ሕዝቅኤል 34:27
ሕዝቅኤል 34:27 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የምድረ በዳ ዛፍም ፍሬውን ይሰጣል፤ ምድርም ቡቃያዋን ትሰጣለች፤ በምድራቸውም በሰላም ታምነው ይኖራሉ፤ የቀንበራቸውንም ማነቆ በሰበርሁ ጊዜ፥ ከሚገዙአቸውም እጅ ባዳንኋቸው ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ሕዝቅኤል 34:27 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የየሜዳው ዛፍ ፍሬ ይሰጣል፤ መሬቱም እህል ያበቅላል። ሕዝቡም በምድሪቱ ላይ ያለ ሥጋት ይኖራሉ። የቀንበሮቻቸውን ማነቆ ሰብሬ በባርነት ከገዟቸው እጅ ሳድናቸው፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ሕዝቅኤል 34:27 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የምድረ በዳም ዛፍ ፍሬውን ይሰጣል ምድርም ቡቃያዋን ትሰጣለች፥ በምድራቸውም ተዘልለው ይኖራሉ፥ የቀንበራቸውንም ማነቆ በሰበርሁ ጊዜ ከሚገዙአቸውም እጅ ባዳንኋቸው ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።