ከወንድሞቻችንም፥ በገላትያ ላሉ አብያተ ክርስቲያን፤ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን። በክፉ ከሚቃወም ከዚህ ዓለም ያድነን ዘንድ በአባታችን በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ኀጢአታችን ራሱን አሳልፎ ሰጠ። ለእርሱ ክብር ይሁን፤ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አሜን።
ገላትያ 1:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከሰዎች ወይም በሰው ከተላከው ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስና ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤ ዐብረውኝም ካሉት ወንድሞች ሁሉ፤ በገላትያ ላሉት አብያተ ክርስቲያናት፦ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ፣ ከዚህ ክፉ ዓለም ያድነን ዘንድ ስለ ኀጢአታችን ራሱን ሰጠ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለርሱ ክብር ይሁን። አሜን።
ገላትያ 1:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፦ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ። ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
ገላትያ 1:1-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በሰዎች ወይም በሰው አማካይነት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስና እርሱንም ከሞት ባስነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ ሆኜ ከተላክሁ ከእኔ ከጳውሎስ፥ ከእኔም ጋር ካሉት ወንድሞች ሁሉ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያን የተላከ። ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ከዚህ ከክፉ ዘመን ያድነን ዘንድ በአምላካችንና በአባታችን ፈቃድ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ። ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን! አሜን።
ገላትያ 1:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከሰዎች ወይም በሰው አማካኝነት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስና እርሱንም ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፤ ከእግዚአብሔር አብና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። እንደ አምላካችንና አባታችን ፈቃድ፥ ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ሊያድነን፥ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ። ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።