ዕዝራ 9:9 - Compare All Versions

ዕዝራ 9:9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ባሪ​ያ​ዎቹ ነንና፥ አም​ላ​ካ​ችን ግን በባ​ር​ነ​ታ​ችን አል​ተ​ወ​ንም፤ ቀለ​ባ​ች​ንን ይሰ​ጡን ዘንድ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ን​ንም ቤት ከፍ ከፍ ያደ​ርጉ ዘንድ፥ የተ​ፈ​ታ​ው​ንም ይጠ​ግኑ ዘንድ፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ያደ​ር​ጉ​ልን ዘንድ በፋ​ርስ ነገ​ሥ​ታት ፊት ሞገ​ስን ሰጠን።

ዕዝራ 9:9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ባሮች ብንሆንም፣ አምላካችን ግን ባሮች ሆነን እንድንቀር አልተወንም፤ ነገር ግን በፋርስ ነገሥታት ፊት ቸርነቱን አሳየን፤ የአምላካችንን ቤት እንደ ገና እንድንሠራና ፍርስራሾቿን እንድንጠግን አዲስ ሕይወት ሰጠን፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም የመከላከያ ቅጥር ሰጠን።

ዕዝራ 9:9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ባሪያዎች ነንና፥ አምላካችን ግን በባርነታችን አልተወንም፤ የሕይወት መታደስን ይሰጠን ዘንድ፥ የአምላካችንንም ቤት እንሠራ ዘንድ፥ የተፈታውንም እንጠግን ዘንድ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም ቅጥር ይደረግልን ዘንድ በፋርስ ነገሥታት ፊት ምሕረቱን ሰጠን።

ዕዝራ 9:9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እኛ ባርያዎች ነበርን፤ አንተ ግን ባርያዎች ሆነን እንድንቀር አልተውከንም፤ አንተ የፋርስ ነገሥታት እንዲራሩልንና በሕይወት ነጻ ወጥተን ቀደም ሲል ፈርሶ የነበረውን ቤተ መቅደስህን እንደገና መልሰን እንድንሠራ፥ እዚህም በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሰላም እንድንኖር ፈቀድክልን።

ዕዝራ 9:9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ባርያዎች ነን፥ አምላካችን ግን በባርነታችን አልተወንም፥ የአምላካችንን ቤት እንድንሠራና ፍርስራሾቹን እንድንጠግን መታደስን ሊሰጠን፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም ግንብ ሊሰጠን በፋርስ ነገሥታት ፊት ፅኑ ፍቅሩን በእኛ ላይ ዘረጋ።