ሕዝቅኤል 3:20 - Compare All Versions
ሕዝቅኤል 3:20 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኀጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱ ዕንቅፋት ባደርግ፥ እርሱ ይሞታል፤ አንተም አልነገርኸውምና በኀጢአቱ ይሞታል፤ ያደረጋትም የጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
ሕዝቅኤል 3:20 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“ጻድቁ ሰው ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኀጢአት ቢሠራ፣ እኔም መሰናክል በፊቱ ባስቀምጥ እርሱ ይሞታል፤ አንተ አላስጠነቀቅኸውምና በኀጢአቱ ይሞታል፤ ያደረገውም ጽድቅ አይታሰብለትም፤ አንተንም ስለ ደሙ በኀላፊነት እጠይቅሃለሁ።
ያጋሩ
ሕዝቅኤል 3 NASVሕዝቅኤል 3:20 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱም ዕንቅፋትን ሳደርግ፥ እርሱ ይሞታል፥ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል ያደረጋትም ጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
ያጋሩ
ሕዝቅኤል 3 አማ54ሕዝቅኤል 3:20 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
“በደግነቱ የታወቀ ጻድቅ ሰው ክፉ ሥራ መሥራት ቢጀምርና እኔም በችግር ላይ እንዲወድቅ ባደርገው፥ አንተ ካላስጠነቀቅኸው በቀር በኃጢአቱ ይሞታል፤ ከዚያ በፊት የፈጸመው መልካም ሥራ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ስለ እርሱ ሞት አንተን በኀላፊነት እጠይቅሃለሁ።
ያጋሩ
ሕዝቅኤል 3 አማ05ሕዝቅኤል 3:20 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ጻድቁ ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት ከሠራ፥ እኔም በፊቱ ዕንቅፋትን አደርጋለሁ፥ እርሱም ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል፥ የጽድቁም ሥራ አይታሰብለትም፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።