ዘፀአት 9:18-19
ዘፀአት 9:18-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እነሆ፥ ከተመሠረተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግብፅ ሆኖ የማያውቅ እጅግ ታላቅ በረዶ ነገ በዚህ ጊዜ አዘንባለሁ። አሁን እንግዲህ ፥ ከብቶችህንም በሜዳም ያለህን ሁሉ ፈጥነህ ሰብስብ። በሜዳ የተገኘ ወደ ቤት ያልገባ ሰውና እንስሳ ሁሉ በረዶ ወርዶበት ይሞታልና።”
ያጋሩ
ዘፀአት 9 ያንብቡዘፀአት 9:18-19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ ነገ በዚህ ጊዜ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግብጽ ላይ ወርዶ የማያውቅ አስከፊ የበረዶ ማዕበል እልካለሁ። ከብቶችህና በመስክ ላይ ያለህ ማንኛውም ነገር ወደ መጠለያ ይገቡ ዘንድ አሁን ትእዛዝ ስጥ፤ ምክንያቱም በረዶው ወደ መጠለያ ባልገቡትና በመስክ ላይ በቀሩት በማንኛውም ሰውና እንስሳት ላይ ወርዶባቸው ስለሚሞቱ ነው።’ ”
ያጋሩ
ዘፀአት 9 ያንብቡዘፀአት 9:18-19 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እነሆ ነገ በዚህ ጊዜ፥ ከተመሰረተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግብፅ ሆኖ የማያውቅ፥ እጅግ ታላቅ በረዶ አዘንብብሃለሁ። በሜዳ የተገኘ ወደ ቤት ያልገባ ሰውና እንሰሳ ሁሉ በረዶ ወርዶበት ይሞታልና አሁን እንግዲህ ላክ፤ ከብቶችህንም በሜዳም ያለህን ሁሉ አስቸኵል።’”
ያጋሩ
ዘፀአት 9 ያንብቡ