ዘፀአት 9:1-9

ዘፀአት 9:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተህ እን​ዲህ በለው፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ። ሕዝ​ቤን ልት​ለ​ቃ​ቸው እንቢ ብትል፥ ብት​ይ​ዛ​ቸ​ውም፥ እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በሜዳ ውስጥ በአ​ሉት በከ​ብ​ቶ​ችህ፥ በፈ​ረ​ሶ​ችም፥ በአ​ህ​ዮ​ችም፥ በግ​መ​ሎ​ችም፥ በበ​ሬ​ዎ​ችም፥ በበ​ጎ​ችም ላይ ትሆ​ና​ለች፤ ይኸ​ውም እጅግ ጽኑዕ ሞት ነው፤ በዚያ ጊዜም በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ከብ​ቶ​ችና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ቶች መካ​ከል ልዩ​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከብ​ቶች አን​ዳች አይ​ሞ​ትም።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ነገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር በም​ድር ላይ ያደ​ር​ጋል ብሎ ጊዜን ወሰነ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ነገር በነ​ጋው አደ​ረገ፤ የግ​ብ​ፅም ከብት ሁሉ ሞተ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብት ግን አንድ ስንኳ አል​ሞ​ተም። ፈር​ዖ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ እን​ዳ​ል​ሞተ በአየ ጊዜ ልቡ ደነ​ደነ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አል​ለ​ቀ​ቀም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን፥ “እጃ​ች​ሁን ሞል​ታ​ችሁ ከም​ድጃ አመድ ውሰዱ፤ ሙሴም በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ወደ ሰማይ ይበ​ት​ነው። እር​ሱም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ትቢያ ይሆ​ናል፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ሻህኝ የሚ​ያ​መጣ ቍስል ይሆ​ናል” አላ​ቸው።

ዘፀአት 9:1-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ በለው፤ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።” አሁንም እንዳይሄዱ ብታደርግና ብትከለክላቸው፣ የእግዚአብሔር እጅ በመስክ ላይ ባሉት እንስሳት፣ በፈረሶችህና በአህዮችህ፣ በግመሎችህና በቀንድ ከብቶችህ፣ በበጎችህና በፍየሎችህ ላይ አስከፊ መቅሠፍት ያመጣብሃል። ነገር ግን እግዚአብሔር በእስራኤልና በግብጽ እንስሳት መካከል ልዩነት ያደርጋል፤ ይኸውም የእስራኤል የሆነ ማንኛውም እንስሳ እንዳይሞት ነው።’ ” እግዚአብሔር ጊዜን ወስኖ፣ እንዲህ አለ፤ “በነገው ዕለት እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ ይህን ያደርጋል።” በማግስቱም እግዚአብሔር ነገሩን ፈጸመው፤ የግብጻውያን እንስሳት በሙሉ ዐለቁ፤ ነገር ግን የእስራኤላውያን ከሆኑት እንስሳት አንድም አልሞተም። ፈርዖን ያጣሩ ዘንድ ሰዎች ልኮ ከእስራኤላውያኑ እንስሳት አንድም እንኳ አለመሞቱን ተገነዘበ። ያም ሆኖ ልቡ እንደ ደነደነ ስለ ነበር፣ ሕዝቡን አልለቀቀም። ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አላቸው፤ “ከምድጃው ዕፍኝ ዐመድ ወስዳችሁ፣ ሙሴ በፈርዖን ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው። በግብጽ ምድር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፤ በምድሪቱ ሁሉ በሚገኙት ሰዎችና እንስሳት ላይ መግል የያዘ ዕባጭ ይወጣል።”

ዘፀአት 9:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ ወደ ፈርዖን ዘንድ ገብተህ ንገረው፤ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ። ልትለቅቃቸውም እንቢ ብትል ብትይዛቸውም፥ እነሆ የእግዚአብሔር እጅ በሜዳ ውስጥ ባሉት በከብቶችህ፥ በፈረሶችም በአህዮችም፥ በግመሎችም፥ በበሬዎችም፥ በበጎችም ላይ ትሆናለች፤ ብርቱ ቸነፈርም ይወርዳል። እግዚአብሔርም በእስራኤልና በግብፅ ከብቶች መካከል ይለያል፤ ከእስራኤልም ልጆች ከብት አንዳች አይጠፋም።’” እግዚአብሔርም፥ “ነገ እግዚአብሔር ይህን ነገር በምድር ላይ ያደርጋል” ብሎ ጊዜን ወሰነ። እግዚአብሔርም ያንን ነገር በነጋው አደረገ፤ የግብፅም ከብት ሁሉ ሞቱ፤ ከእስራኤል ልጆች ከብት ግን አንድ ስንኳ አልሞተም። ፈርዖንም ላከ፤ እነሆም ከእስራኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አልሞተም። የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ፤ ሕዝቡንም አልለቀቀም። እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ “እጃችሁን ሞልታችሁ ከምድጃ አመድ ውሰዱ፤ ሙሴም በፈርዖን ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው። እርሱም በግብፅ አገር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፥ በግብፅም አገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ሻህኝ የሚያመጣ ቁስል ይሆናል አላቸው፤”

ዘፀአት 9:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ንጉሡ ሄደህ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል በለው፦ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤ ዳግመኛ እምቢ ብትል ግን፥ የእግዚአብሔር እጅ በመስክ የሚገኘውን መንጋህን ማለት ፈረሶችህን፥ አህዮችህን፥ ግመሎችህን፥ የቀንድ ከብቶችህን፥ በጎችህንና ፍየሎችህን በታላቅ መቅሠፍት ይመታል። እግዚአብሔር ግን በእስራኤላውያንና በግብጻውያን እንስሶች መካከል ልዩነት ያደርጋል፤ ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አይሞትም። እግዚአብሔር ይህን ነገር ነገ አደርጋለሁ ብሎ ጊዜውን ወሰነ።’ ” እግዚአብሔርም በተናገረው መሠረት በማግስቱ ይህንኑ አደረገ፤ የግብጻውያን እንስሶች ሁሉ አለቁ፤ ነገር ግን ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አልሞተም። ንጉሡ የሆነውን ሁሉ ለማጣራት ሰዎችን በላከ ጊዜ ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አለመሞቱን ተረዳ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ልቡን ስላደነደነ ሕዝቡን አለቀቀም። ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “በእፍኛችሁ እየዘገናችሁ ከምድጃ ጥቂት ዐመድ ውሰዱ፤ እርሱንም ሙሴ በንጉሡ ፊት ወደ አየር ይበትነው፤ እርሱም እንደ ደቃቅ ትቢያ ሆኖ በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ በሚሠራጭበት ጊዜ በሕዝብና በእንስሶቹ ላይ አሠቃቂ የሆነ ብርቱ ቊስል ያመጣል።”

ዘፀአት 9:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ግባ እንዲህም በለው የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ። ልትለቅቃቸውም እንቢ ብትል፥ ብትይዛቸውም፥ እነሆ የጌታ እጅ በሜዳ ውስጥ ባሉት በከብቶችህ፥ በፈረሶች፥ በአህዮች፥ በግመሎች፥ በበሬዎችና በበጎች ላይ ትሆናለች፤ ብርቱ ተላላፊ በሽታ ይወርዳል። ጌታም በእስራኤልና በግብጽ ከብቶች መካከል ይለያል፤ ከእስራኤልም ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አይሞትም።’” ጌታም፦ “ነገ ጌታ ይህን ነገር በምድር ላይ ያደርጋል” ብሎ ጊዜን ወሰነ። ጌታም ያንን ነገር በማግስቱ አደረገ፥ የግብጽም ከብት ሁሉ ሞተ፤ ከእስራኤል ልጆች ከብት ግን አንድ ስንኳ አልሞተም። ፈርዖንም ላከ፥ እነሆም ከእስራኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አልሞተም። የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ፥ ሕዝቡንም አልለቀቀም። ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “እጃችሁን ሞልታችሁ ከምድጃ አመድ ውሰዱ፥ ሙሴም በፈርዖን ፊት ወደ ሰማያት ይበትነዋል። እርሱም በግብጽ ምድር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፥ በግብጽም ምድር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ፈሳሽ የሚያወጣ ብጉንጅ ይሆናል።”