ሕዝቅኤል 24:15-18
ሕዝቅኤል 24:15-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ የዐይንህን አምሮት በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ፤ አንተም ዋይ አትበል፤ አታልቅስም፤ እንባህንም አታፍስስ። በቀስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙታንን ልቅሶ አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፤ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ ከንፈሮችህንም አትሸፍን፤ የዕዝን እንጀራንም አትብላ።” እኔም በማለዳ ለሕዝቡ ተናገርሁ፤ ወደ ማታም ሚስቴ ሞተች፤ በነጋውም እንደ ታዘዝሁ አደረግሁ።
ሕዝቅኤል 24:15-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ የዐይንህ ማረፊያ የሆነውን ነገር በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ፤ አንተ ግን ዋይታ አታሰማ፤ አታልቅስ፤ እንባህንም አታፍስስ፤ ድምፅህን ዝቅ አድርገህ በሐዘን አንጐራጕር እንጂ ለሞተው አታልቅስ። ጥምጥምህን ከራስህ አታውርድ፤ ጫማህንም አታውልቅ፤ አፍህ ድረስ አትሸፋፈን፤ የዕዝን እንጀራም አትብላ።” እኔም በማለዳ ለሕዝቡ ተናገርሁ፤ ሚስቴም ማታውኑ ሞተች፤ በማግስቱም ጧት እንደ ታዘዝሁ አደረግሁ።
ሕዝቅኤል 24:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ የዓይንህን አምሮት በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ፥ አንተም ወይ አትበል አታልቅስም እንባህንም አታፍስስ። በቀስታ ተክዝ፥ ለምዋቾችም አታልቅስ፥ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፥ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፥ ከንፈሮችህንም አትሸፍን የሰዎችንም እንጀራ አትብላ። እኔም በማለዳ ለሕዝቡ ተናገርሁ፥ ወደ ማታም ሚስቴ ሞተች፥ በነጋውም እንደ ታዘዝሁ አደረግሁ።
ሕዝቅኤል 24:15-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የምትወዳትና የዐይንህ መደሰቻ የሆነችው ሚስትህ ተቀሥፋ በድንገት ትሞትብሃለች፤ በዚህም አትዘን፤ እንባህንም በማፍሰስ አታልቅስ፤ በሐዘንም መንሰቅሰቅህን ሰው አይስማህ፤ ለሟችዋ አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህንም በራስህ ላይ አድርግ፤ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ አፍህን አትሸፍን፤ የእዝን እንጀራ አትብላ።” ጠዋት በማለዳም ከሰዎች ጋር እነጋገር ነበር፤ በዚያች ምሽት ሚስቴ ሞተች፤ በሚቀጥለውም ቀን ልክ እንደ ተነገረኝ አደረግሁ።
ሕዝቅኤል 24:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ የዐይንህን ምኞት በቅፅበት እወስድብሃለሁ፤ ቢሆንም ግን ዋይታ አታሰማ፥ አታልቅስ፥ እንባህንም አታፍስስ። በዝምታ ተክዝ፥ ለሙታን አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፥ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ ከንፈርህን አትሸፍን፥ የዕዝን እንጀራም አትብላ። እኔም በማለዳ ለሕዝቡ ተናገርሁ፥ ማታም ሚስቴ ሞተች፤ በማግስቱም እንደ ታዘዝሁ አደረግሁ።